Janderebaw Media


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአ.አ ሀገረ ስብከት ዕውቅና የተሠጠው የወጣቶች መንፈሳዊ ኅብረት ነው::
የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri






+ 14 ሠዓሊያንን ያሳተፈ የሥዕል ዐውደ ርእይ ተካሔደ +

/አዲስ አበባ : ጥር 02 2014 ዓ.ም./
ጃንደረባው ሚዲያ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከጥር 1-2 2014 ዓ.ም. ያዘጋጀው የሥዕል ዐውደ ርእይ በርካታ ጎብኚዎችን በማስተናገድ በድምቀት ተካሔደ::

ዐሥራ አራት ሠዓሊያንን ባሳተፈው በዚህ ዐውደ ርእይ ላይ የሸራ ሥዕላት : የቆዳ ሥዕላት : የብራና ሥዕላት : የዲጂታል አርት እና የስትሪንግ አርት ሥዕላት : የወረቀት የእርሳስ ሥዕላት : የእንጨት ላይ ሥዕላት ለእይታ ቀርበዋል::

በዐውደ ርእዩ ላይ በክብር ሠዓሊነት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የለንደን ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጥልቅ አባታዊ መልዕክቶችን የያዙ ውብ ሥራዎቻቸው ለጉብኝት ቀርበዋል::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?




+የሕፃናት የገና መርሐግብር በድምቀት ተካሔደ::

/አዲስ አበባ : ጥር 01 2014 ዓ.ም./
ጃንደረባው ሚዲያ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል (ብሥራተ ገብርኤል) ጥር 01 2014 ዓ.ም. ያዘጋጀው የሕፃናት የገና መርሐግብር የመንገድ መዘጋጋትን ምክንያት ሳያደርጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕፃናት በተገኙበት ተካሔደ። በመርሐግብሩም ሕፃናትን እያዝናኑ ሊያስተምሩ የሚችሉ በርካታ ትምህርታዊ ጨዋታዎች የነበሩ ሲሆን ተሳታፊ የነበሩ ሕፃናት በደስታ በመጫወት ስለ ገና በዓል እውቀት ሲጨብጡ ውለዋል።


'የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?' ሐዋ. 8፥36




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መልካም የገና በዓል


ልጆች ወደ ተወለደው ሕፃን ይዘው ይምጡ!

የመስቀልን በዓል "የልጆች ደመራ" በድምቀት ያካሔደው የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የፊታችን ጥር 1 2014 ዓ.ም. ሁለተኛውን "የሕፃናት ገና በዓል" በሚል ያካሒዳል:: በዝግጅቱ ላይ ልጆች የጌታን ልደት በትምህርት በዝማሬና በበርካታ ትምህርታዊ ጨዋታዎች የሚያከብሩ ሲሆን ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮችም ተዘጋጅተዋል:: በብዙ ድካምና በከፍተኛ ወጪ በተዘጋጀው በዚህ መንፈሳዊ ድግስ ላይ ልጆችዎን ይዘው እንዲገኙ ተጠርተዋል::


የፊታችን እሑድ የት ሊሔዱ አስበዋል?

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከብፁዓን አበው ጀምሮ ታላላቅ ሠዓሊያንን ያሳተፈ ልዩ የሥዕል ዐውደ ርእይ አዘጋጅቶአል::

"ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው"
መክ. 3:11



10 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

2 441

obunachilar
Kanal statistikasi