የፍትህ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል
ቡታጅራ ህዳር 25/2017
የፍትህ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በጋራ ተዘጋጅቷል።
የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋሲካ ስርሞሎ እንዲሁም የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን ሽፋ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል። በውይይቱ የወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች ፍትህ ፣ ፖሊስ ፅ/ቤቶችና አፈጉባኤዎች ፣ የዞን ፀጥታ ፣ ማረምያ ተቋም ፣ ዞን ፖሊስና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። በውይይቱ ከፍትህና ከዳኝነት ተግባራት ጋር ተያይዞ ሊሻሻሉና ሊፈቱ የሚገቡ ጉዳዮች በስፋት ተነስተው በየደረጃው ከተውጣጡ አካላት ጋር በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋሲካ ስርሞሎ ማህበረሰቡ በፍትህ ተቋማት ላይ ያለው አመኔታ ለመጨመር የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ ሁሴን ሽፋ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ዋና ተግባር እንደሆነ አንስተው በፍ/ቤቶች ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ተከታትሎ እርምጃ እንደሚወሰድም አንስተዋል፡፡
በውይይቱ መድረኩን ያጠቃለሉት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው ውይይቱ እስከ ታች መውረድ እንዳለበት አንስተው ፣ ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ፣ አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርአት ባህላዊ ዳኝነትን በማጠናከር የፍርድ ቤቶችን ጫና መቀነስ እንደሚገባና በቀጣይ ምን ለውጥ መጣ የሚለውን እየተገመገመ መሄድ እንዳለበት ፣ ህዝብ ከፍትህ ተቋማት ብዙ እንደሚጠብቅ አውቀን በቅንጅት በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚጠበቅም አንፅንኦት ሰጥተው አንስተው በውይይቱ መጠናቀቂያ ላይ ፍትህ መምሪያ ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ ሰላምና ፀጥታና ማረምያ ተቋም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው ውይይቱ ተጠናቋል።
https://www.facebook.com/61552754727232/posts/pfbid02icgkr1UccLoLX8GsQtkYSgQ7X6FCqtHRcgZ4j5N2fi8pzpdVmYK5CYHzefwB7CJPl/