🥏 የግቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ስትማሩ እልኸኛ ልትሆኑ ይገባል። ለራሳችሁ ስትሉ እንዲሁም በተስፋ ለሚጠብቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ ስትሉ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ መታመን አለባችሁ
#️⃣ከምንም በላይ አዋዋላችሁ ላይ ጥንቃቄ አድርጉ!! ሰው ውሎውን ይመስላል ሲባል ተራ አባባል አይደለም ወደዳድችሁም ጠላችሁም ውሏችሁ ማንነታችሁን ይገነባል::
#️⃣ትክክለኛ መንገድ ላይ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ገጥማችሁ ከሆነ አሁኑኑ ግንኙነቱን አቋርጡት እና ለነጋቸው ዋጋ ከሚሰጡ እና ሳይኖራቸው ልጆቻቸውን ለማስተማር በሚለፉ ቤተሰባቸው ላብ ላይ ከማይቀልዱ ተማሪዎች ጋር ግጠሙ::
🔗በተለይ ሪሚዲያል እና fresh man ላይ በደንብ ትኩረት ሰጥታችሁ ተዘጋጁ ከዛ በኋላ በሚኖራችሁ ቆይታ ዘና ብላችሁ እየተማራችሁ ጎን ለጎን ቢዝነስ እየሰራችሁ ተመርቃችሁ ስትወጡ ቅጥር ሳትጠብቁ ቤተሰብ ላይም ጥገኛ ሳትሆኑ የራሳችሁን ነገር ራሳችሁን ችላችሁ መስራት ትችላላችሁ
ብልህ ሁኑ !!
ብዙ ነገር እየከበደ እየመጣ ነው እሱን ሁላችሁም በየቤታችሁ አስተውላችሁታል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ነገ እዚህ አለም ላይ ከፍ ብላችሁ ለመኖር ከፈለጋችሁ ዝቅ ብላችሁ እራሳችሁ ላይ ምትሰሩበት ሰዐት ላይ መሆናችሁን አስተውሉ
ማድረግ የምትችሉትን በሙሉ አድርጉ ከናንተ ምንም አይቅር የተረፈውን ለፈጣሪ ተዉለት
ከፊት ለሚጠብቃችሁ ፈተና ዝግጅት ያልጀመራችሁ ካሁኑ ጀምሩ በቂ ጊዜ አላችሁ አሁንም አልረፈደም!!
JOIN :
@ethio_learning_center