Thoughts


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም?
Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1
comment for the writer : @nhymn
Since: Dec-10-2022
discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 dan repost
Me and my bestie🙄🤷‍♀


"ኧረ ቸግሮኛል...ቀጥሮኝ እኮ መሳፈሪያ ስለሌለኝ ቀረሁ..."

"ካካካ አንቺ ችጋራም ምን ብለሽው ቀረሽ..."

"ከፋሚሊ ጋር ልዝናና ነው እኔ ከሌለሁ ይደብራቸዋል...."

"ካካካካ አንቺ ጉደኛ..."

"ምን አባሽ እውነቴን እኮ ነው..."

"እንዴት...."

"ከፋሚሊ ጋር ነኝ...መዝናናቱ ብቻ ነው የቀረን..."

"አንቺ እውነትሽን እኮ ነው😳...."



✍Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka




Lucky charms☘️🌪️ dan repost
ከልጅነቴ ጀምሮ ወጥ ባህሪ ኖሮኝ አያውቅም...I was either ያቺ ቀዥቃዣዋ ልጅ or ፈሪዋ ልጅ🙂
I try to cover it with "lol I might have ADHD or sumn" but A part of me knew this was going to happen,I had the feeling which I knew I wouldn't transition well in to adult life and that I'd fall in to the cracks of my wounds and traumas.
People don't know the depth of the loneliness I feel,ጎደኞች ስለሌሉኝ ምናምን አይደለም but my feelings are a little ( okay a lot) alienated from other people.
I don't know how to keep things mild,I feel things intensely,i hate,I love, I overwork intensely ብቻ ማድበስበስ አልችልበትም።
But that doesn't necessarily mean አቅልዬ ላየሁት ነገር ግድ አይሰጠኝም , unfortunately life has taught me the stronger i hold on to something the quicker it tends to slip out of my hands so I repress my stronger desire and that hurts(a lot)
የሆነ ነገር ፈልጌ ሳገኝ ደስታ አቅሌን እንደሚያስተኝ ሁሉ የኔ የሆነን ነገር ሳጣ ደግሞ physically እስኪያመኝ ድረስ feel አደርጋለው,
አንቅሮ መትፋት ወይም አጥብቆ መያዝ እንጂ playing around isn't something my brain is used to.


Just thoughts.... dan repost
Little sis

We shared parents
And they raised me first
They way they were raised
I know they wanted
To be a better version
Of their own parent
But it wasn't enough
And i needed
Healthier relation
I was figuring out
What was wrong
The way i was raised
And before i finished
Articulating the did
And found out
What i must be
You were born
And i saw you
Being raised like me
I know whats wrong
But didn't do anything
To stop you from it
And grow u healthy
Sis, i am sorry
If my self i am
Better just a little bit
I just saw you growing
Having same trauma
like me
I am sorry sissy
Even though the the first born
Or the eldest one
i am still the daughter
Who didn't figure everything out
Yet.


እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት?
#8

ትዕግስት እና ባህሩ የሁሉንም ታሪክ እየሰሙ እየጠጡ እያለ ሳባ ዞረችና "ቆይ የሰውን እየሰሙ ግፍ አይሆንባችሁም?! በይ ቲጂ ተናገሪ አንፋታችሁም" ስትል ሁሉም "አዎ... አዎ" ብለው ተስተካክለው ወደ እነሱ ዞረው ተቀመጡ "የሚወራ የተለየ ነገር ስሌለው እኮ ነው" ብላ ዝም አለች ኧረ እንዴ ተንጫጫንባቸው

"እሺ እኔ እነግራችኋለሁ ግን ብዙ drama እንዳትጠብቁ ቲጂ እንዳለችው ነው የሚወራ ነገር የለውም።' ብሎ ባህሩ ቀጠለ መቼም ሰፍ ብለን አፉ ጋር ደርሰናል።

"ተዋወቅን ...ስንተዋወቅ "she is the one" የሚል ስሜት አልተሰማኝም ወይም ብቻ.... እንደማንኛውም ሰው ነው የተዋወቅነው ዩኒቨርሲቲ መጨረሻ አመት ላይ ነው አንድ ክፍል መሆናችንን ራሱ ያወቅኩት በresearch ሰበብ ጊዜ ስናሳልፍ እየተዋወቅን መጣን

እውነት ለመናገር ጓደኝነታችን ያመዝን ነበረ። ለዛ ነው እንደምትጠብቁት አይነት አይደለንም ያልኳችሁ። ከጓደኝነት የዘለለ ግንኙነት ስንጀምርም ተነጋግረን ወሰነን ነው እንጂ "በፍቅር ወድቀን" አይደለም ወይም ደግሞ ከሷ ጋር ስሆን የልብ ምቴ ስለሚዘባረቅ አይደለም ወይ "ቀልቤን ወስዳው" የለተለት ኑሮዬን አመሰቃቅላው አይደለም።

እንደውም የምመኘውን መረጋጋት እሷ ጋር ስለማገኘው ነው አብሬያት ነገዬን ማቀድ ስለምችል ነው አምኜበት ወስኜ የወደድኳት እንጂ ድንገት ከእንቅልፌ ስነቃ "ልቤን ከቦታዋ አጥቻት" አይደለም

ጉሮሮዋን እንደነገሩ ጠራርጋ

እኔም ብሆን ከሰው ተራ አውጥቶኝ ብዬ አላለቃቀስኩም ወይም ምግብ ትቼ ምናምና በየመፅሀፍ እና ፊልም ላይ እንደምናየው አልተቀያየርኩም እንደውም ራሴን የምጠብቅበት ሌላ ምክንያት ነው ያገኘሁት እና እንደምትጠብቁት አይነት ታሪክ ስላልሆነ ልንረዳችሁ አንችልም ብለው እጃቸውን ተያያዙ

ምንም ቃል የለኝም ቺርስ አለች ሳባ ብዙ ቺርሶች ተከተሉ


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss




Sost Kilo dan repost


Just thoughts.... dan repost
I pretended to enjoy rap
Or some classical sound
Forced myself for jazz with frantic sax
And then i was saying Music is savor
From a chaotic thought
But the truth was I was just looking
For a comfort In music
Where it truly Was found
Only in your hug



✍nani


Just thoughts.... dan repost
When you are worried
About your mental state
They will mock you
Since you are just a teen
From a poor country
And who cared about
Your mentality?
Are you allowed
To be depressed?
Since its not in your domain
Its problem of the western
Its for the riches Right?!
And then they call you
Dramatic
Over reacting
Creating problem
That never existed
But you know
They exist
And when you say
You are healing yourself
They will all laugh
Cause they don't know
How to be aware of one self
Because mental health
Its kind of abstract
Can't be seen with eyes
Cause its not
some kind of illness
With blood and sores
But one day
we hear the shootings
endless and pointless wars
Just to satisfy "ego" of the leaders
Or unhealed inferiority complex
they say its not personal, politics
But man, hell... it is
And the war, its reasons
You won't find it, in history books
But their neglected childhood
And even now
They always have the budget
Or can get a debt
to buy bombs and pistol
And we, the people
We don't have time
To fix our mindset
And to heal our inner child
Instead we ignore it
Until it burst
And we can't contoll it
So what is wrong with it
Giving yourself time
To heal your inner child
What is wrong with it?


✍nani


Open reading 🕊⃤ dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
📹 ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል አንድ

▬▬▬▬▬▬▬▬  ▬▬▬▬▬▬▬▬
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

◎ የኢትዮጵያ አንባቢዎች ማህበር!
📚 የመጽሐፍት አፍቃሪያን ህብረት!

- https://t.me/Open_reading1
- https://t.me/Open_reading1


ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 dan repost
ዶሮ ሳልበላማ እንዲች ብዬ አልፅፍም ብዬ እኮ ነው ያረፈድኩት🙄 አሁን ልመርቅ ነው አሜን በሉ.....✨✨


መከፋታችሁን ውጣችሁ በግርድፉ "ደህና ነኝ" የማትሉበት እና ከምርም ደህና የምትሆኑበት አመት ይሁንላችሁ....

የምትወዷቸው ይቆዩላችሁ...

ከትራሳችሁ ጋር አፋችሁን አፍናችሁ የማታለቅሱበት አመት ይሁን....

አካሄዳችሁን ከፈጣሪያችሁ ጋር የምታደርጉበት አመት ይሁንላችሁ...አካሄዳችሁ ከእሱ ጋር ከሆነ ሌላው ከመከተል ውጪ አማራጭ እንደሌለው እያስታወሳችሁ የምትራመዱበት አመት ይሁን.......

ፈጣሪ የውስጣችሁን ማዕበል ይገስፅላችሁ...ሰላማችሁ የሚወሰነው በእርሱ ስለሆነ...

ልባችሁ ይስከንላችሁ...'ሁሉ አማረሽን...'...የተባለለት ልባችሁ አደቡን የሚገዛበት አመት ይሁን.....

የታመማችሁ ፈጣሪ ይዳብሳችሁ....

ከምንም በላይ ዋናው የሀገር ሰላም ነውና ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን...ጥሩ ነገር ያሰማን....

እና ተወዳጆች አንድ መልዕክት አለኝ....

    "ነገን አትመኑ...ዛሬን ከልብ ኑሩ....ለምትወዱት ሰው ዛሬ እንደምትወዱት ንገሩት...ማግኘት የምትፈልጉትን ሰው ዛሬ አግኙ ....ማቀፍ የፈለጋችሁትን ዛሬ እቀፉ...'ነገ' ቃል አባይ ነው ብዙም አትመኑት...በተረፈ ሁሉም ያልፋልና እጅ አትስጡ...."



መልካም ጅማሮ😊



✍Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka


My dear people,
እንኳን አደረሰን ምክንያቱም መድረስ ቀላል አይደለም መድረስ ፈልገው ያልቻሉ አሉና መድረሳችንን አቅልለን አንየው

የእንቁጣጣሽ እና የመስከረም ነገር ሁሌም ይገርመኛል ተፍጥሮ ራሷ የሆነ መንቃቃት የቀዘቀዘ ወኔያችንን መቆስቆስ ትጀምራለች

እንቁጣጣሽ ከሌላው በአል በተለየ የሆነ ውሉ ያልታወቀ ተስፋ ውስጣችን ያጭራል መስከረምም ከሌላው ወር በተለየ የለውጥ እቅዶች ይታቀድበታል

አምና ያቀድነውን አሳካንም አላሳካንም ለቀጣዩ አመት ደርሰናል ፈጣሪ እስከፈቀደውም ብዙ እንቁጣጣሽ እናከብራለን ብቻ ግን የማቀድ ሞራላችን እንዳይጠፋ ፀልዩ ሰውን የሚያኖረው ለነገ ያለው ጉጉት አይደል?!

እና ደግሞ ያቀድኩት በሙሉ ለምን አልሆነም ብሎ ማለቀቀስም ተገቢ አይመስለኝም ምክንያቱም ሰው ስኬቱን ብቻ ስላልሆነ

ያም ሆነ ይህ እንኳን አደረሰን ፀሎታችን የሚሰማበት አመት የግለሰብም የሀገርም ብዙ ደስታ የሚስተናገድበት ያድርግልን

ያው ፆምም ቢሆን ነገ ዋዜማው ይበልጣል እያንድንዷ ደቂቃ ተስምታችሁ ትለፍ...


✍ናኒ


𝙄𝙣𝙣𝙚𝙧 𝙥𝙚𝙖𝙘𝙚 𝙩𝙖𝙡𝙠𝙨🖤. dan repost
Fuck የ አዲስ አመት እቅድ አንደዛ እያልን ለስንፍናችን excuse አንስጥ ለውጥ የሚጀምረው ከዛሬ ነው!

Anyway እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🥳


ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 dan repost
ሰርግ ላይ ነበር የተዋወቅነው....ያኔ ድንኳን መስበር ቀላል በነበረበት ጊዜ ነበር ያወቅኩት...ከጓደኛዬ ጋር ዘንጠን ሰርገኛ መስለን እልል እያልን ገብተን ነው ያፈስኩት...

"ደስ ይላል ......"....ብሎ ወንድሙ ጂራ ሲጀምር "ሙሽሮቹን ሞቅ አርጉላቸው..."....እያለ ጭብጨባ አዋጡ ከሚለው ዲጄ ፊት እሱ አለ.....የሰርጉ ካሜራ ማን ነበር....

ድል ያለ ሰርግ ላይ ታዳሚ እንደመሆን ደስ የሚል ነገር ምን አለ...መብላት.... መጠጣት... መጨፈር....አለቀ የታዳሚ ስራው ይሄ ነው...የሙሽሮችን ደስታ መጋራት እና ሰርጉን ማሞቅ እንዳለ ሆኖ ነው የምላችሁ....

ካሜራውን ይዞ ፊቴ ድቅን ሲል ነብስ ከስጋዬ ተላቆ ነበር....እየበላሁ ነበር....እውነቱን ለመናገር ያነሳሁት ቡፌ  ከኪሎዬ ይበልጥ ስለነበር ነው የደነገጥኩት....

መደንገጤን እና ሳሀኔን አይቶ መሰለኝ ፈገግ ነገር አለ...ሲስቅ ያምራል...እዚህ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ደነገጥኩ...የሆነ የሚያረጋጋ ፈገግታ ነው ያለው...እንደፈገገ ካሜራውን ወደ ሙሽሮች አዞረ...አንገቴ እስኪጣመም ድረስ አብሬው ዞርኩኝ....ይባስ ብዬ ምግቤን ጥዬ እከታተለው ገባሁ ....ጉደኛ አይደል የቆልኩት ሳሀኔን አስረሳኝ.......


የጓደኛዬ አስተያየት አሁንም ድረስ አይኔ ላይ አለ...."ወይ ኪራ በምግብ አሰጨከንካት እኮ...."....ትላለች ሁኔታውን ስታስታውስ....

"አበላሏን አይቼ እኮ ነው ድጋሚ ልቀርፅ እሷ አካባቢ ዝር ያላልኩት....እንኳን የሸመተ ካካካካ...."....ተጋግዘው ቀንድ ያስበቅሉኛል....


የሰርግ አዳራሽ ውስጥ የሆነ መንፈስ እንዳለ ግልፅ ነው.... አዎ አግቡ አግቡ የሚል መንፈስ....በየዘፈኑ መሀል የዛ ፈገግታ ባለቤት ካሜራ ማን በመሆኑ እየተበሳጨሁ ነበር...ምናል ታዳሚ ወይ ድንኳን ሰባሪ ቢሆንና በጠጥቼ ነው ሰበብ ደረቱ ላይ ብለጠፍ ምን ነበር....


አላለቀም...



✍Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka




እንማር dan repost
የ12ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ይፋ ይሆናል።ልክ እንደተለቀቀ ኮዳችሁን ለእኛ በመስጠት ውጤታችሁን በዚህ ቻናል በኩል ማረጋገጥ ትችላላችሁ።ከ20 በላይ አድሚኖች እናትን ለመርዳት ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ ነው።መልካም ዕድል!

👇👇
https://t.me/Temaricom
https://t.me/Temaricom


My dear 12 grades, i wish u luck for the longest day, tomorrow, may God give you the strength to accept whatever is coming🙌🙌

ነገሮች የሚሆኑት ለምክንያት መሆኑን እና ለመጪው ያልተገደበ አማራጭ ያለውን ወደፊት አስባችሁ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ ፈጣሪ ይርዳችሁ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish




✨ተተክተሻል✨

ደውዬ የልጄ ክርስትና እናት እንድትሆን ጠይቄያት 'እሺ' ስትል ፈገግ አልኩ በቀሉን እንዳገኘ ሰው ውስጤ ደስታ ሲናኝ ተሰማኝ። ለእሷ ብዬ ያስቀመጥኩት ትልቅ ቅርበት ለአዲሷ ጓደኛዬ እንደሰጠሁት ባወቀች ብዬ ተመኘሁ

ከዛ ለሰርጓ የተነሳነውን ፎቶ አገላብጬ አየሁት የመጀመሪያ ሚዜዋ እንደመሆኔ አጠገቧ ነኝ ሁሉም ፎቶ ላይ "የኔ ብቻ ሚዜ ነው የምትሆኚው ያውም የመጀመሪያ" እንዳላልሽኝ ድራሽሽ ሲጠፋ አለመፈለጌን(ይጠብቃል) በይፋ ስታሳዪኝ የመጀመሪያ ሚዜ የሆንኩት ከወር በፊት እንደሆነ በምን አባቴ ላሳይሽ?!

ገና highschool እያለን እንዴት አብረን እንደምናረጅ፣ ልጆቻችንን ጓደኛሞች አድርገን ባህላችንን እንደምናስቀጥል አብረን እንዳላወራን፣ የወንድ ምርጫችን አራምባና ቆቦ ስለሆነ መቼም ባሎቻችን እንደማይግባቡ ገና አስበን እንዳላዘንን፣ የሰርግ ቀሚሶቻችንን እስከ ልጆቻችን ምርቃት እንዳላቀድን..

Telegram ላይ ሳምንት አውርተሽው እንደምትተዪው ልጅ የስድስት አመት ጓደኝነት እንደቀልድ ትውት ስታደርጊው ምን እንደተሰማኝ ታውቂያለሽ?

አለመፈለግን በደማቁ አስተናገድኩት ከዛ ብቸኝነትን ለመልመድ መጣጣር ያንን ለሰፈር ሰው የሚበቃ ሳቄን እንዴት መቆጠብ እንዳለብኝ ራሴን ማስተማር ነበረብኝ

አለማውራት እንደማልችል ታውቂያለሽ፤ ሚስጥር መያዝም እንደዛው ግን ደግሞ ከስህተቴ መማር ስለነበረብኝ አፌን መሰብሰብ፥ ራሴን መቆጣት አስተማርሺኝ ሰው መፈለግ፥ emotionally dependent መሆን ነውር አደረግሽብኝ "ኧረ ቆምጠጥ ማለት ልመጂ አታዋርጂኝ" ብሎ አዕምሮዬ ልቤን እንዲያምባርቅባት አደረግሽ

በዚህ ቢበቃሽ መች አነሰ?! በረባ ባረባው ሆድ ሲብሰኝ ያንቺ መሄድ ነው ጭንቅላቴ ላይ የሚጎላው ከዛ እንደልማዴ ራሴን እወቅሳለሁ "ይሄንን ባልላት ኖሮ... ባላናድዳት ኖሮ" ምናምን እያልኩ አመታት ያለፈውን እያስታወስኩ ራሴን እወቅሳለሁ

ከዛ የመጨረሻ ያጎሳቆልሺኝ ሰዎችን መቅረብ እንድፈራ ስታደርጊ ነው በቃ ያኔ መበሳጨት ጀመርኩ "ማን ስለሆነች ነው ቆይ ይሄ ሁሉ ይገባታል?! ወይስ የኔ መሄዷን አምኖ የሚቀበል ጠንካራ አስተሳሰብ ማጣት ነው?!" እያልኩ ራሴን ደጋግሜ መገሰፅ ጀመርኩ

በዚ መሀል አዲሷ ጓደኛዬን አገኘኋት... መጀመሪያ ፈርቼ ነበር እንዳንቺ ድንገት ተንስታ እልም ብትል ለማን እዬዬ ልል ነው ብዬ እሷ ግን እንዳንቺ የተወሳሰበች አልነበረችም የወሰድሽውን እምነቴን መለሰችው ያልፈጠረብኝን ግልፅነት አስለመደቺኝ ፈጣጣ ሆንኩ ድጋሜ ደውዬ መነፋረቅን normal አደረግኩት እድሜ ለሷ my color ተመልሷል

እናላችሁ ስታገኟት
በናታችሁ ንግሯት
ይብላኝ ላንቺ እንጂ
እሷ ተክታሻለች በሏት

✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.