Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
የልባችን ድርቀት አንዱ መንስኤ ይሄውና!
~
በዚህ ዘመን ከገጠሙን ከባባድ ፈተናዎች ውስጥ አንዱ የልብ ድርቀት ነው። የልብ ድርቀት ከልብ ድካም የከፋ በሽታ ነው። በዚህ በሽታ በፅኑ ከመጠቃታችን የተነሳ ዒባዳችን ጣዕም አጥቷል። ሶላታችን ኹሹዕ የሌለው በድን እንቅስቃሴ ሆኗል። ዚክራችን ወዝ የለውም። ሲጀመር ዚክር እናደርጋለን? ልባችን በመድረቁ የተነሳ በወንጀል የማንደነግጥ ደንታ ቢሶች ሆነናል።
ለዚህ ሁኔታችን ብዙ ምክንያቶች አሉት። በማህበራዊ ሚዲያ የምንከታተላቸው ነገሮች ለዚህ የልባችን ጉዳት የራሳቸው ድርሻ አላቸው። ማንነታችንን በመግራት ላይ አስተዋፅዖ ካላቸው ትምህርቶች ይልቅ አስቂኝ ነገሮችን ማሳደድ ላይ ተጠምደናል። ለዱንያም ይሁን ለዲን ከሚጠቅሙ ቁም ነገር ትምህርቶች ይልቅ ሰዎችን ለማሳቅ የተዘጋጁ ቪዲዮዎች፣ ፅሑፎች የበለጠ ገበያ እንዳላቸው ለማንም የሚታይ ነው። እነዚህን ነገሮች መመልከት ሲበዛ ደግሞ ልባችን እየደነዘዘ፣ ከተቅዋ ያለን ርቀት እየጨመረ ይሄዳል። ይሄ አላህ የጠበቀው ሲቀር ሁላችንም የተለከፍንበት በሽታ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "ሳቅ አታብዙ። የሳቅ መብዛት ልብ ያደርቃል።" አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor