⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖ dan repost
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ህጉ በሰበር መዝገብ
***
የሰ/መ/ቁ. 214192 ( ያልታተመ) ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞኪራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት እና ተጠሪነታቸዉ ለፌዴራል መንግስት የሆነዉ አስፈፃሚ አካላት የሚያወጧቸዉ መመሪያዎች መከተል ያለባቸዉን መርሆዎች እና ሥርዓቶች፣ አንድ መመሪያ ተገቢዉን ሥርዓት ተከትሎ አልወጣም የሚል ማንኛዉም ጉዳዩ የሚመለከተዉ ሰዉ መመሪያዉ እንዲከለስ ዳኝነት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል እና የዳኝነት ጥያቄዉ የቀረበለት ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ዉሳኔ ወሰኑ እስከምን ድረስ አንደሆነ ይደነግጋል፡፡
አዋጁ እነዚህንና መሰል ድንጋጌዎችን እንዲያካትት የተደረገበት ምክንያትም የሚመለከተዉ የአስፈፃሚ አካል የሚያወጣዉ መመሪያ ግልጽ የሆኑ ሥነ ሥርዓቶችን ተከትሎ እንዲወጣ እና ይህን ሥርዓት ተከትሎ ያልወጣ ከሆነ ከነግድፈቱ ተፈፃሚ ሆኖ እንዳይቀጥል በማድረግ መንግስታዊ አሠራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እና በመመሪያዎች አወጣጥ መርሆዎች እና ሥነ ስርዓት ላይ ቅሬታ ያለዉ ሰዉ የመመሪያዎቹን ህጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓትን በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትሕ ማስፈን ነዉ የሚለዉን የአዋጁን አንዱ ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ እንዲቻል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡
በፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር - ነሀሴ 2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ የበላይ ከሆኑ ህጎች ጋር ይቃረናል የሚሉት የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያወጣውን መመሪያ ሲሆን ይህ መመሪያ በራሱ መመሪያ ከመሆኑ አንፃር ነሐሴ 2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ በእርከን ከመመሪያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ህጎች ጋር አይቃረንም፤ ይህ መመሪያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያልተመዘገበ እና በተጠሪ ተቋም ድህረ-ገጽ ላይ ያልተጫነ በመሆኑ በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 18 መሰረት ተፈፃሚነት የሌለዉ አዲስ የመመሪያ አወጣጥ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ ተጠሪ መመሪያዉን እንደ አዲስ ሊያወጣ ይገባል ካለ በኋላ፣ አመልካቾች ያቀረቡትን የካሳ እና የምደባ ይስተካከልልን ጥያቄን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡
አዋጁ የመመሪያዉ መሻር ቀደም ሲል በመመሪያዉ መሰረት የተሰጠዉን አስተዳደራዊ ዉሳኔ የመሻር ዉጤት እንደሌለዉ ከላይ በተመለከተዉ አንቀጽ 57(4) ላይ የደነገገበት አንዱ ምክንያት ሊሆን የሚችለዉም እንደየጉዳዩ ባህርይ አንድ የአስተዳደር አካል በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ቅሬታ የሚቀርብበት አካል እና የአቀራረብ ሥርዓቱን በተመለከተ በሌሎች ህጎች ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንዲከበሩ እና የአንድ አስተዳደር አካል ዉሳኔ ህጋዊነት በሁለት የተለያዩ አካላት ሊታዩ የሚችሉበትን ሁኔታ እንዳይኖር ለማድረግም ጭምር እንደሆነ ይታመናል።
#ዳንኤል ፍቃዱ