jelalu bin husseyn


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


👆👆👆👆



ልብህን በአላህ ቃል አሳርፍ

"ልብህን ከቁርአን አርቀሀት በጭራሽ ሂወት ሊኖራት አይችልም ።"



@bin_Husseynfurii




السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

✍ውድ የቻናላችን ባለቤቶች ሆይ🍀

📢 በቅርብ ቀን በወንድም ጀላሉ ሁሰይን(አቡ ዚክራ) በሰልሰቢል መስጂድ ረቡእ እና ሀሙስ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ለጀማሪዎች በሚመጥን መልኩ እየተሰጠ ያለው

👉 የኡሱሉ ሰላሳ ኪታብ ትምህርት።‼️

እንዲሁም በኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ በተለምዶ (መሀመድ አወል ረጃ)መስጂድ እሁድ ከ5 አስከ 6 ሰአት ድረስ እየተሰጠ ያለው

👉አተጅዊዱል ሙሰወር ኪታብ ትምህርት

👉እንዲሁም ልባችን እምናሳርፍበት የቂረአት መቅጠኦች

እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ ፅሁፎች በዚሁ ግሩፕ የምንለቅ መሆኑ በታላቅ ደስታ ነው ።‼️

🌲ስለዚህ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመዶ ብታካፍሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ 👌

🌷👉ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪውን ያህል ምንዳ ያገኛል🍀


@bin_Husseynfurii


ሀሰኑል በስሪ እንዲህ ይላሉ


👉አንድ ባርያ ምኞቱን አያረዝምም

ስራውን ቢያበላሽ እንጂ።‼


" كم من دمعة مسحها القرآن ؟ وكم من جرح ضمده القرآن ؟ وكم من روح آنس وحشتها القرآن "
فأهل القرآن في نعمة عظيمة لا يستشعرها سواهم ؟!

اللهم اجعلنا من أهل القرآن يارب 📖


👉እያንዳንዱ ግለሰብ ዘንድ 2 ታሪኮች አሉ አንዱ እየኖረ ያለው ሂወቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሊኖር የሚመኘው ነው።‼


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
እራስን መመልከት
~~~~~~
እየውልህ ወንድሜ! ህሊና አልባ በድን ማሽን አትሁን። የምትገባው ከራስህ እንጂ ከኡስታዝህ ቀብር አይደለም። ሲራጥን የምትሻገረው በራስህ ስራ መጠን እንጂ ኡስታዝህ እጅህን ይዞ አያሻግርህም። ያለ አስተርጓሚ ራቁትህን ከጌታህ ፊት ለምርመራ ስትቆምም ኡስታዝህ ከጎንህ አይቆምልህም። ይህንን ሁሉ የምልህ ማንንም በጭፍን እንዳትከተል ነው። በአሁኑ ሰዓት በየሰፈሩ ያሉ ሸይኾችና ኡስታዞች አብይ መታወቂያ ጭፍንነትን ሥራዬ ብለው የሚግቱ፣ ተማሪዎቻቸውን በጭፍንነት የሚኮተኩቱ መሆናቸው ነው። የወደዱትን በጭፍን እንድትወድላቸው፣ የጠሉትን በጭፍን እንትጠላላቸው እስከ ደም ጠብታ ይታገሉሃል። ቁርኣን፣ ሐዲሥ፣ የዑለማእ ንግግር ተንኮለኛ በሆነ መልኩ ከአውድ ውጭ እያገናኙ የሃሳብ ሽብር ይነዙብሃል። እዚህ ላይ "ለምሳሌ እነ እንትናን ብንወስድ… " ብዬ ባጣቅስ የእነ እንትና ጭፍራ ጦር ሰብቆ ይነሳል። ከነሱ ውጭ ያለው ደግሞ በአመዛኙ ይደግፋል። እውነት ለመናገር ግን ጣት መቀሰሩ ስለሚቀለን እንጂ ይሄ በሽታ ይብዛም ይነስም በየቤቱ ይገኛል። ችግራችን ግን አይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ጥለን ከሌሎች አይን ያለን ጉድፍ ነው የምንመለከተው። የሌሎችን ጥፋት ለማጋለጥ እንረባረባለን። እሺ የራሳችንንስ ማን ያርመው? ለማነው የምንተወው? ኧረ ልባችን ፈቃጅ ተመልካች አጣ!! ድባቡ የተበከለ ሆኖ መገሳሰፅ አልቻልንም። እኛም ለራሳችን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠንም። ግን እስከመቼ?
እና ወንድሜ ከማንም ጎጠኛ ቡድን ጋር ጭፍን ተሰላፊ አትሁን። ከዑለማእ ንግግር ውስጥ ከስሜቱ ጋር በሚገጥምለት መልኩ እየመረጠ የሚያቀርብ ሰው ስታይ በችኮላ እጅ አትስጥ። የትኛውም ቡድን ጋር የተሰለፈው ሁሉ ይህንን እያደረገ ነውና የሱ ከሌሎች በምን እንደሚለይ ረጋ ብለህ መርምር። የማይነቃነቅ ነባራዊ ሐቅ፣ የአህለ ሱና ዋና መታወቂያ አስመስሎ ያቀረበልህ ጉዳይ አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ያለው አቋም እሱ ካወራህ ተቃራኒ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህና ከስሜት ነፃ ሆነህ በሚገባ ፈትሽ። ደግሞ ቆም ብለህ ታዘባቸው። ብዙዎቹ ቡድናዊነት የሰበሰባቸው አካላት
— "እነ እከሌ ጠርዘኞች ናቸው፣ ድንበር አላፊዎች ናቸው" እያለ ከፍ አድርጎ ያስተጋባል። የሚያስከነዱ ጠርዘኞችን ግን አቅፎ ያሽሞነሙናል። ምክንያቱም እነዚህኞቹ እሱ ሲስል የሚስሉ፣ ሲያነጥስ የሚያነጥሱ የገደል ማሚቶዎች ናቸውና።
— "እነ እከሌ ጃሂሎች ናቸው" ይልሃል። በምንም መመዘኛ ከነሱ የማይሻሉ ሰዎችን ግን በትልልቅ መድረክ ላይ ያስተዋውቃል። ምክንያቱ አቋማቸው ከአቋሙ ስለገጠመለት ብቻ ነው።
— "እነ እከሌ አቋም የሌላቸው ወላዋዮች ናቸው" ያለህ ስብስብ በየክስተቱ ባደባባይ የሚዋልሉ ሰዎችን ከጎናቸው አሰልፈው ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም መመዘኛው ርካሹ ቡድናዊ ሚዛን እንጂ ኢኽላስ አይደለምና።

ወንድሜ ሆይ! አላህን አስበህ ስለምትሰራው ነገር የማንንም ጭብጨባ አትጠብቅ። የማንም ተቃውሞም አይጠፍህ። ይልቅ ውስጥህን አዳምጥ፣ ኢኽላስህን ፈትሽ። ያለ ኢኽላስ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ነው። ልፋትህም ከንቱ ድካም። በደዕዋህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሰፊው ህዝብ ይሁን። አትዘንጋ! ዛሬም አብዛኛው ወገናችን ከተውሒድ ግንዛቤ የራቀ ነው። ሺርክ ላይ የሚማቅቀው ብዙ ነው። ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ላይ እስከ አፍንጫው የተነከረው ቀላል አይደለም። ቀዳሚው ጥረትህ የዚህን ወገንህን ሸክም ለመቀነስ ይሁን። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ ገሸሽ በማድረግ ውሃ ቀጠነ፣ ከሰል ጠቆረ ብሎ ለሚነታረክ ጀርባህን ስጠው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አረፋ ነው።
በኢኽላስ እስከሰራህ ድረስ የማንም ጫጫታ ቅስምህን አይስበረው። ሰዎች እንቅፋት ሲያበዙ አንተ ፅናትህን ጨምር። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትበል።
የሌሎችን ጩኸት ሳታጣራ የምታስተጋባ በቀቀን አትሁን። በጭፍን አትደግፍ። በጭፍን አትንቀፍ። እወቅ! እውር ጥላቻና እውር ውዴታ ነገ ከአላህ ፊት ያሳፍርሃል። ማንንም በእውር ድንብር አትከተል። ጭፍን ወገንተኝነት በቃላት ቢያሸበርቅም፣ በሱና፞ ስም ቢቀርብም የተወገዘ ነው። የአሳማ ስጋ በወርቅ ሰሀን ስለቀረበ አሳማነቱ አይቀየርም። አሳማ አሳማ ነው። የመዝሀብ ሰዎች ዘንድ የምናውቀው ጭፍን ወገንተኝነት ተቀባብቶ ተከሽኖ በሱና፞ ዑለማዎች ስም ሲቀርብ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ አንዳንዶች በየሰፈሩ በየመንደሩ እየተቧደኑ ‘ወላእ’ እና ‘በራእ’ የሚቋጥሩባቸው አካላት መመደባቸው ነው።
ደግሞም በልክ እንሁን። በሌሎች ሃገራት ወይም አካባቢዎች ያየነውን ወይም የሰማነውን ኺላፍ ሁሉ ሰበብ እየፈለጉ እየጎተቱ ማምጣት ግልብነት ነው። ወላጆችህ ወገኖችህ በሺርክ እየተጨማለቁ አንተ በሸይኽ እንትናና በሸይኽ እከሌ መካከል ስለተፈጠረው ኺላፍ ጧት ማታ እያቦካህ በአካባቢህ ያሉ ዱዓቶችን ለመፈረጅ አድፍጠህ ብትጠባበቅ የፊትና ጥማትህን እንጂ ንቃትህን አያሳይም። በአካባቢህ ይሄ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ ሳይኖርህ እንዳቅማቸው እየደከሙ ያሉ አካላትን ትንሽዬ ጥረት አይኗን ለማጥፋት ጦር ብትሰብቅ ጥሬነትህን ብቻ ነው የሚያሳየው። ወንድሜ ከቻልክ አግዝ። ክፍተት ካየህ አርም። አቅሙ ከሌለህ ባላቸው አስመክር። በምትችለው ከጎናቸው ቁም። ለሰፈርህ ለአካባቢህ የደዕዋ እንቅስቃሴ አጋዥ እንጂ አፍራሽ አትሁን። ለደዕዋ እንቅፋት በመሆን ሌሎች እንዳይለወጡ መሰናክል አትፍጠር። ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገሮችን መጣል ፀያፍ ጥፋት ነው። ወደ ኣኺራ በሚወስደው የደዕዋ መንገድ ላይ እንቅፋት መጣል ግን እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። እንዲህ አይነቱን የወንጀል ሸክም የምትቋቋምበት ጫንቃው የለህምና ዛሬውኑ ሚናህን ለይ። ዛሬውኑ ለደዕዋ ያለህን አስተዋፅኦ ገምግም።
………………………………………………
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
https://t.me/IbnuMunewor


أَهْــ الْقُرْآنِ وَخَاصَّتُه ــلُ💎 dan repost
📙🍂📙🍂📙🍂📙🍂


سُنَنْ.نَبَوِيَّةٍ.مَهجُورَة.tt ❪➐➋❫

❪التَورُّكُ فِي التَّشَهُّدِ الثَّانِي❫

عَنْ حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ رَضِي اللَّهُ عَنْهُ، فِي صِفَة صَلاةَ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ، و فِيهِ : ❪وَإِذَا جَلَسَ فِي الرَّكْعَةِ الْآخِرَةِ قَدَّمَ رِجْلَهُ الْيُسْرَى وَنَصَبَ الْأُخْرَى وَقَعَدَ عَلَى مَقْعَدَتِهِ❫


📚 فِي.هَذا.الْحَدِيث.tt بَيانُ صِفَةِ صَلاةِ رَسُولِ الله صَلَّىَ اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، واطمئنانِه واعتدالِه فِيهَا فيُسَنُّ أَنْ يَجْلِسَ فِي التَّشَهُّدِ الْأَوَّلِ مُفْتَرِشًا وَفِي الثَّانِي مُتَوَرِّكًا , فَإِنْ كَانَتْ الصَّلَاةُ رَكْعَتَيْنِ جَلَسَ مُتَوَرِّكًا


🖊رَواهُ : البُخَارِيِّ

📙🍂📙🍂📙🍂📙🍂

💦|سَاهم.فِي.نشر.القَناة.فَالدَّالُ.على.الخَيرِ.كَفاعِله.tt

📬 |-قَناة.أَهْلُ.الْقُرْآنِ.وَخَاصَّتُه.tt
┏━━☆━━☆━┓
💎 t.me/qurraan
https://goo.gl/Wkfm5F
┗━━☆━━☆ ━┛










#تلاوة_طيبة

آيات تذكرك بالآخرة اسمعها بقلبك


☁️🌟🌟🌟☁️

ፈገግ ይበሉ


👉ያው እንደሚታወቀው በሻፊኢይ መዝሀብ ሁሉም ኢባዳዎች ላይ ንያን በንግግር ማስገኘት ሱና ነው

💥ከአዝናኝ(አስቂኝ) የፉቀሀዎች ንግግር


አቡል ፈድል አለመህዛኒይ የሚባሉ የሻፊኢይ መዝሀብ ተከታይ ናቸው እና አባቱ በጣም ፈቂህ ነበሩ ልጅ አቡል ፈድል እንዲህ ይላል

አባቴ እኔን መምታት ሲፈልግ በምቱ ላይ ድንበር እንዳያል በፍራት እንዲህ ይል ነበር

"ልክ አላህ እንዳዘዘው አደብ እንዲይዝ ብዬ ልጄን ለመምታት ነየትኩኝ "
يقول: نويتُ أن أضربَ ولدي تأديباً كما أمر الله


እና አባቴ ንያውን ጨርሶ እስኪያሟላ ድረስ ሸሽቼ አመልጥ ነበር ይላል።

🌱البداية والنهاية (١٢/ ١٨٨)🌱

☁️🌟🌟🌟☁️




📚የቁርአን ተፍሲር

{{በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ }}

☄ሱረቱ’ናስ እና ሱረቱል ፈለቅ☄


🪧 ክፍል ሁለት 🪧



🔎 📖
https://t.me/joinchat/TlfK9EJOM_yyqggV
____🎧__________


🔊《የትዕግስት አስፈላጊነት》🔊

🔶 #የኢብኑል ቀይም ጫማ ወደ መስጂድ በገቡበት መዘረፍ…………

https://t.me/joinchat/TlfK9EJOM_yyqggV


⚡️ የቁርአን ተፍሲር ⚡️

{{በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ }}

⚡️ ሱረቱል ፋቲሃ🌙

📚 ክፍል አንድ 📚



🔎 📖
https://t.me/joinchat/TlfK9EJOM_yyqggV
________🎧__________


Ibnu Abas Quran Memorizing And Islamic Terbia Center dan repost
📌 ታላቅ የምስራች ከኢብኑ አባስ የቁርዓንና የኢስላማዊ ተርቢያ አስተምህሮት ማዕከል

መርከዙ ለ2013 የትምህርት ዘመን ዕድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴት ተማሪዎችን በቁርዓንና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

🗓 የምዝገባ ቀን፦ 1/5/2013 እስከ ቀን 7/5/2013

🕌 የምዝገባ ቦታ፦
ፉሪ ፓሊስ ክበብ የስ ውሃ ገባ ብሎ የቀድሞ የኢብኑ ዓባስ የወንዶች መርከዝ

☎️ ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር 0912941706
ወይም 0910192594 ወይም 0911008271 ይደውሉ

🚫 ማሳሰቢያ፦
👉 ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!!

🏠መርከዝ ኢብኑ አባስ የቁርዓንና ኢስላማዊ ተርቢያ ማዕከል
👉https://t.me/joinchat/TlfK9EJOM_yyqggV


አስደሳች ዜና
በኢብነ አባስ የቁርዓንና የእስላማዊ አስተምህሮት ማዕከል ውስጥ ከ2008እስከ 2012 ለተመረቃቹ ተማሪዎች እንዲሁም ለሌሎች ወንድምና እህቶች

📌ማዕከሉ በ2013 በቁርአን ሂፍዝና በኢስላማዊ ተርቢያ ከሚያሰለጥናቸው ተማሪዎች ጎንለጎል
ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ተከታታይ ሳምንታዊ የቂራኣት ኮርስ
ከማዕከሉ አቅራቢያ በሚገኘው ለመአከሉ ተማሪዎች እንደ ማሰልጠኛ በሚያገለግለን ኡመር ኢብኑ አብድልአዚዝ መስጂድ የሚከተሉት ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን እነሆ ያበስራቹኋል።


📋የተጅዊድ ትምህርት

በኡስታዝ ጅላሉ ሁሰይን
──━━✺✿✺━━──

📚መትን አቢ ሹጃዕ
በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ
──━━✺✿✺━━──

📚"ሃያእ ሊብኒ አቢ ዳውድ"

በኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን

──━━✺✿✺━━──
👉https://t.me/joinchat/TlfK9EJOM_yyqggV

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

249

obunachilar
Kanal statistikasi