የትዝታ ክምር
ዴቪድ ሂውም
ከፊት ለፊትህ ባዶ የቲያትር መድረክ አለ፤ አሮጌ መጋረጃዎች ያሉት፤ መሬቱ ለብዙ ጊዜያት ባለመጠረጉም አቧራ ለብሷል። ድንገትም ከጀርባ ወደ ቴያትር መድረኩ አንድ ሰው መጣ፡፡ እናትህ ነች፤ በሰባት አመትህ ሳለ ተረት ታነብልህ እንደነበረው አሁንም እያነበበች ነው፡፡ ድንገትም እናትህ ከመድረኩ ተሰወረች ፤ ሌላም ሰው መጣ። አንተን ይመስላል ፤ ይህንንም መጽሐፍ እያነበበ ነው፡፡ መመሳሰላችሁ ከፊትህ ያለን መስታወት የማየት ያህል ነው፡፡ ድንገት መድረኩን ብርሃን ወረሰው፤ ተመልሶም ባዶ ሆነ...
ዴቪድ ሂውም የሰው ማንነቱ ትዝታዎቹ ናቸው ይለናል። የምታስታውሳቸው ሃሳቦች፣ እናትህ የመከረችህ ምክሮች፣ ከጓደኞችህ ጋር የነበረህ ጨዋታ.... በሕይወትህ ያሳለፍከው ነገር ሁሉ አሁን ላይ ያለህን ማንነት ይቀርጸዋል። ወደ ምድር ስትመጣም ልክ እንደ ባዶ የቲያትር መድረክ ነበርክ፣ አሁን ግን በብዙ ትዝታዎች ተሞልተሃል።
“እኔ ማን ነኝ ለሚለው ጥያቄህም መልስ የሚሆነው ትዝታዎችህ ነህ ይሆናል። ልክ በድስት ውስጥ ያለ እና ሲንተከተክ እንደሚናወጥ ወጥ ነህ፡፡ በአእምሮ ውስጥ ያሉ ትውስታዎች እና ልማዶች ተደባልቀው ልክ እንደወጡ ሁሉ የሆነ ማንነት ይሰጡሃል። ይህ ወጥ በመጀመሪያ ሽንኩርት፣ ዘይት እና በርበሬ ብቻ ነበር... እየቆየ ሲሄድ ግን አይነቱ ይቀየራል፡፡ ምናልባትም መጨረሻው ስጋ ወጥ ወይም ሽሮ ወጥ መሆን ይሆናል፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ወደ ድስቱ የገባ ግብዓት የመጨረሻውን የወጥ ማንነት ይሰጠናል። ያንተም ማንነት እንደዚያው ነው፡፡ ቁጡነትህ፣ እርጋታህ፣ ፍቅርህ፣ ጥላቻህ፣ ችኮላህ፣ ትዕግስትህ፣ መወላወልህ፣ ቆራጥነትህ... ሁሉም ወደ አእምሮህ ከገቡ እና ካሳለፍካቸው ሁነቶች ይመነጫሉ፡
ለሂውም ሰዎች ሁሉ አንድ አይደሉም፡፡ ወጥ ሁሉ የተለያየ ቃና እንዳለው፣ ሁሉ ሰው የመጣበት መንገድ ይለያያል እና ፍጹም የተለያየ ማንነት ይኖረናል፡፡ ከሌላው ጋር አንድ የሚያደርገንም ነገር የለም፡፡ አንተ እራስህ የትውልድ ቦታህን ወይም የተወለድክበትን ጊዜ ቀይረህ ብትወለድ ፍጹም የተለየ ማንነትን ትይዛለህ፡፡ አዲስ በሌላ ጊዜ ወይም ቦታ ላይ የሚወለደው “አንተ” እና አሁን ላይ ያለኸው አንተ አንድ አይነት ሰው አትሆኑም።
እናም ሂውም አንተ የሃሳቦችህ እና የትዝታዎችህ ክምር ነህ ይልሃል። የእኔ ማንነትም የቱ ነው ካልክ፣ ወደ ባዶ የቲያትር መድረክ አፍጥጥ። አእምሮህ በምድር ላይ ያሳለፍከውን ሕይወት በዳግም ምልሰት ያስቃኝሃል፡፡ በአእምሮህ ከተቀረጹ ሃሳቦች ውጪ ማንነት የለህም። ማንነትህን እነርሱ ብቻ ይወስኑልሃል።