ልዩ አማርኛ ጥቅሶች Disk


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


💞...

ቀናቶች  አለፉ ጊዜውም ነጎደ
አንዱ ወር ሲመጣ ሌላኛው ወር ሄደ
ግን አሁንም ሳይሽ አንቺን እመኛለው
እስኪገርመኝ ድረስ ዛሬም ወድሻለው


✨🌹ከወደዱት #SHARE 🌹✨

💜 @yefikir_tiksoch 💜
💜 @yefikir_tiksoch 💜


😘እበጂልኝ🌿

ፍቅርሽ ክፉኛ ቢቀጣኝ
አንደበቴ ታስሮ
መናገር ቢያቅተኝ
መፍትሔ ፈልጌ
ደፍሬ መጣሁኝ።

ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ
አፌ ኩልትፍ ኩልትፍ
ላብድ ነዉ በፍቅርሽ
ብዬ ብጠይቅሽ
እስቲ አብደክ አሳዪኝ
ነበረ ምላሽኝ

ፍቅርሽ አጃጅሎኝ
እብደትን ሞከርኩት
ፀጉሬን አንጨብርሬ
ልብሴን ቀዳደድኩት
ወጣሁኝ ጎዳና
ብርዱን ተላመድኩት

ለካስ እብደት ውስጥ
ጥልቅ የሆነ ሚስጥር
የራስ ነፃ ዓለም
ጭንቀት የሌለበት
ፍቅርሽን ረስቼ
እብደት ተመችቶኝ
በዛው ቀጠልኩበት

ምን ይሆን ምላሽሽ
እንዲ ስሆን አይተሽ
መሥዋት መሆኔን
እንደፍላጐትሽ

ፀፀቱን ካልቻልሽው
እየነሳሽ ጤና
አንድ ላይ እንሁን
አንቺም እበጂና።

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


                     ወገኛ
   ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺‌✽‌┉┉┄┄

ልብሽ የሻተውን አልሻም የምትይ
ምንም እንዳልሆነ የምታስመስይ
ሀሳቤ እንዳልገባሽ ዞር በል የምትይ
ወገኛ ነሽ በጣም ጎበዝ አታላይ
          ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ፍቀጂልኝና አንድ እውነት ልናገር
አይንሽ አውርቶኛል አፍሽ ባይናገር
ፍቅርን ያህል ነገር ተሸክመሽ ባይሽ
ላግዝሽ ተጠጋሁ ሸክሙን ልካፈልሽ
አንቺ ግን ...
ወገኛ ነሽና አሻፈረኝ አልሺኝ
በፍቅር ብጠጋሽ በሀይል ገፋሺኝ
እኔማ አልተውሽም እከተልሻለሁ
ወገኛነትሽን ላስተውሽ ምያለሁ
           ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ያው ባትሰሚኝም ስላንቺ አወራለሁ
ያው ባታነቢውም ስላንቺ እፅፋለሁ
ያው ባንቃጠርም እጠብቅሻለሁ
ወገኛ ነሽና ምን ማድረግ እችላለሁ፡፡

  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


////የተጠገነ ቃል\\\
-------------------------------
የተሰበረ ልብ በምን ይጠገናል፣
       ጊዜ ሽሮት እንኳን
       ጠባሳውም ያማል፣
በታወሰ ቁጥር ህመም ያገረሻል፣
        ስንት ነው ተመኑ
        ዋጋ ወጥቶለታል፣
        ያፈቀረን መግፋት
      እንደው ስንት ያወጣል።
  ከረፈደ ነቅተው የቦዘዙ አይኖች፣
 በእርጅና የደከሙ የዛሉ ጉልበቶች።
         ማስተዋል ሲያገኙ
         ሲነቁ ከህልማቸው፣
 እንደው ቢጠየቁ ቢሰማ ድምፃቸው፣
          የገፉትን ማግኘት
        ይሆን ወይ መልሳቸው።
                  እንጃ፣
ብቻ፣ ባላወኩት አለም በሃሳብ ተሰድጄ፣
  የጎዳሽኝ አንቺን በሀሳብ አስረጅቼ።
           ድንገት ባስብ ጊዜ፣
   ስለሰበርሽው ልብ ፀፀቱ ሲገልሽ፣
            ከሀሳብ መለስ ብዬ
            ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፣
     እርሺኝና ኑሪ ሀዘን አይብዛብሽ፣
  አለም አሰቃይታ ቁጭት አይግደልሽ፣
ሺህ ብታደሚኝም ይኸው ይቅር አልኩሽ፣
 በሄድሽበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምሽ፣
    በእንባዬ አትሜ ይቅርታን ላኩልሽ፣
      እውነት መልካሙ ይግጠምሽ።


ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


🦋🌿ስቀሽ … አበረድሽኝ🌿🦋
…       
ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ ከሰርዶ ተዋዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


........,,.,,.,የኔ መጨረሻ ,..,,,......,,,,.

  አምና ወዳጆቿ..
       ሙዚቃ መዉደዷን ሲያወጉ ሰምቼ
ካሴት አዉጥቻለሁ አመቱን ለፍቼ
         ''አንባቢ ነች'' ሲሉ ሆኛለሁ ፀሀፊ
ጥቂት ጠብቄያለሁ ሆኜ ልብስ ሰፊ
       አጥር ለማጠንከር ግንበኛ ሆኛለሁ
እግሯንም ለመንካት ጫማ ጠርጌያለሁ
     እሷን ለመማረክ ቀን ይገኛል ብዬ
ያልሆንኩትን ስሆን እሷን ተከትዬ
ዛሬ ዕድሉ ቀንቶኝ ከፊቷ ቆሜያለሁ
      ሰርጓን ልቀርፅላት ካሜራ ይዣለሁ።
😒😔

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


••●🍃ልረሳሽ አልቻልኩም••●🍃

አማራጭ አጥቼ የግድ ሲሆንብኝ፣
እምረሳሽ መስሎኝ መጠጥን ለመድኩኝ፣
ተዋት እንኳን ቢሉኝ እኔ መች ሰማሁኝ፣
አንቺን ረሳሁ ብዬ በሱስ ተጠመድኩኝ፣
በጫት በሲጋራ እራሴን ደበቅኩኝ።

ምናልባት ሆኖ...
ልቤ ፍቅርን አምኖ..
የኔ ባትሆኝም፣
ፈጣሪ ባይፈቅድም፣
አንቺ የሌላ ሆነሽ በአይኔ እንኳን ባይሽም፣
ያፈቀረሽ ልቤ ፈፅሞ አልረሳሽም።

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


ልክ እንደ ሎሬቱ ፡ እንደ ጋሽ ፀጋዬ
ወንድ ልጅ ከሰው ፊት ፡ አያለቅስም ብዬ
የእንባዬን ማዕበል ፡ አፍኜው ነው እንጂ
ማልቀስ አምሮኝ ነበር ፡ ጥለሺኝ ስቴጂ
(የደስታ እንባ ታቅያለሽ?)

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


#ስደቢኝ_ግድየለም
.
ስደቢኝ ግድየለም አልቀየምሽም
ደደብ የማትረባ አህያ ነህ ቀሽም
ሲጠሉህ የማታውቅ እልም ያልክ ፋራ
ልክስክስም በይኝ አስቀያሚ ጭፍራ
ከፈለግሽ ደግሞ ደሀ ለቃቃሚ
ብትይኝ ግድየለም እባክሽን ስሚ
.
ከስድቦችሽ መሀል መልካሙን እያየሁ
ፋራ በመሆኔ እጅጉን እኮራለው
አህያ ላልሺኝ ደግሞ አንቺን ተሸክሜ
እስከዛሬ አለሁ ይሄውልሽ ህመሜ
.
ደሀ ነህ ብለሻል ደሀ ነኝ አውቃለው
ሀብታም ስላልሆንኩኝ አመሰግናለው
ምናልባት ግን ሆዴ.....
ገንዘብ ኖሮኝ እኔ በሀብቴ ብኮራ
ስድብሽን ሰምቼ እለይሽ ነ'በራ
ሁሉን ያጣ ሆኜ ብትይኝ ውዳቂ
እንደማልጠላሽ ግን አሁንም እወቂ፡፡

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


💔🥀💔🥀💔🥀💔🥀 💔
አይ ያንቺ ነገር
ጥሩውን ሳወራ መጥፎ ይደርስሻል
በቀረብኩሽ ቁጥር አንቺ እሩቅ ሄደሻል
በቀኝ ስጠብቅሽ ግራውን መርጠሻል
እየቻልኩሽ እኔ አንቺን አቅቶሻል
አይ...ያንቺ ነገር እኔን ይገርመኛል
እኔው እያዘልኩሽ አንቺን ይደክምሻል🤦‍♂
እንዳልሆንሽ ሀሴቴ የንጋቴ ምስል
ሆነሽብኝ ቀረሽ የልብ ላይ ቁስል😔❤️‍🔥❤️‍🩹
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


❤️‍🔥የፍቅር ቃጠሎ ❤️‍🔥

ጉንጭሽ ጽጌረዳ
ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጧት ጨረር የበራ ማለዳ፣
የማትጠገቢ😘
ጣፋጭ ከረሜላ የማር እሸት ነሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ ::
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ! 🙈
እሳት ነበልባል ነሽ ነዳጅ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ
ሆነሻል ሕይወቴ
የጋለው ትንፋሽሽ
የፈመው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ፡፡
እጄን ሰጥቻለሁ ❤️
እስረኛ ሆኛለሁ
ያንቀጠቅጠኛል ወባው ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ❤️‍🔥
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ስተክዝ
ንከሽኝ ልደንዝዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ ::😊

 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


❤️❤️
አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና
ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል። ጓደኞቹ እንዲነግራት ቢያበረታቱትም ደፍሮ መጠየቅ አልቻለም። በቃ እሷን እያሰበ በትምህርቱ እየደከመ ሳቅ ጨዋታ እያስጠላው ሰውነቱ እየቀነሰ መጣ።
ጭንቀታም መሆኑ እጅግ ያሳሰባቸው ጓደኞቹ በስንት መከራ አግባብተው እንዲነግራት ያደርጉታል። እናም ሲፈራ ሲቸር በጣም እንደሚወዳት ይነግራታል።
እሷም ቀብራራ ነገር ነበረችና እንዲህ አለችው 'ውይ በጣም ይቅርታ እንኳን የፍቅር ጥያቄህን ልቀበልህ ይቅርና በአለም ላይ ማንን ትጠያለሽ ብባል አንተን ነው የምለው እና ይሄን ጥያቄ ደግመህ እንዳታነሳብኝ' አለችው።
ልጁም ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግቶና
ፈገግ ብሎ ወደ ጓደኞቹ ይመለሳል። ጓደኞቹም ፈገግታውን ሲያዩ ልጅቷ የፍቅር
ጥያቄውን እንደተቀበለችው አምነው በደስታ ተቀበሉት አንደኛው ጓደኛው 'እሺ አለችህ አይደል? በጣም ደስ ይላል' ሲለው ወጣቱ ልጅ 'አረ በፍፁም! እንደውም በዓለም ላይ እንደኔ የምትጠላው ሰው እንደሌለ ነው
የነገረችኝ' አላቸው።
ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው 'ታድያ እንዴት አላዘንክም እንዴት አልተከፋህም?' አሉት እሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ሲል,መለሰላቸው 'ለምን እከፋለሁ ለምንስ አዝናለሁ? እኔ እኮ ያጣሁት በአለም ላይ ከምንም በላይ የምትጠላኝን ልጅ ነው። እሷ ግን ያጣችው በአለም ላይ ከምንም በላይ የሚወዳትን ሰው ነው ስለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንም መከፋትም ያለባት እሷ ናት' አላቸው።
ይሄ ታሪክ የኛም ሊሆን ይችላል። አንድ የምንወደው ሰው ጥላቻውን ሲያሳየን ወይም ሲርቀን እንከፋለን እናዝናለን እናለቅሳለን ግን ይሄን ማድረግ ያለበት ያ ትቶን የሄደ ሰው ነው እንጂ እኛው ሊሆን አይገባም‼️

 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch
ሼር  💚 @Yefikir_tiksoch


​❣❣❣❣❣❣❣❣
┈┈┈••✦🌹✦••┈┈┈
ባይገርምሽ ገና ወድሻለው😍
    👇👇
ባ☞ ባገር አማን
                 አንቺን መርሳት❣
ይ☞ ይሆንብኛልና
                 መጫወት በእሣት❣
ገ☞ ገሀድ ይሁንልሽ
                አረሳሽም ቃልይ❣
ር☞ ርቀሺኝ እንኳን
                     ብቴጂ ካጠገቤ❣
ም☞ ምንም ጊዜ
             ቢሆን ያፈቅርሻል ልቤ❣
ሽ☞ ሽምገላ አይደለም
                 ❤️ቃልዬ በእውነት❣
ገ☞ ገና እወድሻለው
               እስካለው በህይወት❣
ና☞ ናፍቆቴ ልሆንሽ
                   የልብ ትርታዬ❣
እ☞ እንዴት ብዬ ልርሳሽ
                   ውዻ ቃልሻዬ❣
ወ☞ ወደ ተሻለ ህይወት
                   የምሸጋገር ብሻ❣
ድ☞ ድቅድቁን ጨለማ
                   የምገፋ ብሻ❣
ሻ☞ ሻማዬ አንቺው ነሽ
                 መተኪያዬም የለሽ❣
ለ☞ ለኃይሉ ፍቅርሽ
                   ምርኮኛ ሆኛለው❣
ው☞ ውዻ ቃልሻዬ ❤️
                 ላልከዳሽ ምያለው

 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch


የግጥሙ ርዕስ፦ ላርጋት ወይ አላርጋት

ላርጋት ወይ አላርጋት ብዬ ሳመነታ
ለሷ ካለኝ ፍቅር ድህነቴ ጎልታ
ሳልፋት በቀጠሮ ለራሴ ስሳሳት
ያመንኩት ወዳጄ አደርጎ በጠሳት😢


ሀዘን በርትቶብኝ ባዶ ሲሆን እግሬ
ትዝ ትለኛለች ያቺ ሲሊፐሬ።😊

ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch


​#ለዚህ_ነው_ማላምንሽ
.
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
ቃላት አሳምረው፣
ስለ ዝናብ ውበት አድንቀው የፃፉ
ዝናብ የመጣ 'ለት፣
ዣንጥላ ዘርግተው ተጠልለው አለፉ

ልክ እንደዚህ ሁሉ
ንፋስ ነው ዘመዴ ምናምን የሚሉ
ንፋሱ ሲነፍስ መስኮት ይዘጋሉ

ያንቺም ልብ እንዲህ ነው፣
ይቀበል ይመስል ፍቅር ፍቅር ብሎ
ፍቅር ያካፋ ቀን ያልፋል ተጠልሎ

  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@Yefikir_tiksoch


ብታውቂ
(በእውቀቱ ስዩም)
                
                  ስትስቂ!
         ጠፈርን እንደምታደምቂ፣
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ፣
                 ብታውቂ!
                  ÷÷÷÷÷
                 ስትስሚ!
        አጥንት እንደምታለመልሚ፣
        ታማሚ ልብ እንደምታክሚ፣
                 ብታውቂ!
                  ÷÷÷÷÷
                  ስታወሪ!
           ዱዳ እንደምታናግሪ፣
          መነኩሴውን ከሱባዔ፣
          ፈላስፋውን ከጉባዔ፣
             እንደምትጠሪ፣
               ብታውቂ!
                ÷÷÷÷÷
         እንኳንስ በኔ ልትስቂ፣
       ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ፣
       አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!

✨Join & Share✨

💜 @yefikir_tiksoch 💜
💜 @yefikir_tiksoch 💜


​ትመጣ እነደው ብዬ
     ከበርክ ቆሜ
   ደጅ ደጁን እያየው
  በፍቅርህ ታምሜ
   ልክ ስትመጣ
   ሁሉን እረስቼ
  ከንፈርህን ሳምኩት
መታመሜን ትቼ

       ለካስ
አንተን የሚያሳየኝ
የቁም ቀዠት ኖሩዋል
የሠው እያየሁኝ
  የራሴ ህልም ሆኗል

  መንቃት ባለፈልግም
  ከዚህ ውብ ቅዠቴ
   ድንገት ቀሰቀሰኝ
     የገዛ ብሶቴ


✨Join & Share✨

💜 @yefikir_tiksoch 💜
💜 @yefikir_tiksoch 💜


❤️አንተ ምን አረከኝ?🤔
~~~

ለቅፅበታት  ራሴን  ሆኜ😎፣
ልረሳህ እልና ልቤን አጀግኜ፣
ወላዋይዋን ነፍሴን ላንዳፍታ ለምኜ፣
#የሌላ መሆንህን ውስጤን አሳምኜ🥺
.
🤓ልተውህ እልና አይኔን ረግሜ
ውብ ሳቅህን እንዳላይ ደግሜ
እንድረሳህ  ብዬ  ካንጀቴ  እጥራለሁ
ካይንህ #ተደብቄ ቀ
ናት ቆጥራለሁ👀😢

ሞክራለሁ እንጂ መች ረሳሀለሁ😔
.
በወሬዬ  መሀል  ሁሌ  አነሳሀለሁ🤷‍♀

አየህ
ያንን  ሁሉ  ጊዜ  ላመታት  ስርቅህ
#በይመጣል  ተስፋ ሁሌ ምጠብቅህ🤦‍♀

የሚባክንልህ  ልቤ  ሚስኪኑ፤
ልክ እንደ ድራማ ሁሌ በየቀኑ፤😊
አንተን  እያሳየ  እኔን  ያከሰረ
ኝ፤
እንዳልተውህ አርጎ አጥብቆ ያሰረኝ፤❤️‍🔥

የመልክህ ሰአሊ ለመላ አካላቴ
አንተ ምን አረከኝ ህልሜ ነው ጠላቴ።😔

✨Join & Share✨

💜 @yefikir_tiksoch 💜
💜 @yefikir_tiksoch 💜


♥️ከፍቶኛል ስልህ እንደናፈከኝ🌹

♥️ሳኮርፍህ እያሰብኩህ እንደሆነ🌹

♥️ሳቅፍህ እንደምሳሳልህ🌹

♥️ስስምህ እንደማፈቅርህ🌹

♥️አይኖቼ ሲያዮህ አለሜ እንደሆንክ🌹

♥️ስታስቀኝ የደስታዬ ምንጭ እንደሆንክ🌹

♥️ስምህን ጠርቼ ስምል ያንተ ብቻ መሆኔን፡፡🌹

♥️እጅህን ስይዝህ እንደማምንህ እወቅ።🌹


✨Join & Share✨

💜 @yefikir_tiksoch 💜
💜 @yefikir_tiksoch 💜


😍ጠብቄሽ ነበረ😁

የቆሸሸ ትሪ፡ ድስት እና መክተፊያ
ሰብስቤ አስቀምጬ፡ በአንድ መዘፍዘፊያ
ጠብቄሽ ነበረ
መምጣትሽን አምኜ
በናፍቆት ውስጥ ሆኜ
የቆሸሸ ልብሴን፡ ደጅ ላይ ቆልዬ
ሳሙና ገዝቼ፡ ተስፋን አንጠልጥዬ
እጄን ጉሮሮዬን፡ በአልኮል ወልውዬ
ጠብቄሽ ነበረ
ጥም እያቃጠለኝ፡ ደርሶ እንደበረሀ
ወይ አልገዛሽ ነገር
መሆኔን እያወቅሽ፡ የናጠጠ ደሀ
ስትቀሪ
ጊዜ
ደረቅ ቧንቧ እያየሁ፡ አዘንኩብሽ ውሃ

።።።።።።።።።።።።።።።።

ጠብቄሽ ነበረ፡ ጎመን አጎምኜ
ድንች አደንቼ፡ በቤቴ ውስጥ ሆኜ
አብስዬ ለመብላት፡ ቁርስ ምሳና ራት
ከቤት ባለመውጣት፡ ሀገሬን ለመስራት
ጠብቄሽ
ነበረ
ስትጠፊብኝ ጊዜ፡ አዘንኩብሽ መብራት


😊ለሌሎችም ያጋሩ

•➢ ሼር // SHARE

💜 @yefikir_tiksoch  @yefikir_tiksoch  💜

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

79

obunachilar
Kanal statistikasi