የመንግስት መስሪያ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ አለመክፈል የህግ መሰረት አለው?
***
በዳንኤል ፍቃዱ ( የህግ አማካሪና ጠበቃ)
የመንግስት መስሪያ ቤቶች በፍርድ ቤትም ሆነ ሌሎች የዳኝነት ስልጣን ( ከፊል የዳኝነት ስልጣን/ Semi-Judicial power/) ባላቸው ተቃማት ጉዳያቸውን ሲያቀርቡ የዳኝነት ክፍያ ከፍለው እንደማያቀርቡ ይታወቃል። ከነሱም አልፎ ይህ መብታቸው ተለጥጦ አትራፊ የሆኑ የልማት ድርጅቶች ጭምር የዳኝነት ክፍያ ሳይፈፅሙ ጉዳያቸው የሚስተናገድበት ሁኔታ ይስተዋላል( አሁን አሁን መክፈል ቢጀምሩም) ። ብዙዎች ከመንግስት ለመንግስት መክፈል ማለት ክግራ ኪስ አውጥቶ ወደ ቀኝ ኪስ መክተት ማለት ስለሆነ መክፈል አይጠበቅባቸውም የሚል አመክንዮን ያቀርባሉ።
ለመሆኑ ይህ በተግባር ሲፈፀም የኖረ ልማዳዊ ድርጊት የህግ መሰረት አለው? የፍታብሄር ስነስርአት ህጉ ወይም የዳኝነት አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ የወጡ ህጎችስ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል የለባቸውም የሚል ድንጋጌ አካተዋል? ወይስ ከቀኝ ወደ ግራ ኪስ የሚለው አመክንዮ አሳማኝ ምክንያት ሆኖ ነው?
ለተግባሩ መሰረት የሆነው የፍታብሄር ስነስርአት ህጉ ወይም የዳኝነት ክፍያ አገልግሎትን በተመለከተ የወጡ ህጎች ወይም ሌሎች ህጎች ሳይሆኑ እኤአ ከሕዳር 1974 – የካቲት 1977 ዓ.ም. የደርግ መንግስት ሊቀመንበር የነበሩት ብርጋዴር ጄነራል ተፈሪ በንቲ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ ሳይከፍሉ ክስ እንዲያቀርቡ በሚል ያስተላለፉትን ትዕዛዝ ተከትሎ የመጣ አሰራር ነው።
” ይህ ትእዛዝ በፍርድ ቤቶች የሚኖረውን ተቀባይነት ስንመዝን እንዲህ ያለውን ደንብ ( በጊዜው)* ለማውጣት ሥልጣን ያለው ፍርድ ሚኒስትሩ እንጂ ለሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ( አልነበረም)* / የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 483/ ። ስለሆነም ትዕዛዙ የህግ መሰረት ያለው አይደለም። የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እንዲህ ያለ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚታመንበት ከሆነ በዚህ ረገድ ህግ (አውጪው ከክፍያ ነፃ)* Exemption ን በህጉ እንዲካተት ማድረግ ይገባው ነበር ። ይህ አለመሆኑ ለውዝግብ በር የሚከፍት ይሆናል።” 1
ለውዝግብ በር ከመክፈት በተጨማሪም እነዚህ የመንግስት መስሪይ ቤቶች እና አንዳንድ የልማት ድርጅቶች ክፍያ ስለማይጠየቁ የበዛ ክስ እየመሰረቱ እና ይግባኝ ያለገደብ እየጠየቁ የፍርድ ቤትን ጊዜ እና ገንዘብ እያባከኑ ይገኛሉ። ስለሆነም የፍርድ ቤቶቹ ሃላፊዎች እና ሊያስቡበት ይገባል።
በተጨማሪም ከነዚህ ተቋማት ጋር በክርክር በተቃራኒ ሆኖ እሚከራከር ተከራካሪ እንዲሁም ዳኞች እና የፍርድ ቤት እሚመለከታቸው አካላት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 207 ፣ 211(2) እና 215 መሰረት የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ እና ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ እንዲከፍሉ ማድረግ ያስፈልጋል።
ማጠቃለያ
ከተለያዩ ሃገሮች ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው የፍርድ ቤት ክፍያ መክፈል የለባቸውም የሚሏቸውን የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ የአስተዳደር አካላትን በህጋቸው አካተው ከክፍያ ነፃ ያደርጓቸዋል ። ይህ መሆኑ ወጥ የሆነ የህግ አተገባበር እንዲኖር ይረዳል። ስለሆነም የሚመለከተው አካል ህጉን ሲያሻሽል እዚህ ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ከፉይ እንዲሆኑ ወይም እንዳይሆን ወጥ የሆነ ድንጋጌን ሊያሰፍር ይገባል።
* ቅንፍ የተጨመረ
ፀጋዬ ወርቅ አገኘሁ፣ የዳኝነት ክፍያ አፈፃፀም እና የኪሳራና የወጪ አከፋፈል፣ ህዳር 2001 ዓ.ም.
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሠ/መ/ቁያቀርባሉ።
52 ( ቅፅ 1)
3.የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሠ/መ/ቁጥር 46281 ( ቅፅ 12)