#ልሳነ_ግዕዝ (የግዕዝ ቋንቋ)
#መግቢያ
ቋንቋ የመግባቢያ ዘዴ ከመሆኑ ባሻገር በጽሐፍም ደረጃ አንድን ማኀበረሰብ ከሌላው ጋር ሊያግባባ፣ ሊያዛምድና ሊያስተሳስር የሚችል መሳሪያ ነው ። በዓለም ላይ በሺህ የሚቆጠሩ ቋንቋዎች መኖራቸው ይታወቃል ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የግዕዝ ቋንቋ ነው ። #ግዕዝ የሚለው ቃል የተገኘው #አግዐዘ ከተሰኘው ግስ ሲሆን የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ። እነርሱም መጀመሪያ ፣ የቋንቋ ስም ፣ የፊደል ስም ፣ የንባብ ስም ፣ የዜማ አይነት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ቋንቋው #የአግዓዝያን ቋንቋ ነው ። #አግዓዝያን ማለት የሚያጉዙና የሚጓዙ ተሰደው ፣ ተጉዘው የመጡ ስደተኞች ፣ ባለብዙ ጓዞች በማለት ከሌላ አገር የመጡ መሆናቸውን ይገልጻል። አንድም #አግአዝያን ማለት ነጻ አውጪዎች ከመገዛትም ነጻ የሆኑ ሕዝቦች ማለት ነው ። እነዚህ የሴም ወገኖች ነገደ ዮቅጣን ራሳቸውን አግዓዚ ብለው የሰየሙ ክፍሎች ከደቡብ ዐረቢያ ግዕዝ ከተባለ አካባቢ ተነስተው ዛሬ በኢትዮጵያ ትግራይ ፡ትግረ በተባለው ስፍራ እንደሰፈሩ የታሪክ ድርሳናት ይነግሩናል። #አግዓዝያን የኩሽን መንግስት በጦርነት ድል ነስተው በነገሱ ጊዜ በነገዳቸው ስም ግዕዝ ቋንቋቸው አብሮ ነግሷል ። የመንግስታቸው የስራ ቋንቋም እንዲሆን አድርገውታል ።ከላይ እንደተጠቀሰው ነገደ ዮቅጣን ራሳቸውን #አግዓዝያን ብለው ጠሩት ። ይህንንም ያሉበት ም/ት ለኩሽ መንግስት ከማስገዛት ነጻ መውጣት እና በነፃነት የሚኖሩ ወገኖች መሆን ስለፈለጉ ራሳቸውን #አግዓዚ በማለት ሰይመዋል ። ነገደ ዮቅጣን ፊደልንና አኀዝን በመቅረጽ፣ ሥነጽሑፍንና ሥነጥበብን በማስፋፋት እንዲሁም ሕገመንግስት አርቅቀው ሀገሪቱን ይመሩ እንደነበር በድንጋዮች ፣በሳንቲሞችና ብራናዎች ላይ የተጻፋ ጽሑፎች ምስክሮች ናቸው ።የአክሱም መንግስትም የግዕዝ ቋንቋን የሥራ ቋንቋ አድርጎ ይጠቀምበት ነበር ።ኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ሀገር ናት የሚባለው በግዕዝ በርካታ መጻሕፍት ስለሚገኙበት ነው ። ለምሳሌ የዜማ ፣ የቅኔ መድብላት ፣ የፍልስፍና ፣ የነገስታት ዜና መዋዕሎች ፣ የቅዱሳን ገድላት ፣ የታሪክ ድርሳናት ፣ የጥበብ መጻሕፍት ፣ የግዕዝ የትርጓሜ መጻሕፍት ተጠቃሾች ናቸው ። እነዚህ ድርሳናት በአሁን ጊዜ ላይ የተለያዩ የጥናትና የምርምር ስራዎች ሆነዋል። በሀገራችን የግዕዝ ስነፅሁፍ በአክሱም ዘመነ መንግስት እንደተጀመረ የታሪክ ድርሳት ይናገራሉ። #ንጉስ_ኢዛና የተቀበለውን አዲሱን የክርስትና እምነቱን ለማስፋፋት ይረዳው ዘንድ ብዙ መጻሕፍትን ከግሪክ ወደ ግዕዝ እንዲተረጎሙ አድርጓል። በዘመነ አክሱም የግዕዝ ቋንቋ ዓለም አቀፍ እውቅና ከነበረው ከግሪክ ቋንቋ ጋር ተጓዳኝ ቋንቋ በመሆን አገልግሏል። ለዚህም ማስረጃ የሚሆኑን በአክሱም በሚገኝ የድንጋይ ሰሌዳ ላይ ንጉሱ ኢዛና በ3 ቋንቋዎች በግሪክ፣በሳባና በግዕዝ የፃፋቸው ፅሁፎች ናቸው ። ንጉሱ በ3 ቋንቋ መፃፋ ስለ 3 ነገር ነው ። #በሳቢኛ መፃፉ ጥንታዊ ቋንቋ መሆኑን ለማጠየቅ፣ #በግሪክኛ መዘገቡ በዘመኑ ግሪክ የስልጣኔ መገኛ በመሆኑ ምክንያት ነው ። የግሪክ ስልጣኔ በዘመኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ስለነበር መላው ዓለም ይህን ቋንቋ እንደዛሬው እንግሊዝኛ ይፈልገውና ይገለገልበትም ስለነበር ነው ። በግዕዝ መፃፉ ግዕዝ የቤተ መንግስቱም የሕዝቡም መግባቢያ ቋንቋ ስለነበር ነው።