የአባቶች ምክር


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


አስተማሪ የሆኑ የአባቶች ምክሮችን ÷መንፈሳዊ ፅሁፎችን፣ መፅሐፍቶችንና ትምህርቶችን የምናጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!@Father_advice

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


"መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡

"እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡

ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የአባቶች ምክር
√ በቲክ ቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2tuU7m7/ 
√ በቴሌግራም
🌿 @father_advice 🌿


Noma’lum dan repost
ጌታ ሆይ በማጣቴ ላመሰግንህ ገና ነኝ
በማግኜቴ እንዳመሰግንህ እርዳኝ

🌿 @father_advice 🌿


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


" የንስሐ አባት ማለት ! እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው
" ብጹዕ ወቅዱስ #አቡነ_ሽኖዳ ሣልሳዊ

https://vm.tiktok.com/ZM2twqEBN/


መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ።
⁵ በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።
⁶ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?

⁸ በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

⁹ በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል። … 
¹² ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው። … 
¹⁷ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ። … 
²⁴ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን
።

  የአባቶች ምክር
√
በቲክ ቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2tuU7m7/ 
√ በቴሌግራም
🌿 @father_advice 🌿


"Success needs patience and perseverance. And the person who becomes overcome by boredom and resentment and impatience and does not continue, cannot succeed: wait on the Lord  till He comes to your help, even if it be in the last watch of the night"

+ Pope Shenouda +


"ስኬት ትዕግስት እና ጽናት ያስፈልገዋል። እናም በመሰላቸት ፣ በንዴት ፣ ትዕግስት በማጣት የተሸነፈ እና የማይቀጥል ሰው ሊሳካለት አይችልም: ምንም እንኳን በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ቢሆንም ለእርዳታ ወደ እናንተ እስኪመጣ ድረስ ጌታን ጠብቁ."

+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ +
የአባቶች ምክር
√ በቲክ ቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2tuU7m7/ 
√ በቴሌግራም
🌿 @father_advice 🌿


በቲክቶክ follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
ሼር
https://vm.tiktok.com/ZM2tuU7m7/


"God does not forget a single step you took to go to church, or to visit someone who did not go to church, or to solve a problem. He does not forget your smile to someone who was downcast or the comforting word you said to comfort someone who was sad"

+ Pope Shenouda +

"እግዚአብሔር ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ  ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያን ያልሄደውን ሰው ለመጠየቅ ወይም ችግሩን ለመፍታት የወሰድከውን አንድ እርምጃ አይረሳም። ለተናደደ ሰው ፈገግታህን ወይም ያዘን ሰው ለማጽናናት የተናገርከውን አጽናኝ ቃል አይረሳም። 

+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ +

ሰውን ክፉ ተናግሮ ከማስቀየም እግዚአብሔር ይጠብቀን የእኛ ቃል በጨው እንደተቀመመ በፀጋ ሆኖ የሰዎችን ሰባራ የሚጠግን ያድርግልን!

      🌿 @father_advice 🌿


ወዳጄ ሆይ
ሰው ሆነህ ከሰው ጋር መኖር አቃተው አትባል!


🌿 @father_advice 🌿


አልችልም አትበል ይህ አነጋገር ወይም ቃል የክርስቲያን አይደለምና። የክርስቲያን ቃል እችላለሁ ነው ነገር ግን በራሴ አይደለም ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ  እንጂ

ቅዱስ ቲዮፋን

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13
🌿 @father_advice 🌿


ዘዳግም 6 🌿 @father_advice 🌿
¯¯¯¯¯¯¯
⁴ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
⁵ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።


የሰውን ልጅ በሩህሩህነትህ አሸንፈው ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው ሁሉንም ሰው ውደድ
ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር
ማር ይስሐቅ
🌿@father_advice 🌿


"በገነት ውስጥ አዳምን በመፈለግ እንደሄደው፣ እግዚአብሔር ዛሬም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሰዎችን ይፈልጋል።"

ቅዱስ አምብሮዝ
© @father_advice


"ይህ ጉባኤ ስለ ጌታችን ክብር ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጨ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ነገር ግን የጉባኤው መሰብሰብ በንጉሡ ትእዛዝ ከሆነ ንጉሡ እንዳሻው ይምራው"
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ


"" እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ። ""

እኔም። ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት።

አለኝም። እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ። ""
ራእይ 7 ፡13_17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፥ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።
¹⁶ ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፥ ፀሐይም ትኵሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፤
¹⁷ በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።

🌿 @father_advice 🌿


"ነገ ለአንተ የተሸለ ነው"

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡

ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።

ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
  🌿 @father_advice 🌿


"ጌታ ሆይ ወርቅ ትሰጠኝ ዘንድ አልለምንህም ሀብት ንብረትም አልለምንህም እነርሱ ድኅነትን የሚያስገኙ አይደሉም። ይቅርታህን ማግኘት ግን ከወርቅ ይልቃል። የኃጢአት ሥርየትን ማግኘትም ከብር ይበልጣል።"

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

  🌿 @father_advice 🌿


1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።

  🌿 @father_advice 🌿


ሰዎችን ከፍቅር ውጭ ሌላ በማናቸውም መንገድ ከክፋታቸው ልንመልሳቸው አንችልም።
ፍቅር ሰዎችን ከአውሬነታቸው መልሳ ሰው እንዲሆኑ የምታደርግ ታላቅ መምህር ናት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
🌿 @father_advice 🌿


ሉቃስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ማንም ለሰርግ ቢጠራህ በከበሬታ ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ተጠርቶ ይሆናልና አንተን እርሱንም የጠራ መጥቶ፦
⁹ ለዚህ ስፍራ ተውለት ይልሃል፥ በዚያን ጊዜም እያፈርህ በዝቅተኛው ስፍራ ልትሆን ትጀምራለህ።
¹⁰ ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ወደ ላይ ውጣ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል።
¹¹ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።

የአባቶች አባት ምክር❤️
🌿@father_advice 🌿

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 187

obunachilar
Kanal statistikasi