......ከጊዜ ቡሃላ ለጠላከውም ለወደድከውም ነገር ፍላጎት ታጣለህ።
የቀረበክ ሲጎዳክ ታነባለህ ሰው ላትቀርብ ለራስህ ቃል ትገባለህ። ከዛ፤ የወደድከው ሲቀርብክም ሲርቅህም ተመሳሳይ ስሜት ይሰማካል!
እንዳመጣጡ ተቀብለክ እንዳካሄዱ ትሸኘዋለህ። ክፉ ሆነ ሳይሆን ጓደኝነትህን ባልተገባ ቋንቋ ስለተረጎሙት ነው።
ሰዎች ይከዱሃል ሲያሻቸው ማንነት አልባ ስም ለግሰውህ ቅስምህን ይሰብሩሃል።
አንተ ግን ዛሬም እንደትላንቱ ነህ!
ይህ ጽናትህ ነው!! ታጋሽነትህ ነገሮችን ይለውጣል። ምንም ቢጎዱ ወዳጄ ዝምታን ምረጥ ምክንያቱም ቃላቶችን ስተፋ ጭንቅላትህ እንዳይታይ ተጠንቀቅ። ጥለውህ የሄዱት ስለበዛህባቸው ና አንተን መሆን ባለመቻላቸው ነው። ምትገፋው ሁሌም ወደከፍታ ነውና።
🆔
@glmahii@glmahii