Hawassa muslim medical association


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


የ ሀዋሳ ሙስሊም ሜዲካል አሶሴሽን የሚሰራቸውን ስራዎች ለአባላቶቹ መረጃ የሚያደርስበት ገፅ ነው።
📞 0972535908/0936707364

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


The Messenger of Allaah (peace and blessings of Allaah be upon him) cursed the man who wears women’s clothing and the woman who wears men’s clothing.


أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

የተለመዱት የሆስፒታል ዚያራዎቻችን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ በመተጋገዝ ውስጥ ያለውን ምንዳ በ ድብቅም በ ይፋም ለሚለግሱ ባሮቹ ሊያሳፍስ፣ የመታገስን ምንዳ ለነዚያ ከ ገንዘቦችም ከነፍሶችም በመቀነስ ለሞከራቸው ሊሰጥ ያስቀመጠን ፈጣሪያችን አላህ ምስጋና የተገባው ነው፡፡


በቅርቡ በተደረጉ ዚየራዎች ላይ እንደተለመደው በርከት ላሉ የ ትራንስፖርት ገንዘብ ችግር ለ ነበረባቸው ታካሚዎች ገንዘብ ሰጥተና፡፡ እንዲሁም ልብስ እና ሳሙናም ለመስጠት ችለናል፡፡ የአንድ ወር ከተማሪዎች የተሰበሰበ መዋጮን ሙሉ በ ሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ ለዚሁ ተጠቀመናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሁላቹም ያቅማቹን ያክል ገንዘብ በመለገስ ነገ ወደቤታቸው መመለሻ አጥተው፣ የህክምና ማስኬጃ ቸግሯቸው  ለምናገኛቸው ታካሚዎች እጃችንን ለእርዳታ እንዘረጋላቸው ዘንድ እገዛቹን እንድታደረጉ ጥሪያችን ነው፡፡


አንድ ለየት ያለ ገጠመኝም ነበረን፡፡ ጆሮው ላይ ሎቲ ያንጠለጠለ አንድ ወንድማችንን እዛዉ እንዲያወልቅ ማድረግም ችለናል፡፡

የስነ-ምግባር ምጥቀት፣ የአስተሳሰብ ጥልቀት፣ እንደ ማህበረሰብ ከፍ ያለ የሞራል ደረጃ፣ የነቃ ተውልድ፣ ከ አስተሳሰብ ልሽቀት ተጠብቆ የቆየ ማንነት ያለው ግለሰብ፣ ለአፈጣጠሩ የተገራ የሆነን የህይወት መንገድ ሚከተል የሆነ ሰዉ፣በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ባለ የስነ-ምግባር ሚዛን ላይ ሲቀመጥ በማያሻማ መልኩ ትክክለኝነቱ አመዝኖ ሚታይ የሆነ ማንነት ያለዉ አካል…..በ አጠቃላይ የ ላቀ ስብእና የሚንፀባረቅበት የሆነ ሰው የሚታነፅበት ሀይማኖት ተከታዮች ነን፡፡

ምስጋና በችሮታው  ለሚወደው ነገር ገር ላደረገን አላሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ነው::


ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት
~
ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን።
* ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል።
* የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው።
* የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም።
* ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ }
"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10]

Ibnu Munewor


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ ወንድም እና እህቶች እንዴት ናቹ ድርጅታችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሆስፒታል ሄዶ በመዘየር በትንሽ ገንዘብ ምክነያት ህክምና እያቋረጡ ላሉት ድጋፍ በማድረግ፣  መታከመያ በማጣት ምክነያት ቆሻሻ ከሆኑት የአክፍሮት ሀይላት የተጋለጡት ወንድም እና እህቶች ከአላህ ቀጥሎ አለንላቹ በማለት እንዲሁም መሰረታዊ የሆነ የዲን ጉዳዮች ላይ በማስታወስ ፣ታካሚ ሲሞት አጥቦና ገንዞ በመሸኘት ስራውን እየሰራ ይገኛል ። ሁሌም ቢሆን በምንችለው  ጊዜ ያለው በጊዜው ገንዘብ ያለው በገንዘቡ እንዲሁም በሀሳብ ተጋግዘን ከሰራን ገና ለብዙ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እንደርሳለን። ስራችንን በገንዘብ የምት ደግፋ ወገኖቻችን ሁሌም ቢሆን አዚህ ለሚሰሩ መልካም ስራዎችን በአጠቃላይ ጀርባ እንዲሁም ሞራል ናቹ እና ቀጥሉበት እንላለን። ከግቢ ተመርቃቹ የወጣቹ ልጆች ሁሌም ታስታውሳላቹ አና የወሩ መጨረሻ ስለደረሰ እያስታወሳቹ። አለህ ኸይር ጀዛቹን ይክፈላቹ። ግቢም ያላቹ ወንድም እና እህቶች አሁን ማስገቢያ(የወሩ መጨረሻ) ጊዜ ነውና በካሽ መስጠት ምትፈልጉ ለተመደቡ ሰብሳቢ አካለት በመስጠት በ account ምታስገቡት ደሞ ዛሬ ነገ ሳትሉ በማስገባት የመልካም ስራ ተካፋይ ሁኑ። እነዲሁም ካስገባቹ በኋላ ለሌሎችም ማነሳሻ ይሆናል እና groupu ላይ ሼር ብታረጉት። አላህም የሚመፀዉቱ ሰዎች ትሩፋት ሲነግረን፡

إنَّ الْمُصَّدِّقِينَ وَالْمُصَّدِّقَاتِ
وَأَقْرَضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعَفُ لَهُمْ وَلَهُمْ أَجْرٌ كَرِيمٌ
“የመጸወቱ ወንዶችና፣ የመጸወቱ ሴቶች፣ ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለእነርሱ መልካም ምንዳ አልላቸው፡፡”
مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً ۚ وَاللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْسُطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
“ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡”


Account
ስም ፡YEHAWASSA MUSLIMOCH TENA MAHBER
ZemZem bank 0032777020101
CBE NOOR 1000582135707


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

የ አስራ ሰባት አመት ፍለጋ እና ሽሽት ፍርሀት እና ናፍቆት ባማረ መልኩ ሲቋጭ ደስታ ሳቅ ለቅሶ እናት ለአስራ ሰባት አመት ካይኗ የራቀው ልጇን በማግኘቷ ማውራት አቅቷት ከአይኖቿ የሚወርዱ የደስታ እምባዎች  ብቻ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ከልብ የመነጨ እርካታ በአንድ የተሰበሰቡበት ድንቅ እና ያማረ ጊዜ ትላንት ሀሙስ በሆስፒታላችን ውስጥ በሚገኘው የታማሚዎች ካፌ አሳለፍን።

ውድ የተከበራቹ ወንድም እህቶች እንዲሁም  የዚህ በጎ ተግባር ቤተሰቦች እነሆ
ከባለፈው ጀምሮ እዚሁ ግሩፕ ላይ ብር ጠይቀን ህክምናውን ያስጨረስንለት ወንድማችን አብዱራህማን ከሰው ተጠግቶ ከመኖር ጎዳና እስከማደር፣ ለስምን አመታት ሳይካ ተመላልሶ መታከም፣ እንዲሁም በመጨረሻ ለቤተሰቦቹ መገኘት ሰበብ ይሆን ዘንድ ከኛጋ ያገናኘው፣ የኪንታሮቱ ቀዶ ጥገና፣ ከሰው ሁሉ ሸሽቶ መኖር ብቻ ብዙ ከባድ ጊዜያቶችን አሳልፏል። እኛም ከሱ ባገኘነው መረጃ መሰረት ቤተሰቦቹን ፍለጋ አዲስ አበባ፣ ወራቤ፣ ቅበት በምንችለው ሁሉ ተንቀሳቅሰናል። እነሆ በመጨረሻ ከብዙ ፍለጋ በዄላ ቤተሰቦቹ ተገኝተው በትላንትናው እለት እናቱ፣ አባቱ እና እህቱ ሀዋሳ በመምጣት ወላጆች አስራ ሰባት አመት ከጠፋው ልጃቸው እህትም ከወንድሟ በለቅሶ የታጀበ እኛንም ሳይቀር ባስለቀሰ ደስታ  ተገናኝተዋል። አዲስ አበባ ፣ ወራቤ፣ ቅበት እንዲሁም እኛ ግቢ የምትገኙ ቤተሰቦቹን ፍለጋ ስትለፉ ለነበራቹ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳቹ ይክፈላቹና ምስጋናችን ከልብ ነው።

ሁሌም ቢሆን በምንችለው  ጊዜ ያለው በጊዜው ገንዘብ ያለው በገንዘቡ እንዲሁም በሀሳብ ተጋግዘን ከሰራን ገና ለብዙ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እንደርሳለን። ስራችንን በገንዘብ የምት ደግፋ ወገኖቻችን ሁሌም ቢሆን አዚህ ለሚሰሩ መልካም ስራዎችን በአጠቃላይ ጀርባ እንዲሁም ሞራል ናቹ እና ቀጥሉበት እንላለን። አሁን ደሞ የወሩ መጨረሻም ስለሆነ እያስታወሳቹ። ሁላችሁም በቻላቹት ጠብ ጠብ አድርጉ።

Account
ስም ፡YEHAWASSA MUSLIMOCH TENA MAHBER
ZemZem bank 0032777020101
CBE NOOR 1000582135707


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ወንድማችንን አብዱራህማንን psyca ክትትል ላይ ለ8 አመት የቆየው አሁን ደሞ ኪንታሮት አሞት ሙሉ ምርመራው አልቆ ቀዶ ጥገና እንዲሰራለት ባለፈው እዚሁ ገንዘብ ጠይቀን ነበር።አልሀምዱሊላህ በአላህ ፍቃድ አንድ ወንድ ማችን ሙሉ ሆስፒታል ተኝቶ የሚታከምበት ክፍል መግቢያ 3500፣ ሌሎችም ሁለት ወንድሞች ለቀዶ ጥገናው የሚሆኑ እቃዎች መግዣ  2000እና 1000 አበርክተው እንደዚሁም አብዛኛው አባሎቻችን ባደረጉት እገዛ ቀዶ ተደርጎለት አገግሞ ወደ ማደረያው(ቤቱ) በሰላም ተመልሷል። ደውላቹ ገንዘብ ላበረከታቹ፣ ለቀዶ ጥገናው የሚሆኑ ከሌላ ቦታ  እቃዎች ስትሰበስቡ ለነበራቹ፣ እንዲሁም እንደ ቤተሰብ ሆስፒታል በመሆን ላስታመማቹ፣ አላህ መልካም ምንዳቹ ይመንዳንዳቹና ምስጋናችን ከልብ ነው።

ሁሌም ቢሆን ተባብረን ምንሰራ ከሆነ ገና ለብዙ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እንደርሳለን። አሁን በዚህ ልጅ ጉዳይ ሚቀረን ቤተሰቦቹ ያሉበት ፈልጎ ማግኘት እና ከነሱ መቀላቀል ነው። ኢንሻአሏህ እሱም በቅርብ ይሆናል።

እንደዚህ አይነት የተቸገሩ ወገኖቻችን ለመደገፍ አዲስ በተከፈቱ በማህበሩ አካውንቶች የምትችሉትን አግዙ። በተለይ በዘምዘም ብታስገቡልን ለማውጣት ይቀለናል።

Account
ስም ፡YEHAWASSA MUSLIMOCH TENA MAHBER
ZemZem bank 0032777020101
CBE NOOR 1000582135707


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ለኩ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቢላል የበጎ አድራጎት ድርጅት ለቶፊቅ ህመም ላይ እንዳለና እንዲረዱት ጥያቄ ቀርቦላቸው፡ መታመሙን እርግጠኛ ለመሆን እና ህመሙ ምን እንደሆነ ለማወቅ አስፈላጊውን መረጃ በምስል አስደግፈን እንድንልክላቸው ጠይቀውን ከሁለት ቀን በፊት ልከንላቸው ነበር። አላህ መልካም ምንዳቸው ይክፈላቸው እንዲሁም ድርጅታቸው አላህ ያሳድግላቸው እና ዛሬ ቀን 6:00 ከለኩ ሀዋሳ ድረስ መጥተው ተማሚ ወንድማችንን በመዘየር ለመዳኒት መግዣ እንዲሆናቸው #የ 9000 ብር ድጋፍ አድርገዋል። ወደፊትም አብረን እንድንሰራም አውርተናቸዋል። ሌሎችም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ታርጌታቹ አስፍታቹ ህመምተኞችንም ብታካትቱ እንላለን። እንዲሁም የኛ ማህበር ለሆስፒታል እና ለታማሚዎች በጣም ቅርብ ነውና በዚ ጉዳይ ማንኛውም እስላማዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኛ ጋር በጋራ እንዲሰራና ስራችንን እንዲያበረታታ በአላህ ስም እንጠይቃለን። ፍላጎት ያላቹ ድርጅቶች የቻናሉ ባዮ ላይ ባሉት ስልኮች ይደውሉልን።


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ባለፈው ዚያራ ስናረግ የ12 አመት ልጇን ስታስታምም  የመዳኒት መግዣ ባጣችበት ሰአት ያገኘናት የየቲሞች እናት እስከዛሬ ቀን ለስድስት ቀናት 1200 ብር በቀን እያወጣን ስንገዛላት ቆይተን ነገር ግን ማህበሩ ብዙ ተቀማጭ የለውም እና ስለተዳከመ፡ ዶክተሮቹም ልጁ ገና ለብዙ ቀናት በዚ መልኩ መቀጠል አለበት ስላሉ ምን ይሻላል ብለን አማክረናቸው ነበር። ወሏሂ ነገሩ በጣም አሳዛኝ ነው እናት እሱና የሱ ታላቅ ቢቻ ነው ያሉዋቱ። ሚኖሩትም ወደ ለኩ ቅርብ የሆነ ገጠር ነው። የታመመው ልጅ ምግብ ቤት እየሰራ ታላቁ ደሞ ካገኘ ወደ ለኩ እየሄደ የሰው ሞተር እየሰራ ገና ከጨቅላነታቸው ጀምሮ ሁለቱም እናታቸውን ህመም ስላለባት እንደምንም ብለው ያስተዳድሯት ነበር።ነገር ግን ዛሬ ህመም የሰው ፊት አስቆማቸው። የሚኖሩበት ሰፈር ደሞ የየአክፍሮት ሀይላት መንቀሳቀሻ ቦታ መሆኑ የበለጠ ያማል። ታላቁ ወንድም መስጊድ ለመለመን የዛሬ ሳምንት ጁሙአ ወደ ሰፈር ቢሄድም እስካሁን  ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት ስላልቻለ አልተመለሰም። አሁን በጁዋ ላይ ምንም ነገር የሌላት እናት ሆስፒታል ትገኛለች። ትንሽዬ በቆሎ ዘርተን ምንጠቀምባ መሬት ሽጠን ሰበብ እናደርሳለን ቢሉም ገዢ አላገኙም። ሁላችንም ብንተባበር ትንሽ ለሆነች ገንዘብ ብቸኛ ያላቸው መተዳደርያ ሊሸጡ፣ አሱም እስኪሆን የልጁ ሂወት አደጋ ለይ ነው። ያጀመአ ሁላችንም #የቲሞች ላይ መልፋት እነሱን ማገዝ ያለውን ምንዳ እያሰብን በመተባበር የዚህ #የቲም ልጅ ሂወት መትረፍ ሰበብ እንሁን። ይቺንም ጦሪዋ ታሞባት ጭንቀት ላይ ምትገኘው እናት እናሳርፍ።በቻልነው ልክ እንተባበር ፁፉንም share እናድርግ በጊዜም ወስደን መዳኒት እንድንገዛላቸው ለሌሎችም ማነሳሻ ይሆን ዘንድ ስታስገቡ ማሳወቁ እንዳትረሱ።


የምትጠቀሙት  አካውንት 1000435913389....Abdulmalik Argani Mufekir Negash




ሙስሊም......የ ክብር ስም ነው:: ለበላዩ ጌታ ትዕዛዝ ያደረ፣ ከከለከለው የተከለከለ....በህይወቱ ውስጥ ሁሉ ለፈጣሪው እጅ የሰጠ:: አላማው ጌታውን ማስደሰት ነውና ስህተተ ተገኝቶበት ሚሰጠውን ምክር ተቀብሎ ለመተግበር አያመነታም


ከ ትዕዛዝ ሁሉ በላጭ የሆነው- ተውሂድ፦

ከ እርሱ ውጭ ማንንም እንዳንገዛ ታዘናል:: ሌላ ላይ ሳይሆን እሱ ላይ ብቻ ተስፋችንን እንድንጥል ተነግረናል::
ሁሉን አድራጊ ከሆነው ጌታችን  እንጂ ከተቋጠረ ክር ጥበቃን አንሻም:: የኛ ጠባቂ በአንገት አይንጠለጠልም ...በ እጅ ላይ አይታሰርም....በእግር ላይ አይቋጠርም....ክርም፣ጎማም፣ስዕልም አይደለም:: የኛ ጠባቂ ከዚሁሉ የጠራው የሀይልም የብልሀትም ባለቤት የሆነው አላህ ነው::


በቅርቡ ባደረግናቸው ዚያራዋች ውስጥ የገጠመንን ልናካፍላቹ ወደድን

Pediatrics ward ዚያራ ላይ የ ምግብ እጥረት case የነበረበትን ልጇን ምታስታምም እናትን አገኘን:: እንደተለመደው ዚያራ እያደረግንላት እያለ የልጇ አንገት ላይ ሂርዝ ተመለከትን:: እናትየውንም ስላየነው ነገር ቀስ ብለን ጠየቅን:: ለሊት ሚያስጮኧው ነገር እንደነበር እና ለሱ መፍትሄ ይሆናል ብለው ያሰሩት እንደሆነ ነገረችን:: ከዚህ በመነሳት  ስለ ሂርዝ ሸሪአችን የሚለውን ጨምሮ ስለነገሩ በጣም የተጠላ መሆን ለማስረዳት ሞከርን::

ከዛም እጅግ ደስ በሚል ሁኔታ እራሷ በእጆቿ ሂርዙን በጥሳ ጣለችው:: እናም በአካባቢዋ ባለማወቅ መሰል ተግባር  የሚያከናውኑትን እንዲያቆሙ እንደምትነግራቸው ቃል ገብታልን ተሰነባበትን::

ከአንድ ሰው አንገት ላይ ሂርዝ ለመውለቁ ሰበብ መሆን በጣም ያስደስታል:: ፈጣን ምላሽ ሰጥቶ እዛው በጥሶ ሚጥል ሲኖር ደግሞ ደስታውን ከፍ ያደርገዋል::

ግዑዛንን ከመገዛት ለጠበቀን፣ ክርን ተስፋ ከማደረግ፣...ወደፀዳው ሀይማኖት ለመራን አላህ ምስጋና የተገባው ነው

اللهم إنا نعوذ بك من أن نشرك بك شيئا ونحن نعلم ونستغفرك لما لا نعلم....


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ትላንት የተለመደው ዝያራችን ለማድረግ ወደሆስፒታል አቀናን። ከዛም ወደ የህፃናት ድንገተኛ ክፍል ስንገባ አንዲት #የየቲሞች እናት የ 12 አመት ልጇን እያሳከመች አገኘናት። ልጁ በጣም ክሪቲካል patient አው። diagnos የተደረገውም pyogenic meningitis plus malaria ነው። እናትየውም ህክምናው እንዴት እየሄደ እንደሆነ ስንጠይቃቸው የመዳኒት እንደሌላቸው፣ እንዲሁም አሳቸውም ሚሰግዱበት ልብስ እንደሌላቸው ነገረዉን ተለያየን። እኛም ተመልሰን የመዳኒት መግዣና ሰላት እንዲሰግዱ ልብስ አመቻችተን ተመልሰን እንደምንዘይራቸው ነግረናቸዋል። ያጀመአ ይህ የሚሆነው ከተማሪ ተነሳሽነት በተጨማሪ እናንተ በምታደርጉት ድጋፍ ነውና ሁሌም እጃቹን በመዘርጋት እንድታበረታቱን እንላቹአለን። ተጠናክረን በመስራት ለንደዚ አይነት የቲሞች። አረ እንደውም ልጃቸው እንደዚህ ታሞ መዳኒት መግዣ የሌላቸው ምስኪኖችን ከአላህ ቀጥሎ እንድረስላቸው።

ነብዩ ሰሏሁ አለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው እንዲህ ይሉናል
"والله في عون العبد ما كان العبد في عون أجيه"

" አላህ ባረያውን በመርዳት ላይ ነው ባረያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስከ ሆነ ድረስ"

ለንደዚህ አይነት ለምስኪን የየቲም እናቶችን ማገዝ ሲሆን ደሞ ምንኛ ደስ ይላል።


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ባለፈው ህክምናው የጀመርነው የአእምሮ ታማሚ እና ለአስራ ስድስት አመታት ከቤተሰቡ ተለይቶ ለስድስት አመታት ደሞ ሆስፒታል የኖረው ወንድማችን ህክምና ጉዳይ አሁንም እንደቀጠለ ነው። በታዘዘለት መሰረት ከላይ በምስሉ እንደምታዩት  colenoscopy እና ultrasound ተሰርቶለት diagnosisu Internal hemorrhoid ተብሏል። ቀዶ ጥገና እንዲደረግለት የተወሰነ ቢሆንም  በሰአቱ ከላይ ሶስተኛው ምስል ላይ እንደምታዩት hemoglobinu በጣም ስለወረደ ድንገተኛ ክፍል ሄዶ ደም ተሰጥቶት ተስተካክሎ ይምጣ ብለው ነበር። ነገር ግን በሰአቱ screening ማሽን በመበላሸቱ ምክነያት ምንም አይነት ደም ሆስፒታሉ ውስጥ ስላልነበረ ድንገተኛ ክፍል ብንወስደውም ደም ማግኘት ሳይችል ወደ ማረፍያው ተመልሷል። ከዛም በጳጉሜ 3 ሁለት ዩኒት ደም ተገኝቶ ቢሰጠውም ለቀዶጥገና በቂ መሆን አልቻለም ነበር። ከዛም በቀን 3 እና 4 አንድ አንድ ዩኒት ተሰጥቶት hemoglobinu አራተኛው ምስል ላይ እንደምታዩት 10.5 ስለደረሰ ቀዶ ጥገና መካሄድ ይችላል። እስካሁን ባለው የምርመራ እንዲሁም ከምርመራው በፊት ድንገተኛ ክፍል በቆየባቸው ግዚያቶች ከ4000 ብር በለይ ወጥቷል። አሁን ሁሉም ምርመራ ጨርሶ ለቀዶ ጥገና ዝግጁ ቢሆንም በአጠቃላይ ከ8000ብር በላይ ሊያስፈልግ ስለሚችል ከኛ አቅም በላይ እየሆነ ነው። ልጁ ደሞ ያለበት ሁኔታ ሲታይ በጣም ያሳዝናል per rectum ሚደማው ነገር አሁንም እንዳለ ነው። የሚያድርበት ቦታ ደሞ የካፌ ሰራተኞች ሲደክሙ የሚየርፋበት እና ለማደር አደለም ትንሽ እራሱ እዛ ለመቆየት ሚከብድ ቦታ ነው።  ስለዚ ወንድምና እህቶች  ይህ ብዙ ስቃይ ያሳለፈፈ እና ለብዙ ጊዜያት በህመም የቆየውን ወንማችን አሳክመን ቤተሰቦቹን እንድናገናኘው ዘንድ በምትችሉትን ሁሉ አግዙን።አላህ ለመልካም ነገር ይግጠማቹ

የምትጠቀሙት  አካውንት 1000435913389....Abdulmalik Argani Mufekir Negash




أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ወደፊት ለመንቀሳቀስ ተስፋ...ስንዳከም ብርታት.....ቸልተኛ ስንሆን የህሊና ወቃሽ.....ስንዘነጋ አምላካችን ዘንድ ሚቀመጥልንን ምንዳ አስታዋሽ..... በስራችን ውስጥ ሁሉ ስንቅ......የሆነን በአላህ ፍቃድ  ያገዝናቸው ሰዋች ፈገግታ ነው:: ከበጣም ብዙ አቅመቢስነታችን ጋ የ ችሮታዋች ባለቤት በሆነው ጌታችን ድጋፍ የሰራናት ትንሿ ስራ ጠቁሮ የነበረውን አንድ ሰው ፊት ስታበራ ማየት ቃላት የማይገልፁት ስሜትን ይፈጥራል:: የዚህ ስሜት ተቋዳሽ ያደረገን  አላህ ምስጋና የተገባው ነው:: በፍጡራኑ ቁጥር ልክ...ነፍሱ በወደደችው ልክ...በዙፋኑ ክብደት ልክ...በቃላቱ ብዛት ልክ::



በባለፉት ሳምንታትም የተለመደው ዚያራችን ቀጥሎ ነበር :: አንዲት በኩላሊት ችግር ወደ ሆስፒታል የመጣችን እህት በመጀመሪያው ዙር ዚያራችን ላይ አገኘናት:: ከ ጥሩ አቀባበል ጋር ስላለችበት ሁኔታ ገለፁልን:: እኛም እንደ ሁልጊዜ በዲን ዙሪያ ማስታወስ ስራችንን ሰርተን ስናበቃ  በ ዱአ ተሸኘን:: ከ ዚያራችን ጥቂት ደቂቃዋች በኃላ ታካሚዋ የ አእምሮ ችግር ተከሰተባት :: ከዚህ ጋር ተያይዞ መሰረት የሌላቸውን ነገሮች ማየት እና መስማት (hallucination) እንዲሁም መጮህ ጀመረች::  ጩኸቷ ግን ከሸሀዳ ውጭ ሌላ አልነበረም !!

በሌላ ቀን ላይ እቺኑ ታካሚ በድጋሚ ለመዘየር ችለናል:: በዚ ግዜ ደግሞ አብረዋት ካሉ ሰዋች ጋር ያገኘናቸው ተጨማሪ ምርመራዋችን ማድረግ እንዳለባት እየተነገራት እሷ ግን "ደህና ነኝ" በማለት ከሆስፒታል ልትወጣ ስትል ነው:: ህክምናውን ማድረጊያ ገንዘብ የላቸውም....በሱ ሰበብ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የ ደም ማነስ ቢታይባትም "ደህና ነኝ"በማለት ከ ሆስፒታል ለመውጣት ተነስታለች:: የ ሚገርመው ነገር ደግሞ ከ ሆስፒታል ወጥተው ወደ ቤታቸው ሚሳፈሩበት ገንዘብም አልነበራቸውም::

በዚ ሁኔታ ላይ አገኘናቸው:: የተወሰነ ገንዘብም ሰጠናቸው:: ከዛም በ እንባ የታጀበ ደስታን አየን:: ነገሩ ሁሉ ጨልሞባቸው መቆያውም መሄጃውም በጨነቃቸው ሰአት አላህ አገናኘን:: እዚ ግባ በማይባል ገንዘብ ቢናገሩትም ቢፅፉትም የማይገለፅን ደስታ ሰዋቹ ፊት ላይ አየን!
አዋ ደስታ ያስለቅሳል! በለቅሶ ውስጥ እፎይታ ነበር...በለቅሶ ውስጥ የሚያበራ ፊት ነበር:: ከተለያየን በኃላ አንድ ሰውዮ ተከትሎን መጥቶ
የበዛ ዱአ ተደረገልን::

በኃላ ላይ እንደሰማነው ከሆነ ታካሚዋ "ደህና ነኝ" በማለት ላይ ፀንታ ከ ሆስፒታል ወጥተው ወደ ቤታቸው ሄደዋል:: አላህ ባለችበት ሆና አፊያ እንዲያረጋት ዱአችን ነው::


በእገዛችን ውስጥ ሁሉ ሰዋች ዘንድ የምትፈጠረው እፎይታ ለኛም በተለይ ላገዝናቸው ሰዋች ትልቅ ትርጉም ይኖራታል::


أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ከሀይማኖቶች ሁሉ በላጩን ተመርተን ሳለ ሀይማኖት እንደሌለዉ መቆጠር:: እሱንም እሺ ብሎ ተቀብሎ ወደ ተመሩበት እንደ ቦይ ውሀ መፍሰስ.....ፈጣሪያችን ከ የ ደምስራችን በላይ ለኛ ቅርብ ሆኖ ሲያበቃ  ሩቅ ወዳለ ማማተር... ለምኑኝ እሰጣቹሀለዉ ብሎን ሳለ ወደሱ መከጀልን ትቶ ደካማ ደጅ መጥናት...ቻይ የሆነ ጌታ ኖሮን ከእርሱ ሳንተዋወቅ ወደ ሌላ መዘንበል.....
በ እጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል እንዲሉ ሁሉ በሞላበት ቁጭ ብሎ ምንም የሌለበትን መጐምጀት ላስተዋለዉ ያሳፍራል ያስቆጫልም


እንደተለመደዉ  ታካሚዊችን ለመዘየር ወደ ሆስፒታላችን emergency ጎራ ብለን ነበር:: እጅጉን ቅስም የሚሰብር ነገር በ አይናችን አይተን በ ጆሮዋችንም አድምጠን ተመልሰናል::
ነገሩ እንዲህ ነዉ :

በ pediatrics emergency ወደ አንደኛዉ ክፍል ስንገባ አንድ ፓስተር ሁሉም ህፃናት (ሙስሊም የሆኑትን ጨምሮ) ላይ እጁን እየጫነ ሲፀልይ ተመለከትን:: ወደ አንዱ የሚፀልይበት ልጅ ቀረብ ስንል እሱ ወደ ሌላ ታካሚ ሄደ:: ለ ልጃቸዉ ሲፀለይላቸው የነበሩትን ሙስሊም ቤተሰቦች ቀስበቀስ ማውራት ጀመርን:: ለምን ፓስተሩ ልጃቸው ላይ እንዲፀልይበት እንደፈቀዱም ጠየቅናቸው:: መልሳቸውም "እኛ ካላመንበት... አሚን ካላልን ምን ችግር አለው" የሚል ነበር::

ከዚህ በመነሳት ስለ ተወኩል እና ተያያዥ ጉዳዮች ለማስረዳት ሞከርን:: በስተመጨረሻም ያደረጉት ነገር ልክ እንዳልነበር ከራሳቸው አንደበት ሰምተን ተለያየን::

እዛው ክፍል የዘየርናቸው ሌሎች ቤተሰቦችም(ሙስሊሞች ናቸው) ፖስተሩ እንደፀለየላቸው ነገሩን:: ነገሩ በጣም ያማል: : የተደረገው ነገር ልክ እንዳልሆነ በ ማስረዳት እንደ በፊቶቹ ቤተሰቦች አንድ አንድ ምክሮችን አደረግንላቸው:: በመቀጠልም ስለ ሰላት ጠየቅናቸው:: እናትየው እንደምትሰግድ ነገረችን አባት ግን በኩራት "መስገድ አቁሚያለው" አለን:: በመልሱ ተደናግጠን ስለ ሰላት ማውራታችንን ቀጠልን:: ከዛም ልመና ቀረሽ በሚመስል ንግግር እንዲሰግድ አደራ አልነው:: አኳኃኑ ግን ጭራሽ ንግግራችን የተዋጠለት አይመስልም ነበር: : ከክፍሉ ስንወጣም "እግዚአብሔር ይባርካቹ" በሚል ንግግር ሸኘን::


ድሮውንም ቢሆን ደክሞ የተገኘን እንጂ ደህናውን ለመጣል የሚታገል የለም:: በ ደካማ ጎናችን እንጂ የሚያጠቃን የለም:: ስለ ዲናችን ያለን አናሳ እውቀት ለበጣም ብዙ ጥቃቶች በር ይከፍታል:: ከ ሁሉም ጥቃት ብርቱው ከቀጥተኛው የ ኢስላም መንገድ እንድንወጣ መደረግ ነው::
ሆስፒታል ለሕክምና የሚመጡ ሰዋችን ደካማ ጎን ተጠቅሞ የማክፈሩ ስራ ቀጥሏል::
ጤና ያጣን "ጤናህን እንሰጥሀለን" ከሚል የበለጠ ሚያስደስተው ንግግር የለም::  ጤናን ሰጪም ነሺም አላህ እንደሆነ, የ ለማኝን ልመናም ሁሉ ሰሚ እንደሆነ ሰዋች በደከሙ ሰአት በማስታወስ በ አላህ ፍቃድ ብዙዋችን የ ውሸት ተስፋን እየሰጡ ከሚያከፍሯቸው አካላት መታደግ ይቻላል::
ልክ እንደዛሬው ፀሎት ብዙ ደካማ ሙስሊሞችን በ ገንዘብ የመደለሉ ስራም እንዳለ ነው:: ከ ዲናችን በላይ ክብር የለንም ! እና ሁላችንም ክብራችንን ሚያጎድፉብንን ጠንክረን እንዋጋ!


أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እና የሚሰራውን መልካም ስራ በሀሳብ፣ በገንዘብ እያገዛቹ ያላቹ ወንድም እና እህቶች እንደሚታወቀው ይህን መልካም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ገንዘብ አንዱና በጣም አስፈላጊ የሆነ ግባት ነው። ለጌዜው ደሞ የአሶሴሽናችን ገቢ ከናንተ  የሚሰበሰበው ገንዘብ ነው። እናም አሁን ያለንበት ጊዜ የወሩ መጨረሻ በመሆኑ ሁላችንም በቻልነው ልክ በትንሽ ገንዘብ ምክነያት ህክምና እያቋረጡ ላሉት፣  መታከመያ በማጣት ምክነያት ቆሻሻ ከሆኑት የአክፍሮት ሀይላት የተጋለጡት ወንድም እና እህቶች ከአላህ ቀጥሎ አለንላቹ እምበላቸው። ከግቢ ተመርቃቹ የወጣቹ ልጆች ሁሌም ታስታውሳላቹ አና የወሩ መጨረሻ ስለደረሰ እያስታወሳቹ። አለህ ኸይር ጀዛቹን ይክፈላቹ። ግቢም ያላቹ ወንድም እና እህቶች አሁን ማስገቢያ(የወሩ መጨረሻ) ጊዜ ነውና በካሽ መስጠት ምትፈልጉ ለተመደቡ ሰብሳቢ አካለት በመስጠት በ account ምታስገቡት ደሞ ዛሬ ነገ ሳትሉ በማስገባት የመልካም ስራ ተካፋይ ሁኑ። እነዲሁም ካስገባቹ በኋላ ለሌሎችም ማነሳሻ ይሆናል እና groupu ላይ ሼር ብታረጉት። አላህም የሚመፀዉቱ ሰዎች ትሩፋት ሲነግረን፡

إنَّ الْمُصَّدِّقِينَ وَالْمُصَّدِّقَاتِ
وَأَقْرَضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعَفُ لَهُمْ وَلَهُمْ أَجْرٌ كَرِيمٌ
“የመጸወቱ ወንዶችና፣ የመጸወቱ ሴቶች፣ ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለእነርሱ መልካም ምንዳ አልላቸው፡፡”
مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً ۚ وَاللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْسُطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
“ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡

የምትጠቀሙት  አካውንት 1000435913389....Abdulmalik Argani Mufekir Negash


أسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ማሳሰቢያ !!!!

በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥም ሆነ በዙርያው ባሉት መስጂዶች በታማሚ እንዲሁም በአስታማሚ ስም ሰዎችን ሲያታሉና ሲያጭበረብሩ አይተናል፤መስክረናል ።አንዱም ከሌላው የሚጠቀሟቸው ዘዴና ብልሀቶች አጂብ ከማስባሉ ጋር ጥቂት ሠዎች እንጂ አይደርሱባቸዉም።



አንድ ሰው ገንዘቡን በእኚህ አይነት ሰዎች ቢወሰድ በተስተካከለች ኒያው አላህ ዘንድ አጅሩን ባያጣውም በሀቂቃ ብዙ እየተፈተኑ ያሉት ወንድምና እህቶቻችን ስናይ ሰደቃው መድረስ ያለበት ቦታ ያለመድረሱ በጣም ያሳዝናል።

ለዚህም የሚታገዙትን ግለሠቦች ሀላቸውን በማጣራትና በመከታተል ስራዬ ነው ብለው ለያዙት ለcharity committee በማነጋገርና በመጠቆም ሰደቃቹን ለሚገባቸው አካላት ማድረስ ትችላላችሁ ።

قال تعالى :
لِلۡفُقَرَآءِ ٱلَّذِينَ أُحۡصِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسۡتَطِيعُونَ ضَرۡبٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ يَحۡسَبُهُمُ ٱلۡجَاهِلُ أَغۡنِيَآءَ مِنَ ٱلتَّعَفُّفِ تَعۡرِفُهُم بِسِيمَٰهُمۡ لَا يَسۡـَٔلُونَ ٱلنَّاسَ إِلۡحَافٗاۗ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عليم

˹Charity is˺ for the needy who are too engaged in the cause of Allah to move about in the land ˹for work˺. Those unfamiliar with their situation will think they are not in need ˹of charity˺ because they do not beg. You can recognize them by their appearance. They do not beg people persistently. Whatever you give in charity is certainly well known to Allah.


مفاهيم تكون خاطئة في أذهان بعض الناس /الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ ወንድምና እህቶች አንድ ወንድማችን እዚ እኛ ሆስፒታል በ2009 የአእምሮ ህመምተኛ ሆኖ መጣ። መዳኒት ተሰጥቶት በየጊዜው እየመጣ follow እንዲያረግ እና  መዳኒት እንዲወስድ ተነግሮት ተሸኘ። ነገር ግን እሱ  ከቤተሰቦቼ አልግባባም በማለት ቆየ። ከዛም የሆስፒታል ካፌ ሰራተኞች አስጠግተው ምግብ እየሰጡት እንዲሁም ሚሰሩበት ካፌ ማረፍያ ላይ አንድ አልጋ ሰጥተዉት እሱ በሚችለው ልክ አንድ አንድ ነገሮች እያገዘ የአእምሮ ህክምናውንም እየተከታተለ ያለፉት ስድስ አመት እና ወራቶችን ቆየ። ነገር ግን ያለፋት ሁለት ወራቶች ከአእምሮ ህመሙ ተጨማሪ ከሰገራውጋ ደም ይፈሰው ጀመር። ያስጠለሉት የካፌ ሰራተኞች ድንገተኛ ክፍል ወስደዉት ሲመረመር severe anemic + hemorrhoids ተብሎ 2 unit ደም transfuse ከተደረገ በኋላ ሙሉለሙሉ ሚያሳክመው ሰው ስላልነበረ ከሆስፒታሉ እንዲወጣ ተደረገ።የሆስፒታሉም አስተዳደር ግቢ ካሁን በኋላ ሚያድርበት ቦታ እንዳያድር ለሰራተኞቹ ትዛዝ አስተላለፉ። ነገር ግን ሰራተኞቹ መጠለያ እስኪያገኝ ድረስ ሆስፒታል አካባቢ ያሉ ሱቆች አንዲረዱት እየጠየቁለት እያለ ሙሉ ለሙሉ አልታከመም እና ድጋሚ ህመሙ አገረሸበት። ከደም መፍሰስ በተጨማሪ በተደጋጋሚ ያስመልሰው ጀመር። በዚህም የተጨነቁት የካሬ ሰራተኞች ሁሌ #በሰላት ሰአት ከሆስፒታሉ እየወጣ ጀማአ ሚሰግድበት መስጅድ በመሄድ ተናገሩ። በዚህ ጥቆማ ወደ ሚያድርበት ክፍል ስንሄድ ሁሌ አብሮን ጀመረ ሚሰግደው ነገር ግን በዚህ አይነት ሁኔታ እንደሚኖር የማናቀው ወንድማችን ሆኖ አገኘነው።እናም ወደ ድንገተኛ ክፍል ወሰድ ነው ። severe vomiting+bleeding ስለነበረው አሁንም severe anemic ሆነ። ከዚያም ደም ተሰጥቶት እዛው ድንገተኛ ክፍል ሶስት ቀን ከቆየ በኋላ ሲኒየር ሀኪም አማክረው የደም መፍሰሱ ከ hemorrhoid ሳይሆን ምን አልባት የመፍጫ አካላት ላይ እጢ ወይም ሌላ ችግር ሊኖር ይችላል። ስለዚህ ultrasound እና colenoscopy ይታይ ብሏል። ህክምናውም ወደ surgery opd ተዘዋውሮ ወደ ማረፍያው ተመልሷል። እናም ይህ ወንድማችን አሳክመን  ሚቻል ከሆነ ቤተሰቦቹ ያሉበት ፈልገን ለማገናኘት ካልሆነም ስራ ፈልገን እዚሁ ከተማ እራሱን እንዲችል ለማድረግ ወስነን ከመስጊዶች የተወሰነ ብር ሰብስበን ከማህበሩም ወጪ አርገን አሁን እስካለበት ደርሰናል። አሁን ህክምናው ለመጨረስ የultrasound, endoscopy እና የመዳኒት ወጪ ከዛም ደሞ ከተቻለ ወደ ቤቱ መመለሻ ስለሚያስፈልግ በቻልነው ልክ እንተባበር።



መዘየር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከICU ፊትለፊት በቆርቆሮ የታጠረው የሆስፒታሉ ምግብ ማብሰያ የሰራቶች ማረፍያ ክፍል ታገኙታላችሁ ። የአካባቢው ሰዎች ደሞ በ 0972535908/0736707364/0942441244 ብትደውሉ ያለበት ቦታ እናሳያቹአለን። ባረከሏሁፊኩም።

የምትጠቀሙት  አካውንት 1000435913389....Abdulmalik Argani Mufekir Negash


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قل تعالى :
"يُرِيۡدُوۡنَ اَنۡ يُّطۡفِـُٔـوۡا نُوۡرَ اللّٰهِ بِاَ فۡوَاهِهِمۡ وَيَاۡبَى اللّٰهُ اِلَّاۤ اَنۡ يُّتِمَّ نُوۡرَهٗ وَلَوۡ كَرِهَ الۡـكٰفِرُوۡنَ‏ "

"They seek to extinguish the light of Allah by blowing through their mouths; but Allah refuses everything except that He will perfect His light howsoever the unbelievers might abhor it."


እንደሚታወቀው ግቢያችን ውስጥ ተማሪ ባለመኖሩ የአከባቢው ሰውን በመጠቀም ታማሚዎችን ለማየት ተሞክሯል ።ከ2 ቀን በፊት በዚያራችን ወቅት ያጋጠመንን አንዱን እናካፍላችሁ ።

አንድ ሙስሊም ቤተሠብ ዘይረን ከጨረስን በኃላ ክፍሉ ውስጥ ሌላ ካለ ስንጠይቃቸው
"እዛ ጋር ያሉ ሙስሊም ይመስሉናል ግን ቅድም ሲፀለይላቸው ስለነበር እርግጠኛ አይደለንም" አሉን ።
እኛም ነገሩን ለማጣራት ወደነሱ ተጠጋን። በንግግራቸው መሀል አንዳንድ የነሳራ ቃላቶች እየተጠቀሙ ስለነበር ስለህክምናው ሂደት ብቻ አውርተን ተለያየን።
በዛሬው ዕለት ልብስ የሚያስፈልጋቸው ለመስጠት ጎራ ባልንበት እኚን ቤተሰብ በድጋሚ በመዘይር በውስጣችን የተፈጠረውን ግራመጋባት ነገርናቸው።

እነሱም የመለሱልን ምላሽ ይህን ይመስላል።

"እኛ በእርግጥ ሙስሊም ነን።የልጅቷን ሁኔታ ሀኪሞቹ መንስዔውን ማወቅ አልተቻለም ብለው ብዙ መድሀኒት ሲያስጀምሯት(viral meningioencephalitis r/o Tb meningitis r/o pyogenic M)
ወደ አጎትችን ዑስታዝ ስለሆነ መጥቶ ቁርዐን እንዲቀራላት ስንጠራው ሆስፒታል ውስጥ መሆኑ አስፈርቶት ነው መሠለኝ ወደ ኋላ አለ።........

አዎ! እነሱ የልጅቷን ሁኔታ ሲመለከቱ ፀሎት አደረጉላት።.....

በመጨረሻም church ብታመጧት ልጅቷ ሙሉ ለሙሉ እንደምትፈወስ ዳግም እዚ እንደማንመለስ ነገሩን። በዚህን ጊዜ ግን mother እምቢ አሉ።......"አሉን



∞∞∞ይህንን ክስተት ስንሰማ ልክ አንዱ የሰውነት ክፍሉ እንደተጎዳበት ያክል የነሱ ሁኔታ ካላሳሰበን ፣በአላህ ጠላቶች ላይ ቀልባችን ላይ ጥላቻ ካላደረበት እምነታችን ላይ ጉድለት አለና ልንፈትሽ ይገባናል።


የኛ በዲናችን ወደ ኋላ ማለት፣ካለማወቅም ይሁን ወኔ ከማጣት ለምን እንደዳረገ ልብ ብላቹ ይሆን ?


የነሱ በአንፃሩ መበርታት የት ደረጃ እንደ ደረሰስ?


ሲፀለይባቸውም ዝም ማለታቸውም የተውሂድ ማነስ አያስይዝም?


ነገሩን አውቀን ስናበቃ እጃችንን አጣጥፈን ብንቀመጥስ አያስጠይቀንም ይሆን?


የጉዳዩ አንገብጋቢነት የሁላችንም ርብርብ ይጠይቃልና ከማህበሩ ጎን በመቆም የዚህ ትልቅ አጅር ተካፋይ እንደትሆኑ እንጠይቃለን ።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

225

obunachilar
Kanal statistikasi