TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
Uzbek
Sayt tili
Russian
English
Uzbek
Saytga kirish
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi
Kanallar qidiruvi
Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Kanallar reytingi
Guruhlar reytingi
Postlar reytingi
Brendlar va shaxslar reytingi
Analitika
Postlarda qidiruv
Telegram'ni kuzatish
SearcheeBot
Telegram-каналлар оламидаги сизнинг йўлбошчингиз.
Ботга ўтиш
reklama
TGAlertsBot
Каналингиз репостлари ва эсловлари ҳақида хабар беради.
Ботга ўтиш
reklama
TGStat Bot
Telegram'дан чиқмай туриб каналлар статистикасини олиш
Ботга ўтиш
reklama
Telegram Analytics
TGStat хизмати янгиликларидан бохабар бўлиш учун обуна бўл!
Каналга ўтиш
reklama
Statistika
Saralanganlar
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
@bekuelmisgov0
Kanal geosi va tili:
Butun dunyo, Inglizcha
Toifa:
Hazil va o‘yin-kulgi
ብቁ ሰራተኛ . ብቁ ቀጣሪ . ብቁ ውሳኔ ሰጭ.
Bog‘liq kanallar
|
O‘xshash kanallar
Kanal geosi va tili
Butun dunyo, Inglizcha
Toifa
Hazil va o‘yin-kulgi
Statistika
Saralanganlar
Kanal siznikimi?
Tasdiqlash
Kanal tarixi
Postlar filtri
Oyni tanlash
O‘chirilganlarni yashirish
Repostlarni yashirish
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
4 Jul, 01:59
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው።
ያየነው የአርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ እና መብራቶችን እና ዲጂታል ስክሪኖችን ያካተተ ሲሆን በተጠናቀቁት የኮሪደር ስራዎች ላይ አገልግሎቱ ተጀምሯል።
ጥራቱን የጠበቀ ዘመናዊ መሠረተ-ልማትን ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማስተሳሰር የከተሞቻችንን ምቹነት የማረጋገጥ ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!
The primary goal of our Corridor Development Program is to make the lives of our citizens more comfortable and modern. The Corridor Development Project we visited in Arba Minch includes modern asphalt roads, street lighting, and digital display screens. The completed corridor infrastructure has now been put into service and has begun providing benefits to the public.
Our efforts to ensure our cities are more livable by integrating high-quality modern infrastructure with green development will continue with even greater commitment.
345
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
4 Jul, 01:58
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
የክህሎት ልህቀት ለቱሪዝም ልማት
ላለፉት ሁለት ቀናት በቱሪዝም ኢንስቲትዩት ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የቱሪዝምና የመስተንግዶ ሳምንት በፓናል ውይይት እና በተለያዩ መርሃ ግብሮች በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው ፓናሊስቶች በተሳተፉበት በዚህ መድረክ፣ መጪውን ዘመን የዋጁ የክህሎት ፍላጎቶች እና የዘርፉ የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ፤ ተቋሙ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ከሚገኘውን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ጋር አብሮ ለመጓዝ ለድጅታል ክህሎት ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ብቁ የሰው ኃይል ማፍራትና እና ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ዋነኛ ተልዕከው መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በሀገራችን በፈጣን ሁኔታ እያደገ የመጣው የቱሪዝም መዳረሻዎችን በሚመጥን መልኩ የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
አክለውም የተቋሙ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ የማድረግ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ የማሰልጠኛ ክፍሎችን በማደራጀት በዘርፉ የልህቀት ማዕከል ለመሆን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በበኩላቸው፤ ዘርፉ ከሚፈልገው እውቀት አኳያ አሁንም በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል የማቅረብ ክፍተት እንዳለ ጠቁመዋል።
ይህንን ክፍተት ለመድፈን ተቋሙ ከመደበኛ ስልጠና በተጨማሪ በአጫጭር ገበያ ተኮር ስልጠናዎች በዓመት ከ6 ሺህ በላይ ዜጎችን እያሰለጠነ ይገኛል ብለዋል፡፡
210
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
4 Jul, 01:58
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
በክልሉ በበጀት ዓመቱ ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ሊቆጠሩ የሚችሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የዕቅድ የትውውቅ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ በበጀት ዓመቱ ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በክልሉ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ የሥራ እድል ፈጠራ መሆኑን ጠቅሰው ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በሚቀጥለው በጀት ዓመትም የተሳለጠና ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን የስራ አጥ ቁጥርን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ በልዩ ትኩረትና በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ መዝረዲን ሁሴን፣ የየቢሮው ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳን ጨምሮ የቢሮው፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መዋቅር የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከቢሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
254
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
21 Jun, 12:57
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በለውጡ መንግሥት የተተገበሩ የሪፎርም ሥራዎች የወጣቶችን ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተጨባጭ ውጤቶችን አስገኝተዋል።
ባለፉት 4 ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ሥራዎች ለ19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠራቸውን ጠቁመው፣ ከዚህም መካከል 75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወጣቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለውጡ ካስገኛቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል ወጣቶች ከተለመደው የቅጥር ሐሳብ ወጥተው ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩና ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፈጠራቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም የቤተሰብ የንግድ ሥራዎች እንዲስፋፉ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን አክለዋል፡፡
የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች መስፋፋትና ለዘርፉ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ለወጣቶች ዘመናዊ፣ ፈጣንና ምቹ የሥራ ዕድሎችን የፈጠረ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍና በአህጉራዊ የዲጂታል የሥራ ገበያ ላይ የሀገሪቱንና የወጣቶቹን ተወዳዳሪነት ማሳደጉን አብራርተዋል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አሕመድ በበኩላቸው፤ ከለውጡ በኋላ የወጣቶችን አቅም በማሳደግ ረገድ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ተስፋ ሰጪ፣ ዘላቂና ክህሎት መር የሥራ ዕድሎችን በተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ አቅም መገንባቱን አብራርተዋል።
በመዲናዋ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወጣት ጋሻው ዓለሙ የመኪና ጎማና ባትሪዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሥራ ላይ መሰማራቱን ጠቅሷል፡፡
የምናመርታቸው ምርቶች የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስና ቆሻሻን ወደ ሀብት ከመቀየር ባለፈ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን የሚያሳድጉና ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ናቸው ብሏል።
በማኅበር በመደራጀት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩ የቤትና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን እያመረቱ መሆናቸውን የተናገረው ደግሞ ወጣት አስቻለው ጌትዬ ነው፡፡
በቀጣይም የምርቶቻቸውን የገበያ ተደራሽነትና የሥራ ዕድሎችን ይበልጥ ለማስፋፋት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግሯል። መረጃው የኢዜአ ነው።
ሰኔ 14/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
470
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
21 Jun, 12:56
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
አካባቢያዊ ጸጋን መሰረት ያደረገው ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን ምርታማነትና ኑሮ የሚያሻሽል ሥራ !
በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን (MSMEs) ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲሁም የኅብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል ያለመ የክህሎት ሥልጠና በአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተሰጥቷል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነትና በቆላማ አካባቢዎች የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP-II) ድጋፍ የተሰናዳው ይህ ሥልጠና፤ በወተት ሀብት ልማት፣ በዶሮ እርባታ እና በዕሴት ሰንሰለት (Value Chain) ላይ ያተኮረ የሥራ ዕድል ፈጠራን መሠረት ያደረገ ነው።
በቆላማ አካባቢዎች ለሚገኙ የሥራ ዕድል ፈጠራ አስተባባሪዎች፣ ባለሙያዎችና ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች የተሰጠው ይህ ሥልጠና ዋና ፋይዳው በቆላማ አካባቢዎች በስፋት የሚገኙትን የተፈጥሮና የእንስሳት ሀብት ጸጋዎች በዘፈቀደ ሳይሆን በእውቀትና በሳይንሳዊ መንገድ በማልማት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም መቀየር ነው ተብሏል።
በአካባቢው ያሉ ኢንተርፕራይዞች ከለመዱት ባህላዊ የእንስሳት አያያዝና እንክብካቤ አሠራር ተላቀው፣ ምርትና ምርታማነትን በሚያሳድጉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂና የአመራረት ስልቶች እንዲተኩ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል ።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ መላኩ ወልደዮሐንስ እንደገለጹት፣ ይህ ስልጠና በቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶችና ሴቶች በእንስሳት ሀብት ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ፣ የገቢ ምንጫቸውን እንዲያሳድጉና የኑሮ ደረጃቸውን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ ዕድል ይከፍታል።
አክለውም በተዘጋጁ ሞጁሎች የተሰጠው ይህ ስልጠና በቆላማ አካባቢዎች በወተት፣ በዶሮ እርባታና በማድለብ ዙሪያ ያሉ እንቅፋቶችን በመለየት ወደ መልካም አጋጣሚና ሰፊ የሥራ ዕድል መቀየር የሚያስችል መንገዶችን ማመላከቱን ገልፀዋል ።
በተጨማሪም በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ሳይወሰን በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመሆኑ፣ ሰልጣኞቹ ወደየክልሎቻቸው ሲመለሱ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በብቃት ለማደራጀት እንዲሁም ነባሮቹን ለመደገፍና ለማጠናከር የሚያስችል እውነተኛ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ሰኔ 12/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
312
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
21 Jun, 12:47
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
የጀርመን የልማት ትብብር ድርጅት (KFW) ልዑካን ቡድን በገዋኔ ግብርና ኮሌጅ የሥራ ጉብኝት አደረገ
በጉብኝቱም የኮሌጁን ሥልጠና በጥራትና በዲጂታላይዜሽን ለማገዝ የሚያስችል ከፍተኛ የድጋፍ ስምምነት ተደርሷል።
በዚህ ስምምነት ኮሌጁን ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የሶላር ኃይል አቅርቦት ለመገንባት ከ800 እስከ 1000 ሜትር ካሬ የሚሸፍን የሶላር ፓወር ተከላ እና አነስተኛና መካከለኛ የሶላር ውኃ መሳቢያ ፓምፖች እንዲገጠሙለት ተወስኗል።
በተጨማሪም ዘመናዊ ላብራቶሪዎች፣ ስማርት ክፍሎች፣ የዲጂታል ሥልጠና አቅሞች፣ የእርሻ ትራክተር እንዲሁም ለተማሪዎች የመስክ ጉዞና ለተቋማዊ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች የድጋፉ አካል መሆናቸው ተገልጿል።
በኮሌጁ ውስጥ የወተትና የወተት ተዋፅኦ ማቀናበሪያ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀናበሪያ፣ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
እነዚህ በኢንዱስትሪ ደረጃ የሚቋቋሙ ማዕከላት ለተማሪዎች የተግባር መማሪያ ከመሆናቸውም በላይ፤ ለአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩና የኮሌጁን የውስጥ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ ናቸው ተብሏል።
የKFW ያደረገው ይህ አዲስ ድጋፍ በገንዘብ ሲገመት ከ280 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን፤ ቀደም ሲል ሚኒስቴሩ ባመቻቸው ዕድል ከቻይና መንግስት ያገኘውን የ90 ሚሊዮን ብር የዲጂታላይዜሽን ማጠናከሪያ ድጋፍ ጨምሮ፣ ኮሌጁ በአጠቃላይ ከ370 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአጋር አካላት ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡
ሰኔ 14/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
298
0
0
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር minister of labor and skills
14 Jun, 11:16
Telegram'da ochish
Ulashish
Shikoyat qilish
Prev
Next
451
0
0
7
ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
Yana ko‘rsatilsin
11 378
obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur
የዜጎችን አኗኗር ምቹ እና ዘመናዊ ማድረግ የኮሪደር ልማት መርሃ-ግብራችን ዋነኛ ግብ ነው። ያየነው የአርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ ዘመና...
የክህሎት ልህቀት ለቱሪዝም ልማት ላለፉት ሁለት ቀናት በቱሪዝም ኢንስቲትዩት ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የቱሪዝምና የመስተንግዶ ሳምንት በፓናል ውይይት እና ...
በክልሉ በበጀት ዓመቱ ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ሊቆጠሩ የሚችሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ...