ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ከእስር ተለቀው የገና በአልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳልፈዋል::
********
ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ወንድሙ ኢብሳ እስር ከተፈፀመባቸው ጊዜ ጀምሮ ማህበሩ ተገቢውን ክትትል እያደረገ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አመራር በስልክ እንደገለፁት በእስር ቆይታቸው ይህ ነው የተባለ የአያያዝ ችግር ያልገጠማቸውና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል::
ጠበቃው ችሎት በመድፈር በሚል ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ በሚገኘው የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ጋር በተፈጠረ የቃላት ልውውጥ መነሻ ተደርጎ የአራት ወራት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑ የሚታወስ ነው::
የይግባኝ ክርክሩም በተሟላ ሁኔታ ታህሳስ 26 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተደረገ ሲሆን ችሎቱም ከፍተኛው ፍ/ቤት ለችሎት መድፈር መነሻ አድርጌአቸዋለሁ ካላቸው "17 ነጥቦች" 16ቱን ውድቅ በማድረግ የ4 ወራት እስራት ቅጣቱን በመሻር ከ 18 ቀናት እስር በኃላ እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል::
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ይህ የእስር ቅጣት ከተላለፈባቸው ቀን ጀምሮ "ከፍተኛ እገዛ" ላደረገላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር እና ለማህበሩ መሪዎች እንዲሁም በሂደቱ ለተሳተፉ የህግ ባለሙያዎች ምስጋናቸውንም አቅርበዋል:: የጠበቆች ማህበሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ እና በችሎት የሚሰየሙ ጠበቆችን ከመመደብ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግሮችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በቀጣይ ከጉዳዩና ተያያዥ ነጥቦች ዙሪያ የተሟላ ሪፖርት እና አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃል::
ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
አዲስ አበባ