Draft Registration and Licensing Directive - 01.25.2014.docx
በአገራችን በ1952 ዓ.ም. ወጥቶ ለረዥም ጊዜ ሥራ ላይ የነበረው የንግድ ሕግ በዘርፉ ካለው ለውጥና ዕድገት ጋር እንዲጣጣም ባለፈው ዓመት በአዲስ መልክ በአዋጅ ቁ 1243/2013 ሆኖ እንዲወጣና ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። በሚኒስቴር መ/ቤታችን በኩልም የንግድ ሕጉ ያመጣቸውን ለውጦች ታሳቢ በማድረግ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 52 ንዑስ አንቀጽ 2 እና በንግድ ሕጉ የመግቢያ ድንጋጌ አንቀጽ 5 መሠረት የተሻሻል የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ረቂቅ ተዘጋጅቷል።