በዝረቱል ኸይር የተርቢያ ማዕከል


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ ቻናል ልጆቻችንን በተርቢያ ለማሳደግ የሚጠቅሙ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት ቻናል ነው።
ለሃሳብ አስተያየት እና በአስተዳደግና ተያያዥ ጉዳዮች ማማከር ለምትፈልጉ @Bezretulkheyrterbiya ያናግሩን።
አድራሻ፡ እንቁላል ፋብሪካ ገተር ሕንጻ 3ኛ ፎቅ 303B
0913993130

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ለልጆችዎ ጥፋት ምላሽ ከመስጠትዎ በፊት እነዚህን ጥያቄዎች ይመልሱ፦
1. ተግባሩ ጥፋት ነው ወይስ በወቅቱ ስላናደዶት ብቻ ነው?
2. ልጆቹ ጥፋቱን ያጠፉት ሆን ብለው ነው ወይስ በድንገት ነው?
3.ያጠፉትን ጥፋት ልጆቹ በራሳቸው ማረም ይችላሉ ወይስ የኛን ጣልቃ መግባት ይፈልጋል?
4.በሰዓቱ ምላሽ ለመስጠት የተረጋጋ ስሜት ላይ ኖት ወይስ ጊዜ ይፈልጋሉ?
እነዚህን ጥያቄዎች ቆም ብለን ማሰባችን ለድርጊቱ የምንሰጠው ምላሽ ተገቢ እንዲሆንና ልጆቹን ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ለማድረግ ያግዘናል።
https://t.me/bezretulkheyr


ኃላፊነት የሚሰማው  አባት :-
👉ከሁሉም ቅድሚያ የተፈጠረበትን አላህን በብቸኝነት የመገዛት ዓላማ ጠንቅቆ ያውቃል
👉 ትክክለኛ አርዓያውን ለይቶ የሚያውቅና የሚከተልም ነው
لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا
ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡(33፡21)
👉 የተሰጠውን ቤተሰቡን የማስተዳደር ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣል
👉 ለቤተሰብ ስኬት መሪው ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የሚረዳና የመሪነት ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣ ነው
👉 የቤተሰቡ መከታና ጋሻም ነው።
👉በእያንዳንዱ ተግባሩ በእውቀትና በማስተዋል ለመጓዝ ጥረት ያደርጋል
👉 ንግግሩና ተግባሩ ልጆቹ ላይ ያለውን ተጽዕኖ ጠንቅቆ ያውቃልና መልካም አርዓያ ለመሆን ይጥራል
👉ለቤተሰቡ ጊዜን ይሰጣል
👉እንደ ፍጹም ወላጅ ሳይሆን ከስህተት እንደማይነጻ ማንኛውም ሰው ለስህተቱ ኃላፊነት የሚወስድናና ይቅርታንም የሚጠይቅ ነው።
👉የልጅ አባት የመሆንን ኒዕማ እንደ ትልቅ እድል ተጠቅሞ ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት ይጥራል
👉በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው የአላህ እርዳታ ካልታከለበት ከንቱ እንደሆነ ያውቃልና ሁሌም ነገራቶችን ወደ ጌታው ከማስጠጋትና እሱን ከመለመን አይዘናጋም
أَلَا كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ

https://t.me/bezretulkheyr


ሁሉም በእድሜ ነው!
ልጆቻችንን እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸውን በመቆጣጠር የጨዋታ ጊዜ እንኳን እንዳይኖራቸው ማድረግ፣እንዲፈጽሙ ምንፈልገውን ተግባር በኛ ፍጥነት እንዲያደርጉት መጠበቅ፣በነገራቶች ላይ ከእድሜያቸው በላይ እንዲፈጽሙ መጠበቅ...የመሳሰሉት ተግባራት ተዋህዶን መኖር ከጀመረ ሰነባብቷል ፤ምናልባትም የየዕለት ተግባራችን ከመሆኑ የተነሳ ስህተት መሆኑንም ልብ ላንለው እንችላለን።
ልጆቻችንን ከአቅማቸው በላይ ስናቻኩላቸው፦
👉 ለጭንቀት ተጋላጭ ይሆናሉ
👉 በእድሚያቸው ማጣጣም ያሉብንን ትውስታዎች ያልፋሉ
👉 ከወላጅ ጋር ሊኖር የሚገባ ቁርኝት እንዳይኖር ያደርጋል
📌ውድ ወላጅ! እኛ ልጅነታቸውን ሳንረዳ በኛ ልክ ፍጥነት እየጠበቅን ምናልባትም ለሚፈልጉት ነገር ትዕግስት ማጣታቸው ሊገርመን አይገባም!
ስለዚህ ልጆችን በልጅነታቸው ልክ ዝቅ ብሎ መረዳትና በተግባራቸው ውስጥ ትዕግስት ልንላበስ ይገባል፤አላህ ያግዘን

https://t.me/bezretulkheyr


ከመፍረድ መረዳት፤ከመታገል በጥበብ መያዝ!
ጉርምስና እድሜ ላይ የደረሱ ልጆች ቅሬታ፦ ቤተሰብ አይረዳንም፣የራሳቸውን ስሜት ብቻ ነው የሚያዳምጡት...
የወላጆቻቸው ስጋት፦ ባህሪያቸው ከባድ ነው፣ለጓደኛ የሚሰጡት ቦታ፣የሚባሉትን አይሰሙም፣የተጋረጠባቸው ፈተና ብዛት...
👉 ወላጅነት የውድድር ሜዳ አይደለም ልጆች ከአላህ የተሰጡን ኃላፊነቶች ናቸውና ቅናቻውን መንገድ ይመሩ ዘንድ የአቅማችንን ጥረት የምናደርግበት እንጂ የበላይነታችንን የምናሳይበት ስልጣን አይደለም።
👉እዚህ እድሜ ላይ በአብዛኛው ጎልቶ የሚታየው ወላጅም ኑ ወደ እኔ ፤ ልጅም ኑ ወደኔ አይነት መልዕክት ያለው በአጠቃላይ ገመድ ጉተታ የሚመስል ሁኔታ ነው።
ውድ ወላጅ! በየትኛውም እድሜ ያሉ ልጆችን ለማሳደግ ዋነኛ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ልጆችን የመረዳት ጥበብ ነው፤ የእድሜ ነገር ሆኖ ያሉበት ተጨባጭ እየገባቸው አይደለምና ካለእድሜያቸው ወደኛ ከመጎተት ይልቅ ወደ እነሱ ዝቅ ብለን ፍርጃ ባልተቀላቀለበት ቀረቤታ ከጎናቸው በመሆን መንገድ እንዳይስቱ በጥበብ ይዘን ልናግዛቸው እንጂ ይበልጥ እልህ ውስጥ እየከተትን ወደማይሆን አቅጣጫ ለመብዘንበላቸው ምክንያት ልንሆን አይገባም!
ከምንም በላይ ለእያንዳንዱ ጉዞዋችን ስንቅ የሚሆነን ወደ አላህ ማስጠጋቱ ነውና በዱዓ እንበርታ!

يُؤْتِي الْحِكْمَةَ مَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ الْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِيَ خَيْرًا كَثِيرًا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ

ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚስሰጥ ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡(2፡269)

https://t.me/bezretulkheyr


ለመመዝገብ @Bezretulkheyrterbiya ያናግሩን።


በቀን ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ልጆችዎን በአሉታዊ ቅጥል ስም ይጠሯቸዋል?
ደርቅ፣ቀጮ፣ባሪች፣ድንች፣ልበ ቢስ፣አሮጊቴ፣ሼባው፣ሰነፍ፣ፈዛዛና የመሳሰሉትን አይነት ቃላቶች ለልጆቻችን መጠቀም የተለመደና ምናልባትም ከመላመዳችን የተነሳ እየተጠቀምነው እንዳለን በራሱ ላናስተውለው እንችላለን።
ተጽዕኖው፦
👉 የሰጠናቸው ስያሜ ከባህሪ ጋር ከተቆራኘ እየተባባሰ ይሄዳል
👉 የማንነታቸው አካል ሊያደርጉትና ለራሳቸው ዝቅተኛ አመለካከት እንዲኖራቸው ያደርጋል
👉 አዲስ ነገር መሞከር የሚፈሩና ያለመቻል ስሜት ሊሰማቸውም ይችላል
👉 ትክክለኛ አቅማቸውን የማያውቁና የራሳቸውን ማንነት ያልተረዱም ሊሆኑ ይችላሉ
👉 የሰው ልጅ ሚያውቀውን ነውና የሚያደርገው ሌሎችን ተቺና ተሳዳቢም ሊሆኑ ይችላሉ
አስተውሉ! የልጆችዎን ባህሪና ማንነታቸውን መለየት ይልመዱ፤ልጆችዎ ስህተታቸውን አይደሉምና አሉታዊ ስያሜ በመስጠት ስህተታቸው የነሱ መገለጫ ከማድረግ ይልቅ ባህሪውን ማስተካከል ላይ ያተኩሩ!

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡(49:11)

https://t.me/bezretulkheyr



432 2 11 4 13

ስነ ምግባር በተግባር!
የሰውን እቃ ሳያስፈቅዱ መንካት፣የሰውን መብት አለማክበር፣ድንበር አለመጠበቅና የመሳሰሉትን ባህሪዎችን "ወይ የዘንድሮ ልጅ" ብሎ ከመፍረድ ባሻገር ምናልባት የኛ አስተዋጽዖ ሊኖረው ይችላልና ቆም ብሎ እራስን መገምገም አንዱ መፍትሔ ነው!
👉ልጆች የሌላውን ድንበር እንዲያከብሩ ከልጅነታቸው ጀምሮ በእድሜያው ልክና አግባብ በሆነ መልኩ ልናስተምራቸውና የነሱንም መብት ልንጠብቅላቸው ይገባል። ለምሳሌ ክፍላቸው ስንገባና የራሳቸው ብለን የሰጠናቸው ንብረት ላይ ክብርን ማሳየት ያስፈልጋል።(መከታተላችንና የመምራት ኃላፊነታችን እንደተጠበቀ ነው)

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ
كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?
የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡(ሱረቱ ሰፍ 2-3)

https://t.me/bezretulkheyr


ማስታወሻ
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَاتَّبَعَتْهُمْ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَانٍ أَلْحَقْنَا
بِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَمَا أَلَتْنَاهُم مِّنْ عَمَلِهِم مِّن شَيْءٍ ۚ كُلُّ امْرِئٍ بِمَا كَسَبَ رَهِينٌ

እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡(ሱረቱ ጡር፡21)
https://t.me/bezretulkheyr


ልጆት ሲያለቅስ በጣም ይረብሻል፣ሱቅ ይዘውት ቢሄዱ ያስቸግራል፣የሚፈልገው ነገር ካልተሰጠው መሬት ላይ ፍርፍር ብሎ ያለቅሳል፣ሲናደድ እራሱን ይቧጭራል፣ሰው ላይ ይታፋል፣ይናከሳል... ማለት ሁሉ ነገረ አከተመለት ማለት አይደለም!
👉 በልጅነት እድሜ ስሜትን የመግዛት ክህሎት አይዳብርም፣አዕምሯቸው ገና እድገት ላይ ነው፣ይህ በወላጅነት ጉዞ ላይ ከሚገጥሙ አንዱ ተግዳሮት እንጂ እርሶ ላይ ብቻ የተከሰተ አይደለም...
እናም ውድ ወላጅ ይህን እውነት ከመቀበል ጋር ልጅዎ እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሲሆን የሚሰጡት ምላሽ ወሳኝ ነው!
እንደወላጅ ምላሻችን ምን ይሁን?
🔸 በጩኸት፣በዱላ፣በግብግብ በሃሪው ይበልጥ እንዲባባስ ያደርጋልና በመረጋጋት ይጀምሩ
🔸 ልጆቹን መረዳት፣በተቻለ አቅም በማቀፍና በቁመት ዝቅ ብሎ በማናገር ሃሳብ መግለጽ ማለማመድ
🔸ልጆቹን አሉታዊ ስያሜ ከመስጠት አልፎተርፎም ቤተሰብ ውስጥ በአስቸጋሪነት መነጋገሪያ ከማድረግ ይቆጠቡ(አስቸጋሪ፣ባለጌ፣ሰነፍ...)
🔸 ቅድሚያ የራሶትን ስሜት የሚገዙበትን መንገድ በመግራት ጥሩ አርዓያ ይሁኑ
🔸ሁሌም በዱዓ ከመታገዝ አይዘናጉ

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡(2:186)

https://t.me/bezretulkheyr




بسم الله الرحمن الرحيم
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
ቁርኣን
👉ቅን የሆነን ምራቻ የምናገኝበት የሕይወታችን ብርሃን
👉እያንዳንዷ የሕይወት ጥያቄ ምላሽ ሚያገኝበት
👉የጽናት መሳሪያ
👉የነፍሳችንም ይሁን የአካላችን መድሃኒት
👉የሃሰናት መሰብሰቢያ
👉ስለራሳችን የምናስተነትንበት
👉የቀልባችንና የአዕምሯችን መረጋጊያ
ልጆቻችንን ከቁርአን ጋር
አብዛኞቻችን ልጆቻችንን ከልጅነት ጀምሮ በተለያየ መንገድ ቁርኣን እንዲቀሩ እናደርጋለን፤ልጆች ከትዕዛዝ ይልቅ ይበልጥ በተግባር ይማራሉ።በአሁኑ ወቅት በልጅነታቸው ቁርኣንን ሲቀሩ የነበሩ ልጆች አደግ ሲሉ መተውና ከመድረሳ አካባቢ መራቅ ይስተዋላል።ይህ እሳቤ ከምን ሊመጣ ይችላል?ልጆች ትልቅ ሰው ይቀራል እንዴ? የሚል እሳቤን ከየት አመጡት? ጥያቄው ወደ እያንዳንዳችን ይመለሳል፤ እኛ ከቁርአን ጋር ያለን ቁርኝንት ለልጆቻችን ተርቢያን ይዞ ለማደግ ወሳኝ መሰረት ነው።
ውድ ወላጅ ቁርኣንን በመማማር፣በመቅራት፣በማዳመጥ፣በመኖር... ለልጆቻችን መልካም አርዓያ እንሁን!


وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِم مِّنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰؤُلَاءِ ۚ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ تِبْيَانًا لِّكُلِّ شَيْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በእነሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ (ሕዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን (አስታውስ)፡፡ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡(ሱረቱ ነህል፡89)
https://t.me/bezretulkheyr


ከወላጅ አንደበት
ለሁለት ሴት ልጆች እናት የቀረበ ጥያቄ
(11ዓመትና 13ዓመት)
ጥያቄ፦"ከልጅ አስተዳደግ ጋር ቀደም ብሎ ቢገባኝ ጥሩ ነበር ምትይው ነገር ካለ?"
መልስ፦"ብዙ ነው"
ጥያቄ፦"አንዱን ብታጋሪን?"
መልስ፦"እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸውን እየተከታተሉ ማስተካከል"
ጥያቄ፦"ምን ዋጋ አስከፍሎኛል ብለሽ ታስቢያለሽ?"
መልስ፦"ነገራቶች ለምን እንደሚደረጉና እንደማይደረጉ ሳይሆን የተማሩት ሁሉንም ድርጊት ከኔጋ እንዲያያይዙት ነው ያደረጋቸው፤ ባጭሩ ከኔ ጋር ድብብቆሽ ውስጥ እንዲገቡ ነው የሆነው"...
https://t.me/bezretulkheyr


▫ከአላህ ጋር ያሎት ግንኙነት እንዴት ነው?
▫የዲን እውቀት ለመጨመር ምን ያህል ጥረት እያደረጉ ነው?
▫ ጭንቀት፣ፍርሃት እንዲሁም ንዴትን እንዴት ነው የሚያስተናግዱት?
▫ ሲሳሳቱ ለተግባሮት ሃላፊነት የመውሰድና ይቅርታ የመጠየቅ ልማድ አሎት?
▫ ከሰዎች ጋር ያሎት መስተጋብር እንዴት ነው?
▫ የሕይወት ውጣ ውረድን እንዴት እያስተናገዱት ነው?
▫ እራሶትን እንዴት ነው የሚንከባከቡት?
▫ የሚገጥሞትን ችግር እንዴት ነው የሚፈቱት?
▫ ሰዎችን ያዳምጣሉ?...
👉ልጆቻችን ከምናስተምራቸውና ከምንመክራቸው ነገሮች በተጨማሪ እነዚህም ነገራቶች ለሚገነቡት ማንነት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉና እራሳችንን በመገምገም መልካም አርዓያ ለመሆን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል!
https://t.me/bezretulkheyr


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ የበዝረቱል ኸይር ቤተሰቦች ቀደም ሲል ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት በዛሬው ዕለት ሊጀመር የነበረው  ስልጠና ለቀጣይ ሰኞ ጥር 05/2017ዓ.ል መዘዋወሩን እያሳወቅን  ለ1 ወር  ታቅዶ የነበረው ስልጠና ለ1ወር ከሳምንት መራዘሙን እንገልጻለን።




ከእናትነት ጋር ያለ የጥፋተኝነት ስሜት እንዴት ልቋቋም?
🔸እራስን መውቀስ ለቀጣይ እርምጃችን መማሪያ ሊሆነን እንጂ ይባስ ለጭንቀት ሊዳርገንና ለሚገጥመን ተግዳሮቶች መፍትሄ ለመውሰድ እንቅፋት ሊሆንብን አይገባም
🔸ከምንም በፊት ሁሌም በአላህ ውሳኔ ላይ ያለሽን እምነት አጠንክሪ የሰው ልጅ ሰበብ ከማድረስ ውጪ ስልጣን እንደሌለው አትዘንጊ
🔸የሰው ፍጹም የለውም! የአቅምን ከመሞከር በዘለለ ከእያንዳንዱ እርምጃሽ ጋር ፍጹምንነትን አትጠብቂ
🔸ስህተትሽን ማመን፣ማረም እንዲሁም ትምህርት መውሰድ ልማድሽ አድርጊ
🔸 ለድርጊቶችሽ ሃላፊነትን መውሰድ ተለማመጂ ልጆች ቢሆኑ እንኳ ይቅርታ መጠየቅ ካለብሽ ወደ ኋላ አትበይ
🔸 ብቻሽን አይደለሽም ተግዳሮቱ ሊለያይ ቢችል እንጂ ሁሏም እናት በከፍታና ዝቅታ ውስጥ እያለፈች ነው
👉 እናም ውድ እናት በሚገጥምሽ ተግዳሮት በሰብር እንዲሁም ወደ አላህ በመጣራት ታገዢ

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡(ሱረቱል በቀራ: 153)
    


وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

https://t.me/bezretulkheyr


ስለስልጠናው የአብዛኞቻችሁ ጥያቄ
📌መቼ ነው የሚጀመረው?
    👉ሰኞ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ል
📌ማንኛውም እናት መሳተፍ ትችላለች?
    👉አዎ ትችላለች
📌ትምህርቱ እንዴት ነው የሚሰጠው?
    👉 ምዝገባውን ካጠናቀቃችሁ ቡሃላ በሚላክላችሁ ሊንክ ቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል ኢንሻአላህ
📌ስልጠናው ለምን ያህል ጊዜ ይሰጣል?
    👉 ለአንድ ወር በሳምንት ሁለት ጊዜ

በስልጠናው፦
✅ ወላጅነት ምን ይፈልጋል?
✅ ወላጅነት ጉዞ ላይ ምንከተለው መርህ ምንድነው?
✅ እንዴት ስሜቴን በአግባቡ የምቆጣጠር እናት እሆናለው?
✅ ልጆቼን እንዴት ነው መቅጣት ያለብኝ?
✅  ከልጆቼ ጋር መልካም የሆነ መግባባትን እንዴት ልፍጠር?
✅ ልጆቼን በየእድሜ ደረጃቸው እንዴት ልረዳቸው?
እና ሌሎችም ጥያቄዎት የሚመለሱበት ስልጠና ይሆናል። ኢንሻአላህ
ለመመዝገብ በ0913993130 ወይም @Bezretulkheyrterbiya ያናግሩን።


https://t.me/bezretulkheyr


አላህﷻ ማውሳት፦
✔️ ሸይጣንን ያርቃል
✔️ከልብ ላይ ጭንቀትን አስወግዶ ሰላምና ደስታን ያጎናጽፋል
✔️ አላህﷻ ያስደስታል
✔️ ወንጀልን ያብሳል
✔️ አላህﷻ እሱን ከሚያስታውሱ ጋር ነው
✔️ ወደ አላህﷻ መቃረቢያ መንገድ ነው
✔️ ልብን ሕያው አድራጊ ነው
"አላህን ማስታወስ ለልብ፤ለአሳ ውሃ እንደማለት ነው። አሳ ከውሃ ቢወጣ ምን ይሆናል?" ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁላህ
✔️በአላህ መታወስን ያድላል
فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ
አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡(ሱረቱል በቀራ: 152)
👉ውድ ወላጅ ለልጆቻችን ከምናወርሰው ነገር አንዱ አላህ የሚታወስበትን ቤት መገንባት ነው። የሕይወት ማቅለያ፣የስኬት መሰረት እንዲሁም የሰላማችን ምንጭ ነውና ቤታችንን ሕያው ቤት ለማድረግ አላህ ያግዘን!
عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَثَلُ الْبَيْتِ الَّذِي يُذْكَرُ اللَّهُ فِيهِ وَالْبَيْتِ الَّذِي لاَ يُذْكَرُ اللَّهُ فِيهِ مَثَلُ الْحَىِّ وَالْمَيِّتِ ‏"‏ 
ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦"አላህ የሚታወስበትና የማይታወስበት ቤት ምሳሌው ልክ እንደ ሕያውና የሞተ ነው።"

https://t.me/bezretulkheyr


Online የእናቶች ስልጠና ስለልጅ አስተዳደግ ለአንድ ወር
📌 የሚሰጥባቸው ቀናት፡ ሰኞና ሃሙስ
📌 የሚሰጥበት ሰዓት፡ ከቀኑ 8፡00-9፡30(በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር)
👉ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለመመዝገብ በ0913993130 ወይም @Bezretulkheyrterbiya ያናግሩን።

741 0 14 2 13
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.