ኢብኑ-ያሲር ሸሪዓዊ የውይይት መድረክ Chanel📚📚


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ ቻላል አላማው👉አላማችን የአህለን ስና ወል ጀማአ ስብስብ ለማጠናከር እና ባለ ማወቅ በቢዳአ ተዘፍቀው ያሉ ሰዎች ከጨለማ ወደ ብርአን ወደ ሆነው አህለን ሱና ወል ጀማአ ለማምጣት እና የቢዳአ ሰዎችን በአህለን ሱናውል ጀማአ እየቀጠፉ እና በዲን ስም የሚነግዱ ሰዎችን ማጋለጥ እና የተፈጠርንበት አላማ በተቻለው አቅም ለመወጣት ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው
    👉https://t.me/ibnuyasir10

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ጊዜው ወደ ሀራም ለመድረስ
በጣም ቀላል ከሆነ አላህን መፍራቱ
በጣም ትልቅ ምንዳን ያስገኛል

       


((ግዜው ነው ይሉሀል))
"""""""
\\ግዜ. ምን አረገ ከፍ አለ ዝቅ አለ !!
\ወይንስ ምን አረገ ፈቀቅም አላለ !!
\\ወይ. ትንሽ አልሸሸ !!
\\ስው. በግዜ. እየኖረ. ግዜን አበላሸ!!
\\ጊዜው ነው ይሉሃል. የዘንድሮ ሰው !!
\\በጊዜ. ሳይሰራ. ስራው የጣለው. !!
    """"""""""""""""" ካንተ ጋር ይበላል
       """"""""""""'''ካንተ ጋር. ይጠጣል
      """""""""'''"""'ካንተ ጋር.  ይስቃል
ችግር ሲያጋጥምህ ከጎንህ ይርቃል!!!
ምንድነው. ስትለው. ግዜው ነው ይልሀል!!
""""""""""" ይጠመዘዝ ቢሆን ግዜ እደስአት
""""""" ትናት ዛሬ ሁኖ ምነው. ባየሁት
በነገራችላይ. በድናችንም ምን አይነት ግዜ ነው

ብለን ግዜን መሳደብ አይፈቀድም ሁሉም
የአላህ ውሳኔ ነው ።🌹

  
#አደራችሁ_ቤተሰብ

ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


#የጥበበኛው_ሉቁማን_ምክሮች

#አንድ ቀን ልጃቸውን እንዲህ በማለት ምክር ሰጡት :-
1, ዱንያ (ምድራዊ ህይወት) እንደ ጥልቅ ባህር ነች በሷም ብዙዎች ሰምጠዋል ። ስለዚህ በሷ ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለክ ጀልባህን የአላህ ፍራቻ ፤ መቅዘፋያህን ኢማን ፤ መንገድህን ደግሞ በአላህ ላይ መመካት አድርግ።

#ልጄ ሆይ

ከፈሪሃ አላህ ሰዎች ጋር ሁሌም ተጎዳኝ እነርሱ በሚሰሩት ስራ ተካፋይ ትሆናለህና በተጨማሪም የአላህ ልዩ ፀጋ በነርሱ ላይ ሲወርድ አንተም ከድርሻው ታገኛለህና ። ከመጥፎ ሰዎች ጋር አትጎዳኝ ከነርሱ የሚገኝ መልካም ነገር የለምና ። ይልቅስ የአላህ ቅጣት በወረደችባቸው ጊዜ አንተም ከቅጣቱ ተካፋይ ከመሆን በቀር ።


ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


🎀ጥቂት ማስታወሻ ለሙስሊሟ እህቴ🎀 dan repost
😊አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም 🎁
🎁ዛሬ እሮብ ማታ ለየት ያለ ፕሮግራም አለ ✅

ተጋባዥ ኡስታዞች
⭐️
➡️አቡ ሂበቱላህ
    ርዕስ:- በሰአቱ ይነገራል

➡️አብዱሽኩር አቡ ፈውዛን
    ርዕስ :-  በሰአቱ ይነገራል

🏠ቀን እና ሰዓት ዛሬ ማታ

😓ከምሽቱ 3:20 ጀምሮ🔋

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል✨
😋
t.me/bint_hashim_aselfiey
t.me/bint_hashim_aselfiey


ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«በብስለትህ እና እውቀትህ በመብዛቱ አትተማማን(አትደገፍ) ፤ ይልቁኑ ወደ ኃያሉ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ተደገፍ ፤ ሰዎች ከተለያዩበትም ነገር ወደ ሐቁ እንዲመራህ አላህን ዘወትር ጠይቀው።»

📚 ۞ شرح أصول التفسير【1/2

በጌታህ ጥላስር ለመሆን የሞቀ ፍራሽህን ለቀቅ አድርገህ ሱብሂ መስገድ ግድ ይልሃል ሀቢቢ ተነስ
#ፈጅር

https://t.me/ibnuyasir11


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ተጋበዙልኝ መልካም ለይል....!

=002
ቻናል፦ t.me/ibnuyasir11


ሙስሊሞችን ያለአግባብ በከሃዲነት መወረፍ ከሚያስከትላቸው መዘዞች ሁለቱን እነሆ!


* አንደኛ፦👇
የአንድን ሙስሊም ክብር ያለ አግባብ ማጉደፍ ጉዳዩን የተመለከቱ ሸሪዓዊ ትዕዛዛትን መጣስ ከመሆኑ ባሻገር ለከፋ ቅጣትም ያጋልጣል።


عن ابن عمر، عن النبي -صلى الله عليه وسلم- أنه قال: «...مَنْ قَالَ فِي مُؤْمِنٍ مَا لَيْسَ فِيهِ، أَسْكَنَهُ اللَّهُ رَدْغَةَ الْخَبَالِ حَتَّى يَخْرُجَ مِمَّا قَالَ».
= ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
«በአንድ አማኝ ላይ የሌለበትን የተናገረ ከንግግሩ ጣጣ እስኪወጣ ድረስ አላህ የ“ጥፋት ማጥ” ውስጥ ያኖረዋል!»
[አሕመድ  (ቁጥር፡ 5385)፣ አቡ ዳዉድ (ቁ. 3597) እና ሌሎችም የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲሥ ነው፤ “ሲልሲለቱ’ል-አሓዲሥ አስ-ሰሒሓህ” (ቁ. 437) ይመልከቱ።]

በሌላ አጋጣሚ ሰሓቦች «የ“ጥፋት ማጥ” (رَدْغَة الْخَبَالِ) ምንድነው?» ብለው ሲጠይቁ ነብያችንም «የእሳት ነዋሪዎች እዥ!» ብለው መልሰዋል። [ኢብኑ ማጃህ (ቁ.3377)]

- «ሙስሊምን መሳደብ አመፅ ነው!» የሚለው የነብያችን ንግግር [አል-ቡኻሪይ (ቁ. 46)፣ ሙስሊም (ቁ. 64)] ማንኛውንም አግባብ-የለሽ ስድብ የተመለከተ ከሆነ ጭራሽ እምነት ላይ የሚያነጣጥር ዘለፋ ደግሞ ከዚህ የከፋ መዘዝ እንደሚጎትት ግልፅ ነው።

☞ ሸይኹ'ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ እንዲህ ይላሉ፦

فإذا كان من يقضي بين الناس في الأموال والدماء والأعراض إذا لم يكن عالما عادلا كان في النار؛ فكيف بمن يحكم في الملل والأديان وأصول الإيمان والمعارف الإلهية والمعالم الكلية بلا علم ولا عدل..
«በንብረት፣ በነፍስና በክብረ ስብእና ጉዳዮች ላይ በሰዎች መሃል የሚዳኝ ሰው አዋቂና ፍትኸኛ ካልሆነ የእሳት የሚሆን ከሆነ ስለ እምነት መንገዶች፣ ስለ ሀይማኖቶች፣ ስለ እምነት መሰረቶች፣ ስለ መለኮታዊ የእውቀት ዘርፎችና አጠቃላይ እሴቶች ያለ እውቀትና ያለ ፍትህ የሚፈርድስ እንዴት ይሆናል?!»   ["አል-ጀዋቡ አስ-ሶሒሕ.." (1/108)]

ይህንን የሚያጠናክረው ሁለተኛው ነጥብ ነው፦

* ሁለተኛ:-👇
አንድ ሙስሊምን ያለ አግባብ “ከሃዲ፣ የአላህ ጠላት፣ ሙናፊቅ..” ብሎ መጥራት እምነትን ለአደጋ የሚያጋልጥ አደገኛ ጠንቅ ነው።


عن ابْنَ عُمَرَ، قَالَ رَسُولُ اللهِ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: « أَيُّمَا امْرِئٍ قَالَ لِأَخِيهِ: يَا كَافِرُ، فَقَدْ بَاءَ بِهَا أَحَدُهُمَا، إِنْ كَانَ كَمَا قَالَ، وَإِلَّا رَجَعَتْ عَلَيْهِ
= ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
«ወንድሙን “አንተ ከሃዲ” ያለ ማንኛውም ግለሰብ = ከሁለቱ አንዳቸው ይህን ተሸክሞ ይመለሳል፤ እርሱ እንዳለው ካልሆነ በስተቀር (ፍርዱ ወይም መዘዙ) ወደ ራሱ ይመለሳል!» 
[አል-ቡኻሪይ (ቁ.6104)፣ ሙስሊም (ቁ. 60)]

-አቡ ዘር ባስተላለፉት ሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ፦
«..وَمَنْ دَعَا رَجُلًا بِالْكُفْرِ، أَوْ قَالَ: عَدُوُّ اللهِ وَلَيْسَ كَذَلِكَ إِلَّا حَارَ عَلَيْهِ»
= «..አንድን ሰው በከሃዲነት የፈረጀ ወይም “አንተ የአላህ ጠላት!” ብሎ የጠራው እርሱ እንዳለው ካልሆነ (ፍርዱ ወይም መዘዙ) ወደራሱ መመለሱ አይቀርም!» ብለዋል።
[አል-ቡኻሪይ (ቁ.6045)፣ ሙስሊም (ቁ. 61)]

- ሣቢት ኢብኑ አድ-ዶሕ-ሓክ በሚያስተላልፉት ሐዲሥ ደግሞ
«... وَمَنْ رَمَى مُؤْمِنًا بِكُفْرٍ فَهُوَ كَقَتْلِهِ»
= «አንድን አማኝ በከሃዲነት የወነጀለ እርሱን እንደ ገደለው ነው!» ብለዋል።
[አል-ቡኻሪይ (ቁ.6105)]

ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


በርግጥ የኔን ብርሃን እንዲደምቅ አቅም የምሰጠው እኔ አይደለሁም፣ አላህ እንጂ። መድመቅ ካለበት ይደምቃል፣ ምንም እንኳ አጥፊዎች ቢበዙ። እነዚያ ቂሎች ግን ደብዛዛ ብርሃናቸው የደመቀ ይመስላቸዋል እንጂ አይሳካም።

ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


#መልካም_ሥራ_ተቀባይነት_እንዲያገኝ #መሟላት_ያለባቸው_ነገሮች_ምንድ ናቸው* ?!

መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሶስት (3) ነገሮች መሟላት አለባቸው ።

.    እነሱም:-
በአላህ አንድነትና ብቸኛ አምላክነት በትክክል ማመን።!


.    (ቁርአን እንዲህ ይላል👇

إن الذين امنوا وعملوا الصالحات كانت لهم جنات  الفردوس نزلآ » سورة الكهف.

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎንም የሠሩ " የፈርደውስ ገነቶች ለነሱ መስፈሪያ ናቸው።!

و قال صلى الله عليه و سلم قل امنت بالله ثم استقم « رواه مسلم. »
📰 የአላህ መልእክተኛ " ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም )

"እንዲህ ብለዋል :- በአላህ አመንኩ በልና በፍቃዱም ቀጥ በል።
.      (ሙስሊም
)

2} ሥራው የጠራና ከልብ የመነጨ መሆን:- ይህም ማለት ➖የሚሰራው መልካም ሥራ ለአላህ ውዴታ ተብሎ መሆን " እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው።

📰ሥራው" ስዎች ለማስደሰት ከሰው ፊት አክብሮትንና አድናቆትን ለማትረፍ ተብሎ የተሰራ የይስሙላ ሥራ) መሆን የለበትም።!

📜 «‌ و ما أمروا  الا ليعبدوا الله مخلصين له الدين حنفاء. » سورة البينة.

አላህን ፡- ሀይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች " ቀጥተኞች ሆነው ሊገዙት፦ (98:5)


*ሰራዎች  መከናወን ያለበት የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ባስተማሩት መሰረት መሆን አለበት*።

📜«وما اتاكم الرسول فخذوه وما نهاكم عنه فانتهوا واتقوا الله إن الله شديد العقاب»  سورة الحشر.
📜መልዕክተኛው የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከእርሱም የከለክላቹሁን ነገር ተከልከሉ።  አላህንም ፍሩ ፦ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነውና።(59፡7)


📜 و قال صلى الله عليه و سلم من عمل عملآ  ليس عليه امرنا فهو رد »  رواه مسلم.
የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም)
የእኛ ፍቃድ ያልሆነን ነገር ያከናወነ ሰው ተግባሩ ውድቅ ነው። ሲሉ ተናግረዋል። (ሙስሊም)


ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


★ለወሬ የለውም ፍሬ★

የተሰማ ሁሉ አይወራም
★የተሰማ ሁሉ አይታመንም
★የሰሙትን ሁሉ ሳያጣሩ ማውራት የሰይጧን አጫፋሪነት ነው።
★የማጣሪያው መንገድ ኡለሞች ናቸው ።

قال الله تعالى: (وَإِذَا جَاءَهُمْ أَمْرٌ مِّنَ الْأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُوا بِهِ ۖ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى الرَّسُولِ وَإِلَىٰ أُولِي الْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ الَّذِينَ يَسْتَنبِطُونَهُ مِنْهُمْ ۗ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ لَاتَّبَعْتُمُ الشَّيْطَانَ إِلَّا قَلِيلًا)

[ ከጸጥታ፣ከድል ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ ያሰራጫሉ ፡፡ ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር ፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶች በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር፡፡]
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 83)


قال الله تعالى:  {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِين}َ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡)
(ሱረቱ አል-ሁጁራት - 6
)


የመንደር ወሬ ፣አሉባልታ፣መሰለኝና ሳይሆን አይቀርም  እየተባሉ ሚወሩ ወሬዎች ሸይጣንን ከማስደሰት በስተቀር  አይጠቅሙም አላህም ፊት ያስጠይቃሉ ።
ተቀያየመ፣ታጣላ፣ተዋጋ!
በወሬ ስንቱ ከሰረ! 


ሳያዩ ፣ሳይሰሙ ፣ ሳያጣሩ ፣ሳያረጋግጡ
ከማውራት አላህ ይጠብቀን
🤲🤲

መልካም የኢባዳ ቀን
ቻናል:-
https://t.me/ibnuyasir11


አልሃምዱሊላህ ነጋልን


ነጋ አይደል እኮ ፀሃዩዋን ለማየት እድል ሰጠን
በዛው ነብሳችንን አልያዛትም። እስትግፋር ወደሱ ልንመለስ እድል ሰጠን አይደል እና አሁንም ከትላንትናው መለስ ብለን ከትላንቱ የበለጠ እሱን መገዛት ለወንጀሎቻችን ምህረትን መጠየቅ ወደሱም ሽሹ 🥀🥀


አልሃምዱሊላህ
الحمدلله🌸   
Alhamdulillah

በእዝነቱ በችሮቻው በራህመቱ አንግተናል
ለላቀው ጌታችን አሏሁ ሱበሀነሁ ወተአላ
የላቀ ምስጋናና ውዳሴ ይገባው
🥀🥀

ቀንህን በዚክር ጀምረው

የጧት ዚክር እንዳንረሳ!!
      〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
               #ፈዘኪር

       🥀🥀ሶባሐል ኸይር🥀🥀
      


#ፈጅር ... ሰላት     
⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡     
   ፈጅር ....         
ለፊትህ ብርሀን ፣  ለልብህ እረፍት  ፣  ለነፍስህ መርጊያ ናት ! 
 
حي على الصلاة
حي على اافلاح   
الصلاة خير من النون  ❗️ 

 🇰🇼ፈጅር አዛን 5.28


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ተጋበዙልኝ መልካም ለይል....!

=001
ቻናል፦ t.me/ibnuyasir11


#የሸይኽ ፈውዛን ሃፊዘሁላህ ምክር!

#ሃውድን መጠጣት ከፈለግክ በመንሃጅ ላይ ቀጥ በል!

·
#ሸይኽ ፈውዛን፡ ከነብዩ (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀውድ መጠጣት ከፈለግክ አላህ እና መልክተኛውን ታዘዝ፡፡

·

#የሙሀመድ ኡመት ነኝ ብሎ ነገር ግን የመልክተኛውን (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንሀጅ የማይታዘዝ፤ የማይተገብር እና የማይከተል ይህ ሰው ኢስላም ከሚለው ስም አይጠቀመም፡፡
#ይልቁንስ ሰዎች በተጠሙበት ሰዓት ሃውድን አይጠጣም አላህ ይጠብቀን እና፡፡

#እናም ከዚህ ሀውድ መጠጣት የፈለገ ሱናን አጥብቆ ይያዝ (ይተግብር)፤ ሱናን አጥብቆ መያዝ ደግሞ ቀላል ነገር አይደለም፤ ፈተና እና መከራ አለው፡፡ #የሚያነውሩህ፤ የሚያስቸግሩህ፤ ክብርህን የሚያጎድፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
#ይሄ ሰው ፅንፈኛ፤ ጠርዘኛ፤ እናም ሌላም›› ይሉሃል፤ ወይንም በንግግር ብቻ ላያበቁ ይችላሉ ይገሉሃል፤ ወይንም ያስሩሃል፡፡

#ነገር ግን ታገስ ደህንነትን እና ከሃውድ መጠጣትን ከፈለግክ፡፡ #የአላህ መልክተኛን  (ﷺ) አለይሂ ወሰለም) ሀውድ ላይ እስክታገኝ ድረስ  #ሱናን በመያዝ ላይ ታገስ (ፅና)፡፡

#ምንጭ ☞
شرح الدّرة المضيّة في عقد أهل الفرقة المرضية


#መልካም_ለይል

ቻናል:-
https://t.me/ibnuyasir11


#ዝምታ ከወርቅ በላይ ውድ ነው!

ዝምታን ላወቀበት ጥበብ ነው!
መጥፎ + የማይጠቅም ነገር ከመናገር!
#
ዝም ማለት መልካም/ ኸይር ነው!
ዝምታ በተለይ
#ለሴት ልጂ አስፈላጊ + ክብሯ + ከትላልቅ የውበቷ መገለጫዎች አንዱ ነው!!!
ነገር ግን! ለዚህ የክብር መገጫ
የታደሉት በጣም ትንሾቹ ናቸው!!!

ቻናል:-
https://t.me/ibnuyasir11


➤ሒጃብን ትተው ተራቁተው የሚሄዱ እህቶች ምን አለ አንድ ቀን ለብሰው ጣአሙን ባወቁት በቀመሱት ብዬ ተመኘሁኝ ወላሂ!

➤ሰላም መረጋጋት ሰኪና ደስታ ክብር ሀያእ እዛ ውስጥ ነው ሀቂቃ ለኛ ሴቶች ክብራችን ሂጃባችን ነዉ ሸሪዓውን የጠበቀ ሒጃብ ኒቃብ ከለበስን ማንም ቀና ብሎ አያየንም እንከበራለን

➤ታዳ አላህ ይህን የመሰለ ክብር ሰጥቶን ሲየበቃ ለምን በራሳችን እጅ እንረክሳለን አላሁሙሰተአን ሂጃብሽን ጥለሽ ፋሸን የምትከተይዋ እህቴ አላህን ፍሪና ሸረዓውን የጠበቀ ሒጃብ ልበሺ ፉሽን እያልሽ ከኼራሽንም ዱንያሽንም አታበላሺ::


➤ሒጃብ የለበሳቹ ውድ እህቶቼ አላህ ኢስቲቃማህ የወፍቃቹ ጠንክሩ ምንም ነገር ቢፈጠር በሒጃባቹ እንዳትደራደሩ ሶብሩ!!
➤ላለበሳቹ ደግሞ አላህ ይወፈቃችሁ አላህ ገር ያድርግላችሁ !

➤ሀቂቃ የህን የመሰለ ደስታና ሰላም ሳትቀምሱት ሳታዩት አየምልጣቹ የአላህን ትዛዝ አክብሩ  በምእራብ ፋሽን አትሸወዱ አትሸምገሉ እነሱ እኛን ለማበላሸት ነዉ  ቀን ከለሊት የሚለፋት ከሀቅ መንገድ አንድንወጣ ነው የሚፈልጉት ስለዚህ እህቴ ሙራድቸውን
❨ ፍላጎታቸውን ) አትሙይላቸዉ!!


ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


የዕውቀትን ደረጃ ብናውቅ ተኝተን ባላደርን ነበር

ኢብኑል ቀይም ﺍﻟﻠﻪ ይዘንለት ዕውቀትና ገንዘብ ሲያነፃፅር እንዲህ ይላል

ﺍﻟـْﻌﻠﻢ
ﻣِﻴﺮَﺍﺙ ﺍﻷﻧﺒﻴـﺎﺀ، ﻭَﺍﻟـْﻤَﺎﻝ ﻣِﻴﺮَﺍﺙ ﺍﻟـْﻤُﻠُﻮﻙ ﻭﺍﻷﻏﻨﻴـﺎﺀ
ዕውቀት የነብያቶች ውርስ ነው፣ገንዘብ ደግሞ የሀብታሞችና የነገስታቶች ውርስ
ነው።

ﺍﻟْـﻌﻠﻢ ﻳﺤﺮﺱ ﺻَﺎﺣﺒﻪ ﻭَﺻَﺎﺣﺐ ﺍﻟﻤَﺎﻝ ﻳﺤﺮﺱ ﻣَﺎﻟﻪ .
ዕውቀት ባለቤቱን ይጠብቃል፣ባለ ገንዘብ ግን ገንዘቡን ይጠብቃል።


ﺍﻟـﻤَﺎﻝ ﺗُﺬﻫﺒﻪ ﺍﻟـﻨَّﻔَﻘَﺎﺕ، ﻭَﺍﻟـﻌﻠﻢ ﻳﺰﻛﻮﺍ ﻋﻠﻰ ﺍﻟـﻨَّﻔَﻘَﺔ .
ገንዘብ ወጪ ሲደረግ ይቀንሳል፣ዕውቀት ወጪ ሲደረግበት ይጨምራል
(ይተላለፋል
)
ﺻَﺎﺣﺐ ﺍﻟـﻤَﺎﻝ ﺇِﺫﺍ ﻣَـﺎﺕَ ﻓَﺎﺭﻗﻪ ﻣـَﺎﻟﻪ ﻭَﺍﻟْـﻌﻠﻢ ﻳﺪْﺧﻞ ﻣَﻌَﻪ ﻗَﺒﺮﻩ .
ባለ ገንዘብ ሲሞት ከገንዘቡ ይለያያል፣ባለ ዕውቀት ግን ዕውቀቱ አብሮት ቀብሩ
ይገባል።

ﺍﻟْـﻌﻠﻢ ﺣَﺎﻛﻢ ﻋﻠﻰ ﺍﻟـﻤَﺎﻝ ﻭَﺍﻟـْﻤَﺎﻝ ﻟَﺎ ﻳﺤﻜﻢ ﻋﻠﻰ ﺍﻟـْﻌﻠﻢ .
ዕውቀት ገንዘብ ላይ ይፈርዳል፣ገንዘብ ግን ዕውቀት ላይ አይፈርድም


ﺍﻟـﻤَﺎﻝ ﻳﺤﺼﻞ ﻟِﻠْﻤُﺆﻣﻦِ ﻭَﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮ، ﻭَﺍﻟـْﺒَﺮ ﻭﺍﻟـﻔﺎﺟﺮ ﻭَﺍﻟْـﻌﻠﻢ ﺍﻟـﻨﺎﻓﻊ ﻟَﺎ ﻳﺤﺼﻞ ﺇﻻ ﻟِﻠْﻤُﺆﻣﻦِ .
ገንዘብ ለካፊርም ለሙዕሚንም፣ ለደግም ለአማፂ ሰው ሊኖረው ይችላል፣
ጠቃሚ ዕውቀት ግን ሙዕሚን እንጂ አያገኘውም።

ﺍﻟـْﻌَﺎﻟﻢ ﻳﺤْﺘَﺎﺝ ﺇﻟﻴﻪ ﺍﻟْﻤُﻠُﻮﻙ ﻓَﻤﻦ ﺩﻭﻧﻬﻢ ﻭَﺻَﺎﺣﺐ ﺍﻟـﻤَﺎﻝ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳﺤْﺘَﺎﺝ ﺇﻟﻴﻪ ﺃﻫﻞ ﺍﻟـْﻌَﺪَﻡ
ﻭﺍﻟـﻔﺎﻗﺔ .
ለአዋቂ ሰው ነገስታቶችም ከነሱ በታች ያሉትም ወደሱ ፈላጊ ናቸው፣ ባለ ገንዘብ
ግን ወደሱ ሚፈልጉት ድሆችና ምንም የሌላቸው ናቸው

    قرآني حياتي 

  
ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11     


ቁርአን ብርሀናችን


   ቁርአን ብርሀናችን ጨለማ ገፋፊ
    አማኝን አብስሮ ወደ ጀነት ገፊ

     ቁርአን መሪያችን ለቅኑ ጎዳና
  እርካታንም ሰጪ በርሱ ላይ የፀና

   የነብያት ገድል የዳዕዋ ተራኪ
ያንድነት ሚስጥር ተውሂድን ሰባኪ

  ህግጋቱን ረቂቅ ዘመን  ተሻጋሪ
   ፍትህን ያሟላ  እውነት ተናጋሪ

       ቁርአን🌺🌺ቁርአን🌺🌺

ቻናል:-
https://t.me/ibnuyasir11


💦ዲን ባጣቃላይ ስነ- ምግባር ነው!!
〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰
◾️በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ ።
ምስጋና ለአላህ ይገባው።ሶላትና ሰላም በነብዩ ላይ ይስፈን።
ﻣﺎ ﻣﻌﻨﻰ ﻛﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ : ‏( الدِّينُ كُلُّهُ خُلُقٌ. فَمَنْ زَادَ عَلَيْكَ فِي الْخُلُقِ: زَادَ عَلَيْكَ فِي الدِّينِ ‏) ؟
➲ ‟ዲን፦ ሁሉም ስነብግባር ነው በስነ ምግባር የበለጠህ ሰው በዲን ይበልጥሃል"
የሚለው የኢብኑልቀይም ንግግር ትርጉ ምንድን ነው?

➊  .ዲን" የሚለውን ቃል የአረብኛ ቋንቋ ሊቆች፦
"ስነ ምግባር ፥ባህሪ፥ መታዘዝ፥ አምልኮ፥ መተናነስ፥ኢስላም፥ ሃይማኖት፥ ምንዳ ፥ህግ …" በማለት ተንትነውታል


➋  .ኹሉቅ" የሚለውን ቃል ደግሞ እንዲህ በማለት ተንትነውታል፦ " ባህሪ፥ ስነ ምግባር፥ የክብር ስሜት፥ ሃይማኖት… ˝

ስነ-ምግባር የሚያጠነጥንባቸው አብይ ነጥቦች:-


⓵ . ከአላህ (ሱ·ወ)ጋር ያለ መልካም ስነ-ምግባር፦
ማንኛውም ሙስሊም ከአላህ ጋር ያለውን ግንኙነት (መስተጋብር) ሊያሳምር ይገባዋል ። የአላህን ትዕዛዛት ሊቀበል እና የከለከላቸውን ኃጢአቶች ሊከለከል ግድ ይለዋል የትዕዛዛት ሁሉ ዋና ተውሒድ ነው። ከኃጢአቶች ሁሉ ይበልጥ አደገኛው በአላህ ማጋራት ነው።
ይህ ነጥብ የስነ  - ምግባር ሁሉ መሰረት፣ መነሻና ጥልቁ ነው።

⓶ . ከነብዩ((ጋር ያለ መልካም ስነ-ምግባር ፦
የነብዩን ትዕዛዝ በአክበሮት መቀበል፣ የከለከሉትን መከልከል ባወሩት ማመን እና እርሳቸው በደነገጉት ብቻ አላህን ማምለክ ከነብዩ ጋር ያለ መልካም መሰተጋብር ነው።

⓷ .ከሰዎች ጋር ያለ መልካም ስነ - ምግባር ፦አንድ ሙስሊም ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ያማረ ሊሆን ተገቢ ነው ።
"ስነ-ምግባር ፦ሀብትን መለግስ፣ ከማስቸገር(ከመጉዳት) መታቀብ፣ ሲያስቸግሩት መቻልና ፊትን ፈገግ ማድግ" የሚለው የዑለማዎች ትንታኔ ከዚህ ከሶስታኛው ነጥብ ጋር ተያያዥነት አለው።
ለዚህም ነው፥  ስነ-ምግባር ዲን የሆነው ፤ ዲንም ስነ-ምግባር የሆ ነው ።አንድ ሰው አላህ ያዘዘውን በተገበረ ቁጥር እና የከለከለውን በተከለከለ ጊዜ ስነ- ምግባሩ እያደገና እየጨመረ ይሄዳል።

አንዳድ ሰዎች ይሄን
‏‟ﻣﻘﺎﻟﻲ ﺍﻟﻘﺎﺩﻡ ﺍﻟﺪِّﻳﻦُ ﻛﻠُّﻪ ﺧُﻠﻖ ﻓَﻤﻦ ﻓﺎﻗﻚَ ﻓﻲ ﺍﻟﺨُﻠﻖ ﻓَﻘﺪ ﻓﺎﻗﻚَ ﻓﻲ ﺍﻟﺪِّﻳﻦ ‏،
➲ ‟የሚለውን ንግግር የኢብኑል ቀይም ያደርጉታል ።ግን እኔ  ፈልጌ አላገኘሁትም።
ያገኘሁት ከላይ እንደጠቀስኩት፦

‏‟الدِّينُ كُلُّهُ خُلُقٌ. فَمَنْ زَادَ عَلَيْكَ فِي الْخُلُقِ: زَادَ عَلَيْكَ فِي الدِّينِ ‏،

የሚውን ነው።📔(መዳሪጁ አስ -ሳሊኪን 3/2187) የተሰኘውን መፅሐፉን ማይት ትችላላችሁ።


ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🌸የጧት ዚክር🌸

♦️አስጊና አሰቃቂ አስፈሪ ጨለማ
መብራት የሌለበት ቲንሸየ ሻማ
ማይነጋ መሳይ የሀሳብ ቀጠሮ
በመከጀል ተስፋ ነገን ዛሬ ቋጥሮ
መንጋቱን ታያለክ ባሳብ ተወጥሮ
        ↷ ⇣💎⇣↷
ቀንህን በዚክር ጀምረው

የጧት ዚክር እንዳንረሳ!!
      〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
              
#ፈዘኪር

         
#በሉ አድድድድድ  እያደረጋችሁ

              
               ሰበኸ ኸይር???

                

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.