የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ‼️
ትምህርት ሚንስቴር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ተቋማት ስለ ጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል #ለአልዐይን አማርኛ እንዳሉት "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ብለዋል።
"ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ተናግረዋል።
ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል።
የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር፣የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ሲል ሚድያው ገልጿል።
ምንጭ ፡ አል-ዓይን
Join for more 👇
https://t.me/GraduationInfohttps://t.me/GraduationInfo