◉●••#ስለ_ወደድኩት_በድጋሜ_የተለቀቀ
❖┈┈••◉┈┈◉●••┈┈❖
አንዳንድ ሰዎች የሚጠይቋቸው አድክም #ጥያቄዎች ❓ እና መመለስ ያለብን #መልሶች
❀ ❀ ❀
❖ ከአሜሪካ ያለ ዘመድ ከሌሊቱ ሰባት ሰአት🕖 ደውሎ ተኝተሀል እንዴ?
#አይ_ምስር_እየለቀምኩ_ነበር
❀ ❀ ❀
❖ ከፍቅረኛህ💕 ጋር አልጋ ላይ ስትሳሳም💋 ቆይተህ ልብስህን ማወላለቅ ስትጀምር: እንዴ ምን ልታረግ ነው?
#ፎቶ_ልነሳ!
❀ ❀ ❀
❖ሲኒማ ለመግባት ተሰልፈህ እያለ ውይ እዚ ደሞ ምን ታረጋለህ...?
#የትምርት_ቤት_ክፍያ ልከፍል መጥቼ ነው
❀ ❀ ❀
❖ ለፍቅረኛህ❤️ እቅፍ ፅጌረዳ ልትሰጣት ሄደህ በርላይ ተቀብላህ ወይኔ አበባ ነው? ለኔ?
#አየ_ድፎ_ዳቦ🍞 ነው ወስደሽ ላባትሽ ስጫቸው ይባርኩት ።
❀ ❀ ❀
❖ ለበአል በግ🐑 ገዝተህ ወደ ቤት እየሄድክ, ለበአል ሊታረድ ነው?
#አይ_በማደጎ_ልናሳድገው ነው ። ተዋወቀው ወጋየሁ ይባላል ።
❀ ❀ ❀
❖ ከሻወር ገላህን ታጥበህ 💦እንደወጣህ አግኝቶህ, ገላህን ታጥበህ ነው?
#አይ_ጎርፍ_ውስጥ_ወድቄ_ነው።
❀ ❀ ❀
❖ ወደ ቢሮ ፎቅ ለመውጣት ሊፍት እየጠበቅህ, ወደላይ ነው ?
#አይ_ሊፍቱ ቢሮዬን ሊያመጣልኝ ሄዶ እየጠበቅሁት ነው።
❀ ❀ ❀
❖ ሆቴል🏩 ገብተህ ጠረፔዛ በአይንህ እየፈለክ እያለ አስተናባሪው መቶ መቀመጫ ፈልገህ ነው?
#አይ_የእትዬ_እልፍነሽ ውሻ🐼 ከሰፈር ጠፍቶ እያፈላለግን ነው
╭─┅═ঊ
Join @Mudenyaz ঊঈ═┅─╮