Admas News


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከርእስ ውጪ

ሴቶችዬ ተጠንቀቁ ተብላቹሃል 🥶🫣

Credit - ስምኦን ደረጄ


የቃሊቲ እስረኞች ወደ ሌላ ወህኒ ቤት ሊዛወሩ ነው::

የቃሊቲ ወህኒ ቤት እሥረኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሌላ እሥር ቤት እንደሚዛወሩ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታወቀ፥እስረኞቹን ገላን አካባቢ ወደ ተሰራው ማረሚያ ቤት የማዛወሩ ሥራ እስከ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም እስኪጠናቀቅ ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደማይችልም አስታውቋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እስረኞቹ የሚዛወሩበትን ምክንያት እና የቤተብ ጥየቃ የሚመለስበትንም ቀን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከመጪው ሰኞ ታህሳስ 14/2017 ጀምሮ መደበኛው አገልግሎት እንደሚቀጥል እና ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደሚችልም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
(ሲሳይ አጌና)


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሆስፒታል ገብታለች!

ከኩላሊት ጋር በተያያዘ ሰሞንኛ መነጋገሪያ የሆነችው ሩሃማ መር*ዝ ጠጥታ ሆስፒታል መግባቷ ተሰምቷል። መርዙ*ን ከመጠጣቷ በፊት "የኢትዮጵያ ሕዝብ ፀልዩልኝ እናቴን አደራ" በማለት መልዕክት ማስተላለፏ ነው የተሰማው።


29ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የመውጫው ቀን እየተቃረበ ነው፣ አሁኑኑ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌ ብር በ10 ብር የ4 ሚሊዮን ብር እና የሌሎችም ዕድሎች አሸናፊ ይሁኑ
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


💥PAWS Big Airdrop created by Blum CEO💥

በዚህ ሊንክ ግቡ https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=5SJ5KTgY

➝Start በሉ
➝ታስኮችን ስሩ
➝ጓደኞቻችሁን invite አድርጉ

ይህ ፕሮጀክት በ BLUM CEO(መስራች)ና developers ነው የተሰራ ስለዚህ በደንብ ስሩት።
ተጨማሪ መረጃ ሲወጣ እናሳውቃችኋለን እስገዛው start ብላችሁ early user ሁኑ✅


ይህ መልዕክት እንደደረስዎት ወዲያውኑ እድልዎን ይሞክሩ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር በመቁረጥ የ4 ሚሊዮን ብር እና የሌሎችም ዕድሎች አሸናፊ ይሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለተጫበማሪ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ


Admas lottery dan repost
አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 28ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል


እናስታውስዎ አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 28 ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት፡፡የአሁን ሙከራዎ እድለኛ ልታደርጎት ትችላለች፡፡ 605 ላይ A ብሎ በመላክ ወይም በቴሌብር በ10 ብር ይቁረጡ፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


የይቅርታና ምኅረት ቦርድ 257 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲወጡ የውሳኔ ሐሳብ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የይቅርታና ምኅረት ቦርድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ዐቃቤ ሕግ ወይኒ ገብረሚካኤል በሰጡት ማብራሪያ÷ ከይቅርታና አመክሮ አፈፃፀም ጋር በተያያዘና የይቅርታ ቦርዱ የውሳኔ ሐሳብ የመስጠትና የማፀደቅ ሥራን አስመልክተው የተከናወኑ ተግባራትን አብራርተዋል፡፡

በሰጡት ማብራሪያም ቦርዱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ከክልል ፍትሕ ቢሮዎች ወይም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጎች የቀረቡ የይቅርታ ጥያቄ የውሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸውን 402 የፌዴራል ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ መመርመሩን ገልጸዋል፡፡

ከምርመራው በኋላም 257 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲወጡ የውሳኔ ሐሳብ በማሳለፍ በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ፀድቆ ተፈፃሚ ሆኗል ማለታቸውን የፍትሕ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም ቦርዱ የ89 ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን እና 51 ታራሚዎች ደግሞ በቦርዱ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የመርካቶው የእሳት አደጋ አሁናዊ ሁኔታ ከቦታው


🔈#መርካቶ

" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንድ ሰው በዚህ የከፋ ጊዜ አብሮ ተጋግዞ እሳቱን ማጥፋት ሲገባው የራሱ ያልሆነን ንብረት ለመዝረፍ ሲሯሯጥ ማየት እጅግ ያሳዝናል።

ሌላው በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተከታይ ለማፍራት ሲባል ያልተባለውን በማለት፣ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ' ላይክ ፣ ሼር ፣ ፎሎው ' አድርጉን እያሉ በዚህ የችግር ወቅት ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን መመልከቴ አሳስዝኖኛል።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (መርካቶ)


#FireAlert 🔥

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።


" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል

በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ " የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " በማለት የቤተሰብ አባሏ ገልጸዋል።

የአካባቢው አቃቤ ሕግ በበኩላቸው ግርፋቱን መፈጸማቸው የተጠረጠሩ ባለቤቷን ጨምሮ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ መካሄዱን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ጃርሶ ቡሌ (ዘመዷ) ምን አሉ ?

" ኩሹ ቦናያ የ3 ልጆች እናት ናት።

ገበያ ላይ አስሮ የመግረፉ ድርጊት የተፈጸመው ባለፈው ወር መስከረም 9/ 2017 ዓ.ም. ነው።

ግርፋቱ የተፈጸመባት ባለቤቷ ገልገሎ ዋሪዮ ይባላል።

ኩሹ እና ባለቤቷ ገልገሎ በትዳር 12 ዓመት ቆይተዋል

በኑሯቸው ችግር ውስጥ ሲወድቁ ባለቤቷ ወደ ውትድርና ይገባል። በውትድርና 4 ዓመት ያህል ቆይቷል።

እሷ ልጆቿን ለማሳደግ ብቻዋን ስትጥር ነው የቆየችው።

ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ግን ባለቤቱን መደብደብ ይጀምራል።

በተደጋጋሚ ወደ ቤተሰቦቿ እየሸሸችም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ወደ ቤቷ ትመለስ ነበር።

ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ከባለቤቱ ጋር መስማማት አለመቻሉም ፤ ዘወትር ባለቤቱን እና ልጆቹን ይደበድብ ነበር።

በአገር ባህል መሰረት ሽማግሌዎች በባለትዳሮቹ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በተደጋጋሚ ለሽምግልና ተቀምጠዋል።

ችግሮች ሳይፈቱ ሲቀሩ ወደ አባቷ ቤተሰብ ሸሸች። ሽማግሌዎች ተነጋግረው ባለቤቷ ጠባዩን እንዲያሻሽል እርሷም ወደ ቤቷ እንድትመለስ መከሯት።

እርሷ ግን ነገሩን በደንብ እንዲያጤኑት ወደ ቤቷ ብትመለስ አንደሚገላት’ ተናገረች።

የሽማግሌዎቹን ቃል አላከበረችም በሚል ሽማግሌዎቹ ታስራ እንድትገረፍ ወስነውባታል።

የሽማግሌዎቹ ውሳኔ የቦረናን ባሕል አይወክልም ፤ ይህ የጥቂት ሰዎች ውሳኔ ነው።

በሚኖሩበት አካባቢ ባለ ዛፍ ላይ አሰሯት። ይህንን ያደረጉት ልጇ እያለቀሰ፣ ሌሎች ቆመው እያዩ ነው።

በስፍራው ተገኝተው የነበሩ በሙሉ ፎቶ እንዳያነሱ፣ ቪድዮ እንዳይቀርጹ ተከልክለው ነበር።

ስትገረፍ ከዋጪሌ ዱብሉቅ አንድ መኪና በድንገት መጣ።

አንድ ልጅ ከመኪናው ወርዶ ቪድዮ መቅረጽ ጀመረ ፤ በዚህም የተፈጸመውን ወንጀል ሌሎች ሊያዩት ይችለዋል።

የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ኩሹ በዛፍ ላይ ታስራ በባለቤቷ ግርፋት ከደረሰባት በኋላ ክፉኛ ተጎድታለች።

የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል።

የቤተሰብ አባላቶቿ የደረሰባትን ወድያውኑ አልሰሙም ነበር። ለሳምንት ያህል ሕክምና ሳታገኝ ቆይታለች።

ወንጀሉ አንደተፈጸመ ወድያውኑ ቪድዮው አልተለቀቀም ነበር። ከሳምንት በኋላ ነው ሰው ያየው። ወላጆቿም የሆነውን ያዩት ከቪድዮው ላይ ነው።

መጀመርያ በአሬሮ ሆስፒታል በኋላም ወደ ያቤሎ ሆስፒታል ሄዳ ሕክምና የተከታተለች ቢሆንም የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ ሐዋሳ ሆስፒታል ተልካለች። "


የዋጪሌ ወረዳ አቃቤ ሕግ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጉዮ አሬሮ ጥቃቱ በቃቃሎ መንደር መፈጸሙን እና ከተፈጸመ ከሳምንት በኋላ ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።

" መረጃው እንደደረሰን የምርመራ ቡድን በማዋቀር መረጃ መሰብሰብ ጀምረናል " ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ሽማግሌዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ተናግረዋል።

" ክስ ለመመስረት የሕክምና ማስረጃ እንፈልጋለን። አሁንም የሕክምና ክትትል እያደረገች በመሆኑ መረጃው ገና ተጠናክሮ አልቀረበልንም። ሕጋዊው ጉዳይ ግን ሂደቱን ጠብቆ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ


“ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ” - ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጂ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ሩት ማርሻ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየች ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በፊት አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ተማሪዋን፣ “ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ” ከማለት ውጪ ስለአሟሟቷ የጠቀሰው ግልጽ ማብራሪያ የለም።

ይህ በእንዲህ እያለ “ ተማሪዋ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በመጣላቷ ከፎቆ ተወርውራ ነው የተገደለችው ” የሚሉ ወሬዎች እየተዘዋወሩ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሰራጫችሁት ፅሑፍ ተማሪዋ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፈች ከመግለጽ ውጪ ስለአሟሟቷ አያብራራም፤ በሌላ ወገን ደግሞ ተማሪዋ የሞተችው “ ከፎቅ ተወርውራ ” እንደሆነ እየተገገረ ነው፣ እውነታው ምንድን ነው ? ሲል ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል።

ከዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ምላሽ የሰጡን አቶ ማቲዎስ ጪናሾ፣ “ በፃፍነው ላይ ድንገት ሕይወቷ አለፈ ነው የሚለው። አሁን ደግሞ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ያለው ” ብለዋል።

“ እርሷ ጋር የነበረ ልጅም አለና ከእርሱ ኢንቬስቲጌት እያደረጉ ስለሆነ መረጃውን ፓሊስ ይፋ ሲያደርግ እኛም ይፋ እናደርጋለን ብለን ነው እየጠበቅን ያለነው ” ነው ያሉት።

እስካሁን የተገኘ ፍንጭ አለ ? ከፎቅ ተወርውራ ስለመገደሏ አመላካች ጉዳዮች፤ የአሟሟቷ ሂደት እንዴት ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ ፣ “ የአሟሟት ሂደቱን እኛ አሁን ይሄ ነው ብለን መናገር አንችልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ምክንያቱም ጉዳዩን የያዘው ፓሊስ ነው። የሞቷ ምክንያት ይሄ ነው ብሎ ይፋ ሲያደርግ ነው ይፋ ማድረግ የምንችለውና አሁን እኛም የተረዳነው ነገር የለም ” ሲሉም አክለዋል።

“ ዝም ብለው ወሬዎቹ አሉ። ወሬዎቹ የተለያዩ ናቸው” ያሉት አቶ ማቲዎስ፣ “ ‘ከ4ኛና 5ኛ ፎቅ ወድቃም’ ይባላል፤ ‘ሰው አንቋትም’ ይባላል፤ የተለያዬ ወሬ ነው ያለውና ያንን አሁን እንደ ምክንያት አንቀበልም። መቀበል የምንችለው የተጣራ መረጃ ሲገኝ ነው ” ብለዋል።

አደጋው የደረሰው ከቀናት በፊት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ፣ አስከሬኑ አዲስ አበባ ወደሚመለከተው ሆስፒታል ሌሊት ተወስዶ፣ በማግስቱ ሀዋሳ ከቤተሰብ እንደደረሰ፣ ቤተሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደፈጸመ፣ ዩኒቨርሲቲውም ትላንት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት እንዳካሄደ አቶ ማቲዎስ ተናግረዋል።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የወላይታ ሶዶ ዞን ፓሊስ ለጊዜው ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ደግሞ ጉዳዩን እንደሚያጣራ ገልጿልናል።

(ጉዳዩን እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ እናደርሳችኋለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA


" ሌሊት 10 ሰዓት ነው በትዳር አጋሯ የተገደለችው ፤ አንቆ ነው የገደላት " - የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ

በትግራይ፣ በውቕሮ ከተማ ድል ባለ ሰርግ ከተሞሸረች በኃላ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ ታንቃ ስለተገደለችው ሊዲያ ዓለም ጉዳይ የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ለቢቢሲ አማርኛው ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ፥ " ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ነው የተገደለችው " ብለዋል።

" ባለቤቷ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ለፖሊስ እጁን ሰጥቷል ፤ አሁን በሕግ ቁጥጥር ስር ይገኛል " ሲሉ አክለዋል።

ለድምጺ ወያነ ቃላቸውን የሰጡት የውቕሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ገብረ መድኅን ገብረጊዮርጊስ  ፥ " ተጠርጣሪው ብርሃነ ገብረጨርቆስ የተባለ ግለሰብ ነው " ብለዋል።

" የ4 ቀናት ባለቤቱን አንቆ ነው የገደላት " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቡ እጁን ለፖሊስ ከሰጠ በኋላ ራሱን ለማጥፋት የተለያዩ ሙከራዎች አድርጎ እንደበረ ገልጸዋል።

" ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እና ክትትል እያደረገ ነው " ብለዋል።

ሙሽራው የውቕሮ ተወላጅ እና በአዲስ አበባ በንግድ ስራ ይተዳደር ነበር። ውቕሮ ባረፈበት ሆቴል ውስጥ ንብረቱ እንደተገኘ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪው ሙሽራ እና የተገደለችው ሙሽሪት ሊዲያ ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3 ነው በደማቅ የሰርግ ሥነ ሥርዓት የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈጽመው የነበሩት።


❗️#ሰበር

የእስራኤል መንግስት የሃማስ አለቃ ያህያ ሲንዋር መሞታቸውን አረጋግጫለው አለ!

የሳራኤሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሀማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ወታደራዊ ሃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

እስራኤል ቀደም ሲል በጥቅምት 7 በሃማስ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በማቀነባበር ሲንዋርንበመወንጀል የእስራኤል መንግስት በጋዛ ሰርጥ አጸፋዊ ጥቃት ሰነዝራ ነበር::

በጋዛ ስትሪፕ ውስጥ የሃማስ መሪ የነበረው እስማኤል    ሃኒዬህ  በነሀሴ ወር ላይ በኢራን መገደሉን ተከትሎ ያህያ ሲንዋር መረከባቸው ይታወሳል::


የአዲስ አበባ ነዋሪዋና የቤት እመቤቷ ወ/ሮ ፀሐይ ገበየሁ በሞከሩት የ27ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ3ኛው ዕጣ የ1ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ ወደ ንግድ ሥራ እንደሚሰማሩበት ገልጸውልናል ፡፡




መምህሩ 4,000,000 / አራት ሚሊየን / ብር ተሸለመ !
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪው መምህር ማሙሽ ሔኖክ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሎተሪ የመቁረጥ ልምድ ያለው ሲሆን በተለይ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ ከተጀመረ ወዲህ በየዙሩ አድማስ ሎተሪን ይቆርጣል ፡፡ ታዲያ እንደተለመደው የ27ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በመቁረጥ የመውጫውን ቀን ሲጠባበቅ ነበር እና ዕጣው ከወጣ በኋላ በማግስቱ ለማመን የከበደው ስልክ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተደውሎለት የ4ሚሊየን ብር አሽናፊ መሆኑን ብስራቱ ይነገረዋል ፡፡ ለማመንም ከበደኝ ይላል መምህር ማሙሽ ፡፡ ታዲያ የ4 ሚሊየን ብር ቼኩን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተረክበዋል ፡፡ በደረሰውም ገንዘብ የንግድ ስራ ለመጀመር እንዳቀደ ተናግረዋል ፡፡


በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ዋጋ ላይ ምን አስተያየት አሎት?

10% = 30 ቢልየን ብር

ያሎትን አስተያየት ኮሜንት ላይ ይፃፉልን ::

እርሶስ ይገዛሉ?

https://t.me/+M8eqhx02b51jNGQ0
https://t.me/+M8eqhx02b51jNGQ0

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.