ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ አስገዳጅ ህግ እንደሚቆጠር ግልፅ ነው። ነገር ግን በቅድሚያ የሚደረገው የውል ስምምነት ከህግና ከሞራል የሚፃረር መሆን የለበትም። በዚሁ መሰረት ከውል ጋር በተያያዘ ተዋዋይ የሆነ ወገን ውሉን የፈፀምኩት ተገድጄና ከፍላጐቴ ውጭ ነው በሚል የሚያደርገውን ክርክር ዳኞች (ፍ/ቤቶች) የዚህን ተዋዋይ ወገን እድሜ፣ ጾታ፣ የተዋዋይ ወገኖችን ልዩ ግንኙነት እና አጠቃላይ ተያያዥነት ያላቸው አኳኋኖች ጭምር መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1706/1/,1678/ሀ/,1809 ድንጋጌዎች መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 12 ላይ አስገዳጅ ወሳኔ ሰጥቶበታል።