😱😱😱😱
@loliyeeዶ/ር አብይን ከጠላት ለማዳን
ቤተ መንግስቱን ያመሰው ትራፊክ አስገራሚ ገጠመኝ
ስሜ ለግዜው ይቆይ በሞያዬ ግን ትራፊክ ፓሊስ ነኝ ከትላንት ህዳር 11 2011 ዓ.ም የመውሊድ በአል የሚከበርበት እለት ቢሆንም እንደሁሌው ለሊት 12:00ሰአት ወጥቼ ወደ ስራዬ
አመራሁ ።
ምድብ ስራዬ
@loliyee መስቀል አደባባይ አከባቢ ከታች ከቦሌ መስመር የሚመጡ እና ከላይ ከአራቱም አቅጣጫ ወደ ቦሌ
ያለውን የትራፊክ ፍሰት መቆጣጠር ነበር። ቀደምብዬ በመድርስ ስራዬን
@loliyeeማከናወን ጀመርኩ ሰመኑን በሀገራችን በተሰማነው አስደንጋጭ ዜና ምክንያት በተሰጠን ተጨማሪ ተልእኮ ከመደበኛ ስራዬ በተጨማሪ በእየአንዳንዱ መኪና ውስጥ ያሉ ሰዋችን በተቻለኝ አቅም ማንነታቸውን ለማጣራት እሞክራለሁ።
አንድ ነጭ ላንድ ክሩዘር መኪና በስጢፋኖስ በኪል ቁልቁል መጣና መብራት ስለያዘው ቆመ። ጠጋ ብዬ ወደ ውስጥ ቃኘት ሳደርግ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ናቸው ለክብራቸው እጅ
ነስቼ ዘወር አልኩ። ወድያው መብራት ለቀቃቸው በተቃራኒው ከቦሌ የሚመጡትን ስላስቆማቸው ጠጋ አልኩና ቅኝቴን ቀጠልኩ አቶ ለማ
የነበሩበት መኪና በሄደ በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ ከቆሙት መኪኖች ባንድ እና በተለየ መኪና ውስጥ አቶ ለማ መገርሳን
ደግሜ በማየቴ በድንጋጤ አይኔን ሶስቴ ከድኜ ከፈትኩ አልተሳሳትኩም ልክ ነበርኩ የቆምኩበት እግሬ ተንቀጠቀጠ
ሰውነቴ በላብ ተዘፈቀ ሁለት ለማ መገርሳ ሁለት ተመሳሳይ ፊት እዛው በቆምኩበት ደንዝዤ ሳልንቀሳቀስ አረንጋዴው በራና መኪናው በስጢፋኖስ ቤተ ክርስትያን ጋር ሽቅብ ተፈተለከ። አንድ ሰው የአቶ ለማ መገርሳን ፊት ተመሳሳይ ሰርጀሪ አሰርቶ
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድን ሊያጠቃ ወደ ቤተመንግስት እየሄደ ይሆን በድንጋጤ ሞተሬን ያቆምኩበት ቦታ ጠፋኝ አዙሪት እንደያዘው ሰው 360 ድግሪ ተሽከርክሬ ሞተሬ ላይ ወጣሁና በመጨረሻ ፍጥነት በአየር ላይ እየበረርኩ መኪናው ወደ ሄደበት አቅጣጫ ተፈተለኩ። ግምቴ ልክ ነበር ከሩቅ አየሁት ወደ ቤተ መንግስቱ መግቢያ ፍቱን ሲያዞር ጭንቀቴ ከመብዛቱ የተነሳ ሳልደርስበት ነፍሴ
የምታመልጠኝ መሰለኝ።ቤተ መንግስት በር ላይ ስደርስ ግቢ ውስጥ ባጋጣሚ ዶክተር አብይ ከግቢ ሲወጡ ስላገኛቸው
ከመኪናው ወርዶ ሲያወራቸው በቅርብ ርቀት አየሁት። ከሞተሬ ላይ ከመውደቅ በማይርተናነስ መውረድ ወረድኩና
@loliyeeወደ ጥበቃዋቹ በመጠጋት የተፈጠረውን እውነታ ሳስረዳቸው ድንጋጤያቸው ከኔ ብሶ ቁጭ አለ። ግቢውን ባንድ እግሩ
አቆምነው ።የዶክተር አብይ ጠባቂዋች ከመቅፅፈት ዶክተር አብይን በምርጥ ብቃት ከአይናችን ሰወሩት። ሰውየውን በግላጭ አገኘሁት ሰውነቴ ከመንቀጥቀጥ አልፎ በእልህ ይንዘፈዘፋል ፊቱ ተገትሬ አፈጠጥኩበት እሱም አፈጠጠ ፊቱ የክቡር አቶ ለማ መገርሳ ቢሆንም ትክክለኛው ለማ አይደለም ብዬ ስላሰብኩ ቢያፈጥብኝም አልፈራሁትም። የሀሰት ፊቱን ገፍፌ ሳነሳው ዋናው ተጠርጣሪና እና ተፈላጊ
ነው።ጭፈራዬን አቀለጥኩት በህልሜ መሆኑን ያወኩት ጩኸቴ ያባነናት ሚስቴ በጆክ ሙሉ ቀዝቅልዛ ዉሃ ፊቴ ላይ
ቸምቧ ስታደርግብኝ ነበር።እችክ እችክ ማነው? ምንድን ነው?
ሰበር ዝናብ ነው የኔ ባል በል ተኛ።
😂😂😂😂
@loliyee@loliyee