🔆ስኬት_እና_ስህተት እንዲሁም_
ውድቀት ?
〽️ስኬት የደስታ ቁልፍ አይደለም ይልቁንስ የስኬት ቁልፍ ደስታ ነው ! ምክንያቱም የምንሰራው ስራ ከወደድንው ስኬታማ ና ውጤታማ የማንሆንበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም ! ! !
🔆ደስታችን ከስኬታችን ያደርሰናል !
በሞያህ ደስተኛ ከሆንክ የምታስበው
ስኬት ወደ አንተ ይመጣል !
በምትሰራው ነገር ደስተኛ ከሆንክ ከጥሩ ነገር ትሰራለህ ከጥሩ ቦታ ትደርሳለህ ውጤትን ታገኛለህ !
〽️ስኬት ማለት ያለህበት ቦታ ሳይሆን የምታስበው የምታስበው ነገር ነው !
ስዎች ራሳቸው የወሰኑትን አለያም ያሰብትን ያክል ደስተኞች ናቸው !
እያንዳንዱ ሰው የሚደሰተው በዘጋጅው የደስታ መጠን ያክል ነው
〽️ደስተኛ የሚያደርግህ ያለህ ነገር ማንነትህ ያለህበት ቦታ አለያም የምትሰራው ስራ ሳይሆን የምታስበው ነገር አስተሳሰብህ ነው ! ምክንያቱም ደረጃህን የሚወስነው አቋምህ ሳይሆን አስተሳሰብህ ስለሆነ !ማንነታችንን ተቀብለን ከራሳችን ጋር ሰላም እስካልፈጠርን ድርስ ባለን ነገር ደስተኞች አንሆንም !
〽️በስኬታማ ሰውና በሌሎች መካክል ያለው ልዩነት የጥንካሬ ማጣት አለያም የችሎታ ማነስ ወይም የእውቀት አለመኖር ሳይሆን የፍላጎት ውጤት ነው !
ስኬት የተለየ ሚስጥር ያለው ሳይሆን የዝግጅት እና ጠንክሮ የመስራት ከውድቀት የመቆም ውጤት ነው !
ግን አጭበርብሮ ስኬት ከመቆናጠጥ
በክብር መውደቅ ይሻላል !
ስኬት በቅንነት እንጅ በብልጠት አይደለም ! ሊሆንም አይችልም ⁉️
〽️ውድቀት ስህተት እንጅ ወድቆ መቅረት አይደለም ፤ውድቀት ከተማርንበት ስኬት ነው ፤
ከተረዳነው የማይስተካከልበት ምንም አይነት ምክንያት የለም ስህተት የማይሰሩ ሰዎች ምንም የማይሰሩ ናቸው ፤ስህተት ሰርቶ የማያውቅ ሰው አዲስ ነገር መክሮ የማያውቅ ሰው ነው ፤ስህተት የማትፈፅም ከሆነ አንድ ነገር ለመስራት እየሞከርክ አይደለም ፤
〽️መሳሳት ያለ ሲሆን ለማረም መሞከር ደግሞ የሚስከብር ነው ፤
ማቀድ አልቻልንም ማለት ለመውደቅ እያቀድን ነው ማለት ነው / ካልተዘጋጀን እጥፍ ውድቀት ይሆናል ፤
ስህተት መስራቱን እያወቀ ለማረም የማይሞክር ሌላ ስህተት እየጨመረ ነው ፤
እርካታችን ጥረታችን ላይ እንጅ ውጤት ላይ አይሆንም የምናደርገው ነገር ሁሉ ለስኬት ብቻ ሳይሆን ለሰዎች ብለን ነው የሰው ልጅ ከስተቱ ይማራል አንድ ስተት መስራቱ ሌላ ስተት እንዳይደግም ያደርገዋል ፡፡
〽️ሁሌም ለሰው ልጅ ከምንም ነገር በላይ ስህተቱ አስተማሪው ነው ፦
የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚይሆን
የተጠረበ ድንጋይ ሐውልት እንደሚይሆን ሁሉ ፣
እንተም በብዙ ችግሮች ውጣ ውረዶች ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ ! በመሆኑም ሳታትንፍ ጠንካራ ስትሸነፍ የተረጋጋ ሁን !
〽️ውድቀት ከባድ ቢሆንም ለመነሳት አለመሞክር ደግሞ የከፋ ነው ፥
ውድቀት መውደቅ ሳይሆን ከወደቁበት ለመነሳት አለመሞከር ነው !
⚠️ታላቁ ድላችን እና ክብራችን አለመውደቃችን ሳይሆን በወድቅን ቁጥር መነሳታችን ነው ! ውደቀህ ለመቅረት ሳይሆን ለመነሳት ጣር !የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስክን አሻሽል ፥መሰናከልህን ለሚመኝ በስኬት ጎዳና ቀድመህ ተገኝ !
ሰላም!!
〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️
@gondaa @hubeei @gondaa@gondaa