💚ጓደኞቻችን መልካም ስነ ምግባር ያላቸው ከሆነ ቀስ በቀስ የነሱን
ማንነት እንወርሳለች ከዚያ ከፍ ወዳለውና ወደ ተከበረው ምርጥ ማንነት እንወጣለን ምክኒያቱም ሁለት ንደኛሞች ሳይዋሀዱ መጥፎም ይሁን ጥሩ አንዳቸው የሌላኛቸን በሃሪ ይወርሳሉ💚
----ለምሳሌ አንድ ሰው መጥፎና ፀያፍ በሀሪ ያለውን አዲስ ጓደኛ ይተዋወቃል ከዚያ መጀመሪያ ከንደኛው የዋለ ቀን ሚሰራውን ፀያፍ ተግባር እያወገዘ እና እየተፀየፈ ይውላል በነጋታውም ይህን ተግባሩን ሲመለከት ደባሪ ተግባር እንደሆነ ይገለፅለታል ከ3-5ኛውም ቀን እንደዛው
………ቀስ በቀስ ከሳምንታት በኃላ ግን ያንን እኩይ ተግባር ይለምደዋል ምክኒያቱም በተደጋጋሚ ስለተመለከተው ከዛም ቀላል አድርጎ ያየዋል ይህ የሆነበት ምክኒያት አዕምሮው እኩይ ተግባሩን በተደጋጋሚ ስለተመለከተው ስለለመደው ነው ከአይምሮው ዘንድ መጥፎነት ካባውን አውልቆ ወደ ምንምነት ተቀይሯል ውሸት ሲደጋጋም እውነት እንደሚመስለው ወንጀልም ሲደጋገም ፅድቅ መልካም ስራ ይመስላል እንዲሉ ……ጓደኛ መምረጥ በወደፊቱም በመጥፎውም ሆነ ጥሩ እኛነታችን ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው።💚ስለዚህ እኛ ወደ ፊት መሆን የምንፈልገውን አይነት ሰው መርጠን ለንደኝነት እንያዝ😊
ከአህያ የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትመጣለች ትላለች እናቴ😁
@damnsquad