በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ የተመረጡ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎችን በቀጥታ ይከታተሉ
የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ይከፈታል።
የዘንድሮው አውሮፓ ዋንጫ በጀርመን አስተናጋጅነት ይካሄዳል።በውድድሩ 24 ሃገራት ተካፋይ ሲሆኑ እስከ ፍጻሜው 51 ጨዋታዎ ይደረጋሉ። ከ24 ሃገራት 622 ተጫዎቾች ለዚህ ክብር ይፋለማሉ።
አስተናጋጇ ሀገር ጀርመን ለዚህ ታላቅ ድግስ 10 ዘመናዊ ስታዲየሞችን አሰናድታለች።
ዛሬ ደማቁ የመክፈቻ ስነ ስርአትና ጨዋታ በሙኒኩ ግዙፍ ስታዲየም አሊያንዝ አሬና ይከናወናል።
ጀርመን ከስኮትላንድ 75 ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ይጫወታሉ። ጨዋታው በፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመን ተርፒን ፊሽካ ይጀመራል።
የአውሮፓ ዋንጫ ተጠባቂ ጨዋታዎችን ኤፍ ኤም አዲስ 97.1ና የኢትዮጵያ ሬዲዮ በጥምረት በመላ ሀገሪቱ ላሉ አድማጮች ያደርሳሉ።
በቴሌግራምና በድረ ገጻችን ይከታተሉ።የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ ለሌሎችም እያጋሩ ቤተሰብ ይሁኑ።
ለተሻለ ነገ እናዋጣለን!!!