❓ግቢ ከገባን በኋላ ምን አይነት የኖት አፃፅፍ ስልት ብንከተል ነው ውጤታማ የምንሆነው ?
❓እንዴት አርጌ ብፈጥነው ሌክቸረሮች የሚያስተምሩትን እየተረዳሁ ኖት መፃፍ የምችለው ?
❓Highschool ላይ ያለውን የመማር ማስተማር ሙድ እንዴት መብላት ይቻላል?
*⃣ለሌክቸሩ መዘጋጀት
1⃣ሌክቸር ከመደረጋችሁ በፊት አንብባችሁ ግቡ
መምህራኖች የሚሰጧችሁን ሞጁል እና ንት ብትንትን አርጋችሁ ተረዱ እና ወደ ክላስ ግቡ
2⃣በምትማሩት እርዕስ ላይ የተፃፉ መረጃዎችን ከ Google ፈልጉ
አንዳንድ መምህራኖች አሉ ተማሪን ግራ ለማጋባት ብለው ከ curriculum ውጪ እየዘባረቁ ያሚያስተምሩ።ካዲያ ለነዚህ መምህራኖች መድሃኒቱ ጎግል ነው!እነሱ የሚጠቀሙትን መፅሃፍ የማግኘት እድል ሊያጋጥማችሁ ይችላል ፤ ባይሆን እንኳን የተለያየ አገላለፅ የዕውቀት አድማሳችሁን ያጎላላችኋል
3⃣ፊት ካለው ወንበር ተቀመጡ
ብዙ ተማሪዎች አስተማሪ ፊት ከተቀመጥኩ አስተማሪ በጥያቄ ያፈጥጠኛል ሰው ያየኛል ምናምን ብለው ይፈረሉ!ትልቁ ስህተት እዚጋ ጋር ነው ''ነገር በዓይን ይገባል ይል የለ ያገሬ ሰው!'' ስለዚህ የአስተማሪውን እያዳንዱን እንቅስቃሴ ፊት ለፊት ካለው ወንበር አካባቢ ተቀምጣችሁ ፣ ተከታተሉት!
እጃቸውን ከፍ ሲያረጉ ፤ ግንባራቸውን ከታች ወደ ላይ ከፍ ሲያረጉ ፤ ስሜታዊ ሆነው እግራቸውን ሰበር ካረጉ ያኔ ተጠንቀቁ ፈተና ላይ ሊወጣ የሚችለው part እየነገሯችሁ ነው ማለት ነው!
4⃣ ኖት የመፃፊያ ቁሳቁሶች እንደያዛችሁ እርግጠኛ ሁኑ
ማስደገፊያ የለለው ወንበር ላይ ካላችሁ ፣ ወይም የፀሃይ ብርሃን የሚያንፀባርቅባችሁ ከሆነ መምህሩ ከምግባቱ ቦታ ቀይሩ
5⃣ በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን ኖት ለመፃፏችሁ በፊት ፣ ቀን/ወር/ዓ.ም ብላችሁ ለእያንዳንዱ ቀን date ፃፉ
ይሄን አብዛኞቻችሁ አልሞከራችሁትም ግን እመኑኝ ፣ ብዙዎቻችን ያላረግነው የስኬት ትልቅ ሚስጥር ነው!ይሄን ስታረጉ ትምህርቱ በቁጥጥራችሁ ስር የወድቃል ፣ በየትኛው ቀን ምን እንደተማራችሁ ፤ መምህሩ በምንያክል ፍጠነት እየሄደ እንዳለ ፣ መምህሩ በየትኛው የጊዜ ክፈፍፍል ይበልጥ ፈተና እንደሚያወጣጣ እና ብዙ ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ታገኙበታላችሁ!
6⃣ለኖት አፃፅፋችሁ ትኩረት ስጡ!
በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ትርፍ መስመሮችን እለፉ!መምህሩ አዳዲስ ነገሮችን ሲናገር እነዛ መስመሮች ላይ ስታሰፈሩ ስታነቡ ይገባችኋል!
ኖቶቻችሁ ቁልጭ ቁልጭ ያሉ እና የሚነበቡ ይሁኑ!