በጥናት ሰአታችሁ ልብ ብትሉት 1. ለነገ ዝግጁ ሁኑ
ለነገ ዝግጁ ስትሆኑ ሰአታችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ የቤት ስራችሁን በብቃት ወይንም በጊዜው ለማጠናቀቅ ይረዳችኃል!
2. የጥናት ቡድን ፍጠሩ
ይህ ወሳኝ ነገር ነው ጉልበት ይሰጠናል የጥናት ቡድኖች በመፍጠር እውቀትን እና ልምዶችን ልንጋራ ይገባል!
3. አንድ ነገር ለመስራት መደበኛ ልምድ ይኑራችሁ!
– ከትምህርት ጋር የተገናኙ ስራዎችን ለመስራት እለታዊ የሆነ መደበኛ ጊዜ ስትመድቡ ሁሌም ቢሆን የሚሰጣችሁን የትምህርት ሀላፊነቶች እና የቤትስራዎች በአግባቡ እና በጊዜው ሰርቶ ለመጨረስ ይረዳችኃል! በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎችም ይህን ተረድተው ከአላማችሁ እንዳያሰናክሏችሁ ያግዛል።
4. ለጥናት ምቹ የሆነ ቦታ ያመቻቹ !
– ሁሌም ቢሆን የምታጠኑበት ስፍራ ምቾት ሊሰጣችሁና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳችሁ ሊሆን ይገባል! ካልሆነም ግን ሁኔታውን ትታችሁ ትኩረታችሁን ራሳችሁ ጋር የማድረግ ልምድ አዳብሩ።
5. ሁሌም ቢሆን ተጠባባቂ እቅድ ይኑራችሁ
– ብዙ ጊዜ ለትምህርት እና ለጥናት የምንገለገልባቸው መሳሪያዎች በማንጠብቃቸው ሰአቶች ሊበላሹ ብሎም ሊጠፉና ሊሰረቁ ይችላሉ! ስለዚህም በተለያየ መልኩ በማዘጋጀት በተጠባባቂነት ልንይዛቸው ይገባል!
6. የቀን መቁጠርያ አዘጋጁና ተጠቀሙ
– በሁሉም የትምህርት ተቋማትና ደረጃዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ የጥናት ስራዎች ይሰጣሉ! ታዲያ እንደ ርዝመታቸው እና እጥረታቸው ተማሪዎች በመዘናጋት ስራቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ይስተዋላል! ይህን አስወግዶ ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ከእለት ተእለት የትምህርት እና የጥናት እንቅስቃሴ ጀምሮ የረጅምና የአጭር ጊዜ ሀላፊነቶቻችንን በቀን መቁጠርያ አማካይነት እቅድ ልናወጣላቸው እና ልንተገብራቸው ይገባል!
7. የተደራጃችሁ ሁኑ
በትምህርት ቆይታችሁ የምትገለገሉባቸውን መሳሪያዎች የትምህርት ሰአት የጥናት ሰአታችሁን የመዝናኛ ሰአታችሁን እቅዳችሁን በመለየት ሁሉንም በስርአት በቦታውና በሰአቱ በመጠቀም የተደራጃችሁ ሁኑ!
8. አዎንታዊ አስተሳሰብን ያጎልብቱ !
የትምህርት ቤት ሕይወት ጠንካራ ስራን የሚፈልግና በጭንቀት ብሎም በመሰናክሎች የተሞላ ነው! እነዚህን የሚገጥሙንን ጭንቀቶችና መሰናክሎች ተቋቁመን ስኬታማ ለመሆን ከምንመኛው የምረቃ በዓላችንም ለመድረስ አዎንታዊ አስተሳሰብን ልናጎለብት ይገባል!
9. እረፍት ውሰዱ
ጥናት ከመጀመራችሁ በፊት ሆነ በጥናት መሀል አጭር የእረፍት ጊዜ መውሰድ ችግር እንደሌለው ልንረዳ ይገባል! ምክንያቱም የእረፍት ጊዜያቶች መንፈሳችሁን እንድታድሱ እና ወደጥናት ስትመለሱ ትኩረት አድርጋችሁ እንድትሰሩ ይረዳችኃል!
10. ዝርዝር የስራ እቅድ ወይንም check list ይኑራችሁ!
– ብዙን ጊዜ የምንማራቸው ትምህርቶች እለታዊ የሙከራ ስራ እና የቤት ስራዎች ይኖራቸዋል! በመሆኑም የሁሉንም የምንማራቸውን የትምህርት አይነቶች ሀላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት እቅድ ልናዘጋጅላቸው ይገባል! ይህም የስራ ሀላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት ይረዳናል!
https://t.me/alphatutorialcenter