Bahiru Teka dan repost
👉 በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ መነደፍ
ሙእሚን በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይነደፍም ። እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት ኢኽዋን አሕባሽን በመቃወም ስም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሰላማዊ ትግል ብሎ ዋጋ አስከፍሎታል ። በዚህ ሰላማዊ ትግል ስም ብዙ ወንድሞቻችንን አጥተናል ። አብዛኛዎች የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ። ሌሎች ሀገር ለቀው ተሰደዋል ። ብዙ እህቶች ክብራቸውን አጥተዋል ። አደባባይ ላይ ኒቃብና ጅልባባቸው ጫማ ተጠርጎበት ወደ እሳት ተወርውሯል ። ያለ ምንም ርህራሄ አናታቸው ተሰንጥቋል ። ጥቂት የማይባሉ ተረጋግጠው ህይወታቸውን አጥተዋል ። ከሴት እህቶቻችን ውስጥ አንዷ በጡቶቿ ላይ ኤሌክትሪክ ተለቆባት ደርቃ የሞተች አለች ። ኢኽዋኖች በዚህ መልኩ ዋጋ አስከፍለው መጨረሻ ላይ ከአሕባሽ ጋር አንድ ነን ብለው አሕባሽን አንግሰዋል ። የኋላ ኋላ በመጅሊስ ስልጣን ተጣልተው አይንህ ላፈር ተባብለው ተለያይተዋል ።
ኢኽዋን መጅሊሱን ሲዝ የፈለገ መውሊድ ያውጣ የፈለገ ጫት ይቃም ብሎ የዐቂዳና የአመለካከት ነፃነት አውጇል ። በዚህም ትልቁን ወላእና በራእ የሚለውን እንዲሁም በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል የኢስላም መርህ ንደዋል ። ያ ቁስል ሳይድን ትካዜው ሳይረሳ አሁንም ሙስሊሙን ዋጋ ሊያስከፍሉ ይመስላል ። በመሆኑም ሙስሊሞች ባጠቃላይ ሰለፍዮች በተለይ በየአንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ኢስላም ምን ይላል ብለን ልንጠይቅ ይገባል ።
ድንጋይ በመወረወር ፣ መንገድ በመዝጋት ፣ ንብረት በማውደም በንፁሃን አካልም ሆነ ንብረት ላይ ወሰን በማለፍ የሚጠየቅ መብት የለም ። ገጠርም ይሁን ከተማ የሚደርሱ በደሎች ካሉ መጀመሪያ ወደ አላህ መመለስና በደላችንን ምንም ለማይሰወርበት አምላካችን ማቅረብ ፍትህ ከሱ መጠበቅ ይኖርብናል ። ከዚህ ካለፈ እስከሚቻለው ድረስ በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር ጥያቄ በማቅረብ መብትን መጠየቅ ይቻላል ። መልስ አላገኘሁም ብሎ የሚደረጉ ረብሻዎች ጉዳት እንጂ ጥቅም የላቸውም ። ተጎጂው ደግሞ ሁሌም ምስኪኑ ሙስሊም ማህበረሰብ ነው ። የንቅናቄው መሪዎች ፊት ለፊት ሆነው አይደለም የሚመሩት መመሪያ ሰጥተው መስመሩን ዘርግተው የሚሆነውን ሩቅ ሆነው ነው የሚከታተሉት ። ይህ በተደጋጋሚ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ንቅናቄ ታይቷል ።
እንደ ምሳሌ በ2001 ላይ ሚዛን ቴፒና ወሎ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ተከልክለዋል በሚል የአ/አ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለሶስት ቀን የምግብ ማቆም አድማ እንዲያደርጉና በሶስተኛው ቀን ሁሉም ተማሪ ጁሙዓ ፒያሳ ኑር መስጂድ ሰግዶ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ መመሪያ ተሰጥቶ ሰላማዊ ሰልፉ ተጀምሮ ጥቂት ሳይጓዝ ተማሪው በላእ ወርዶበት ሰማይና ምድር ጠቦት እርስ በርሱ እየተረጋገጠ የወደቀው ወድቆ የተነሳው ቆመጥ እየተቀበለው ሲታመስ መመሪያ ሰጪዎቹ የአ/አ ጥግ ላይ ሰግደው ምን ላይ ደረሰ እያሉ ሲጠይቁ ነበር ።‼
የድምፃችን ይሰማን ንቅናቄ ሲመሩ የነበሩት አብዛኞቹ ኳታር ፣ ካናዳና አሜሪካ ሆነው ነበር ሲመሩ የነበሩት ። በመሆኑም ሙስሊሞች ማን ለምን ተነሱ እንደሚላቸው ሊጠይቁና ሊያውቁ ይገባል ። በስሜት መነዳት በዱንያም በአኼራም ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም ። ያለፈው ይበቃል በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ መነደፍ የለም ።
https://t.me/bahruteka