ዛሬ ለሽልማት የቀረበው መፅሐፍ
የአንድ ሺ ዓመት አነጋጋሪው የትንቢት መጽሐፍ
የዓለማችን አስደንጋጭ እና ብዙ የመከራ ዘመናቶች እንዲሁም መጭው የፍሰሀና የደስታ ጊዜያት የተተነተኑበት የወቅቱ ድንቅ መፅሐፍ
"ሥሜን በሰሜን እነግርሃለሁ በዛው በደራስጌ ማርያም ጠብቀኝ "!!
ንጉሱ ዳግማዊ ቴዎድሮስ
ጀምስ ብሩስ ወደ አውሮፓ ካሻገራቸው የኢትዮጵያ የምስጢር መጻሕፍቶች መካከል ፣ ፍካሬ ኢየሱስ ፣ መጽሐፈ ሄኖክ ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ የሚገኙበት ሲሆን ይህ ፍካሬ ኢየሱስ የሣልሳዊ ቴዎድሮስ አነሳስ መፅሐፍ እነዚህን እና መሰል መረጃዎች አካትቶ የተዘጋጀና በታሪካዊ የኢትዮጵያ ገድላትና ድርሳናት ትንተና በልጽጎ የቀረበ የወቅቱ የሚስጥር መጽሀፍ ነው።
በምሥራቅ በኩል ቴዎድሮስ የሚባል ደገኛ ንጉስ ይነሳል። እሱም ፈቃዴን የሚፈጽሙትን ከመከራ ያተረፍኩዋቸውን የሚሰበሰብ ነው። በዚያን ዘመን አቡነ ፀሐይ ወሰላማ የሚባል ጳጳስም ይወጣል ምድርንም ይባርካታል። አብያተ ክርስቲያንም ያድሳል። በበረሃ ፈሳሽ ውሃ ይፈልቃል። ሁሉም ንጉሥ ቃል ይፀናል። ፍቅር በረከት በምድር ላይ ይነግሳል። የአንዲት ላም ወተት የአንድ በሬ እሸት ለብዙ ይበቃል።
በመጀመሪያው እትም ላይ የደረሰኝን መጽሐፍ ገዝቼ እንዳነበብኩ በቀጥታ ወደ አሳታሚው ነበር የደወልኩት በመሆኑም ይህ ለዘመናት ያልተፈታ እንቆቅልሽ ተተንትኖ በማንበቤ የተሰማኝን ደስታ በእውነት አዘጋጁን ላመሰግነው እወዳለሁ።
👉 የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
@azop78