ከማዛሮት መጽሐፌ የተወሰደ
💥 ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ እንደገለጸው ውሃን የመሳብ ከፍተኛ ዐቅም ያላት ጨረቃ በእኛ ውስጥ ያለውንም ከፍተኛ የውሃ መጠን በመሳብ የውስጣችን ውሃ ማዕበልነት ታስነሣለች፡፡
💥በተለይ በጠፍ ጨረቃ (new moon) እና ሙሉ ጨረቃ (full moon) በምትሆንበት ጊዜ አእምሯቸው የታወከ ሰዎች በሚታከሙበት ሆስፒታል የሚሠሩ ሐኪሞች ሕመምተኞቹ እንደሚረበሹ፣ እንደሚቅበጠበጡ በስፋት ይገልጣሉ፡፡
💥 በዚህ ምክንያት የአእምሮ ሕመምተኛ “ሉናቲክ” ይባላል፡፡ “ሉና” ማለት በላቲን ጨረቃ ማለት ሲሆን ሕመማቸው የበለጠ በሙሉ ጨረቃ ጊዜ የሚጐላ መሆኑን ለማሳየት ከጥንት ጀምሮ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡
💥 ለዚህ ነው የኢትዮጵያ መተርጒማን ሊቃውንት ምልአተ ወርኅ (ጨረቃ ሙሉ) ስትሆን ደም ይመላል፣ ብርድ ብርድ ይላል፣ ደዌ ይቀሰቀሳል በማለት የጻፉት፡፡
💥 በ2011 “ዎርልድ ጆርናል ኦፍ ሰርጀሪ” ላይ የቀረበ ጥናት 40 ፐርሰንት የሕክምና ኀላፊዎች “የሙሉ ጨረቃ ዕብደት” (ፉል ሙን ማድነስ) በሕመምተኞች ላይ እንደሚከሰት እንደሚያምኑ ሲገልጽ የአደጋ ጊዜ ስልክ ጥሪዎችም በሙሉ ጨረቃ ጊዜ 3 ፐርሰንት ሲጨምሩ በጠፍ ጨረቃ ጊዜ ደግሞ 6 ፐርሰንት ይቀንሳል ይላል፡፡
💥 በ2008 ላይ የብሪቲሽ አጥኚዎች የጨረቃ ዑደትና ዶክተሮች እንዴት ሕመምተኞችን እንደሚያዩ በዘረዘሩበት ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ “ሜዲካሊ አንኤክስፕሌንድ ስትሮክ ሲምተምስ” በማለት በህክምና ሊገለጽ የማይችል ሕመምተኞች በሙሉ ጨረቃ ጊዜ የራስ ሕመም፣ የድንዛዜ ስሜት፣ ያመናል ይላሉ፤ ሲመረመሩ ግን በነርሱ ሰውነት ላይ ግን ምንም ችግር የለም፡፡ ይህ በሕክምናው ይህ ነው ተብሎ የማይገለጥ መልስ የለሽ ነው የሚል አስተያየት ተገልጧል፡፡
💥 ከልብ ጋር በተያያዘ ከላይ እንደተገለጸው በአንጎላችንና ልባችን የያዘው ውሃ መጠን → 73% ነውና “Indian Journal of basic and applied research” ላይ የወጣው ጽሑፍ በጠፍ ጨረቃና በሙሉ ጨረቃ ጊዜ ልብህ የመጨረሻ የአፈጻጸም ብቃት ላይ ስለሚሆን ስለዚህ ወደ ስፓርት መሥሪያ (ወደ ጂም) ከመሄድህ በፊት ጨረቃ ያለችበትን ሰሌዳ አረጋግጥ ይላል፡፡ ምክንያቱም ሰውነታችን ውስጥ ያለውን ውሃ በመሳብ የውስጣችንን ማዕበል የምታስነሣ በመሆኗ፡፡
[የድንዛዜ ዘመን እያበቃ ነውና ለራሶ ሲሉ ማዛሮትን ያንብቡ።]