የድሀ ፍቅር
ክፍል 7
በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,.
የማትሪክ ፈተና መጥቶ እኔና ሜላት ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተገናኝን
,የማትሪክ
ውጤት ቅድሚያ የኔ ወጣ ደስ የሚል ውጤት አምጥቼ አለፍኩ በጣም ደስ እለኝ
ሜላትም
ደስ አላት,የሜላትም ውጤት መጣ ሜላት ግን አላለፈችም ነበር በጣም ያሳዝናል
አዘንኩ
አብረን እንደምንቀጥል ነበር የማስበው በቃ ግን አልሆነም,
ሜላት በውጤቷ ብዙም አልተበሳጨችም ይልቅስ የኔ ማለፍ አስደስቷታል ,እኔ ግን
አዝኛለው .ውዴ አለችኝ እንደከፋኝ አውቃ ወዬ አልኳት,አየህ የእኔ መውደቅ አሪፍ ነው
ምንክያቱም ባልፍ እንኳን አንድ ዮኒቨርሲቲ ላይደርሰን ይችል ነበር እኔ እዚህ ከሆንኩ
ግን
ቢያንስ አንተጋ እየመጣሁ እጠይቅሀለው የፈረደበት የአባቴ ድርጅት አለ እዛ መቀጠር
እችላለው ለእናትህና ለወንድምህም እኔ ቅርብ ሆኜ እንከባከባቸዋለው አለችኝ,.
ከሜላት ያልጠበኩትን ነገር ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ይከፋታል ብዬ አስቤ ነበር
በተቃራኒው ግን አልከፋትም,.እሽ ብያት ተያይዘን እኛ ቤት ሄድን ለእናቴ የኔ ማለፍ
አስደሰታት ሜላት እንዳላለፈች ስታውቅ አዘነች ግን ሁሉም ለበጎ ነው ,እናቴ
እንደተለመደው ነጠላዋን አንጠልጥላ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደች እኔና ሜላትም ያበጠው
ይፈንዳ ብለን ተያይዘን ዘና ለማለት ሄድን ,ያን ጊዜ ግን ብር ስለነበረኝ እኔ ልክፍል
አልኩ
ሜላት አልፈቀደችልኝም,.
እኔና ሜላት ስንዝናና ውለን መሽ ልንለያይ ስንል የባንክ አካወንት መክፈት እንዳለብኝና
አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል መጀመር እንዳለብኝ ነገረችኝ ከተቻለ አዲስ አበባ
ዮኒቨርሲቲ እንዳይደርስህ ፀሎት አድርግ አለችኝ ,ለምን አልኳት ,ከጏደኞቼ ጋር ዘና ልንል
ነው ብዬ ያለህበት ድረስ መምጣት እችላለው አዲስ አበባ ከደርሰህ ግን አልችልም
አለችኝ እሽ እስኪ እናያለን ፈጣሪ ያውቃል አልኳት,
ሜላትን ወደ ቤቷ ሽኝቼ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ በቃ እናቴ ደስ ብሏታል እኔም ደስ አለኝ
የእናት ደስታ ከማየት በላይ ምን ያስደስታል ምን በቃ ደስተኛ ነኝ,ምን እንደሚፈጠር
ባይታወቅም ፈጣሪ ያለው እንደሚሆን ግን አምናለው,ሜላቴን ማጣት አልፈልግም በቃ
ከልቤ እወዳታለው የመጀመረያየም የመጨረሻዬም እሷ ብቻ ናት በችግር ጊዜ እንኳን
ፊቷን
አላዞረችብኝም አብራኝ ነበረች ,.ሁሌም ሳፈቅራት እኖራለው,.
ቀኑ ደርሶ የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰኝ አወኩኝ "ደብረማርቆስ"ዮኒቨርስቲ ነበር የደረሰኝ
ለሜላት ደውዬ ነገርኳት ልቀይር ወይስ ይሁን አልኳት አይ አትቀይር አሪፍ ነው አለችኝ
እሽ
አልኳት በቃ እንገናኛለን ተባባልን,. ማድረግ የነበሩብኝን ነገሮች ሳስተካክል ዋልኩ እናቴ
በአቅሟ የምትችለውን እያደረገች ነው.,
የምዝገባ ጊዜ ሳያልፍ መመዝገብ ስለነበረብኝ ልሄድ እንደሆነ ለሜላት ነገርኳት እሷም
አብሬህ እሄዳለው አለችኝ ,እሽ ብያት እሷም ለቤተስብ ምክንያት ፈጥራ አብራኝ ሄደች
ተመዝግቤ ዞር ዞር ብለን ከተማዋን ስናይ ዋልን ደብረማርቆስ ውብ ናት ,እኔና ሜላት
ደስ
የሚል ጊዜ አብረን አሳለፍን ለመጀመርያ ጊዜ አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ
አደርን
,በህይወቴ የማልረሳው ድንቅ ቀን .እኔና ሜላት ለ ሁለት ቀን ያክል ቆይተን ወደ አዲስ
አበባ
ተመለስን .ነገ ማታ እቤት እመጣለው ብላኝ ተለያየን,...
በማግስቱ ማታ ሜላት እቤት መጣች በእጆቿ ፊስታል አንጠልጥላለች ተቀብያት ገብታ
ተቀመጠች ገና ከመቀመጧ ምንም እንዳትለኝ አለችኝ በፍረሀት ምንድነው አልኳት
ፊስታሉን ፈትታ ለቢጃማ የሚሆን ቱታ የውጪ ቲሽርት ጅንስ ሱሪ ጫማ ቦርሳ ስልክ
ሳይቀራት
ገዝታ ነበር የመጣችው ምን ልበል ምንም እንዳትል ብላ አስጠንቅቃኛለች ዝም አልኩ
አመስግናለው ከማለት ውጪ,.
ሜላት ለኔ ከምንም በላይ ነች በርትተህ ተማር እኔም እየመጣሁ እጠይቅሀለው እነ
ማዘር
ከናፈቁህ አንተም በእረፍት ጊዜ መጥተህ ታያቸዋለህ ብቻ ትኩረትህ ትምህርትህ ላይ
ይሁን አለችኝ እሽ ማሬ አልኳት.እናቴም ተባረኪ ልጄ አለቻት በርታ እሽ ልጄ አለችኝ
በስስት
እያየች የእናት እንጀት ሆኖባታል,.ወንድሜም ስማ ለኛ እንዳታስብ እሽ እኔ እንዳንተ
ጎበዝ
እሆናለው አለኝ እሽ እልኳቸው ሁላችንም እንባ ተናንቆናል,.ትንሽ አምሽተን ሜላትን
ሸኘኃት
,.የተለመደውን ግንባሯን አንገቷን ከንፈሯን ስሜ ተለየኃት,.
ዝግጅቴን አጠናቅቄ የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ስለነበር ለመሄድ ወሰንኩ ሜላትም
እናቴና
ወንድሜ ሆነው ሸኙኝ እንደምወዳቸው ነገርኳቸው ሜላቴ አፈቅርሻለው አልኳት በቃ
ቻው
ብዬ ተለየኃቸው. የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ ጉዞ ጀመርኩ የብቸኝነት ህይወት አንድ
ተብሎ
ተጀመረ ,እኔና ሜላት እንደዋወላለን ሜላቴ እዛው አባቷ መስሪያ ቤት መስራት
ጀምራለች
እኔም ትምህርቴን የመጀመርያ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሆኜ ጀምርያለው........
ይቀጥላል ...
ቶሎ እንዲቀጥል..like 👍❤️👍❤️👍❤️❤️❤️❤️
@bosbitch