🎤 ቀኖቹ እየሄዱ ነው።
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➧ እነዚህ አላህ የማለባቸው በእነዚያ በታወቁ ቀናቶች ጌታችሁን አስታውሱ ብሉ የነብዩን ኡማ ያመላከተባቸው ልዩ ቀናቶች እያለቁ ናቸው።።
ምን ሰርተናል ባለፉት ቀናቶች ሁሉም የዒባዳ አይነቶች ከፊት ሆነው እኔስ እያሉ እንድንሽቀዳደም በሚገፋፉበት ጥቂት ቀናት ምን ሰራን ምንስ ወደ ኋላ አደረግን ለነገው ቤታችን ወይስ የበይ ተመልካች ልንሆን ነው?
እነዚህ ሰለፎች ያለ ሀይላቸውን ተጠቅመው ለአኼራ ስንቅ ሲያዘጋጁባቸው የነበሩት ቀናቶች በምን መልኩ እያለፉ ነው? በቀሩት ቀናት በመንችለው የመልካም ስራ አይነት እንትጋ አንዘናጋ ስንቅ ያስፈልገናል መንገደኞች ነን የሚቀበለን ዘመድ አዝማድ ሳይሆን መልካም ስራችን ነው።
በመሆኑም እንዳንቦዝን እንዳንተክዝ የሚያደርገን መልካም ስራ አብሽር የሚለን ከቀብር ጀምሮ አላህ ፊት እስክንቆም ሲራጥን ለመሻገር ሚዛናችን ከፍ እንዲል የስራ መዝገባችን በቀኝ እጃችን እንዲሰጠን የቀኝ ጓዶች እንድንባል ፈሪቁል ፊል ጀናህ ከሚባሉት ለመሆን ስንቅ ያስፈልገናል። ቀሪ ሒሳባችን አያስተማምንም እንትጋ አንዘናጋ ለዚህ ትልቁ አጋጣሚ እነዚህን የቀሩት ቀናቶች መጠቀምን አማራጭ የሌለው ተግባራችን እናድርግ አላህ ለመልካሙ ሁሉ ይወፍቀን።
http://t.me/bahruteka