አንድ ቀን ረሱልﷺ ሰአላባህ ኢብን፣ አቢ አብድረህማን የተባለውን የ 16 አመት ልጅ፣ ወደ አንድ ቦታ ይልኩታል። ይህ ልጅ በጉዞ ላይ ሳለ መንገድ ላይ በድንገት አንድ ሴት በራን ከፈታ ገላዋን ስትታጠብ ይመለከታል። አይኑ ባሳየው ነገር ተፀፀተ ይህ ልጅ እስቦበት ሳሳይሆን ንፋሱ መጋራጃውን ሲከፍተው በድንገት ነበር ያያት።
እናም ይህ ልጅ በጣም ደነገጠ እንዲህም አለ :- ረሱልﷺ ልከውኝ እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር እመለከታለው? በማለት እራሱን ወቀሰ። ታድያ ይህን ሃራም ነገር አይቼ እንዴት ብዬ ነው ረሱልﷺ የማየው? ሃራም ባየሁበት አይኔማ ረሱልﷺ አላያቸውም ብሎ የተላከውን ትቶ ሳይመልስ ይጠፋል።
ረሱልﷺ የዚህ ልጅ መጥፋት አሳሰባቸውና ሁለት ሰሃቦችን እንዲፈልጉት ይልካሉ። ሳሃቦችም መዲና ድረስ ሄደው ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም
ረሱልﷺ ልጁን እዳጡት ይነግራቸዋል።
ረሱልﷺ ጉዳዩ እጅጉን ስላሳሰባቸው ለሁለተኛ ጊዜ ሌሎች ሰሃቦችን አክለው አሁንም፣ ደግመው ልጁን እንዲፈልጉት ይልኳቸዋል። ሰሃቦችም እሱን ፍለጋ ዞረው፣ ዞረው መጨረሻ ላይ አንድ ገበሬ ዘንድ ይደርሳሉ። ገበሬው ገና ሲያያቸው እርዳታ ፈለጊ መሆናቸው ሲያውቅ ምን ልርዳቹ በማለት ጠይቆ ያስተናግዳቸዋል።
እነሱም እንዲህ አሉ:- አንድ ልጅ አይተሃል? ብለው ብዙ የሚያውቅበትን ምልክት ይነግሩታል። ምልክቱን ሲነግሩት ፣ሰውየው ልጁን ወደየው አወቀው፣ ከዛም ይህ ልጅ እኮ እዛጋ የምታዩት ተራራ⛰️ ነው የሚኖረው፣ ምን እንደነካው እኔጃ ሁል ጊዜ ያለቅሳል እያለቀሰም (አስተግፊሩሏህ) እያለ ጌታውን ምህረት ይጠይቃል። (አስተግፊሩሏህ) እያለ ነው የሚውለው ፣ ልጁ ከማንም ጋር አይገናኝም መሸት ሲል ማታ አካባቢ እኛ ጋር እየመጣ፣ ወተት ይጠይቃል ከዝያም ወተቷን ፊት፣ለፊቱ ያስቀምጣትና እንባውን ወተቷ ላይ እያፈሰሰ ይችን ፣ ወተት ጠጥቶ ይሄዳል በተረፈ ከማንም ፣ አይገናኝም በማለት የልጁ ሁኔታ በሀዘን ነገራቸው።
ሰሃቦችም በጣም ተገረሙ የተባሉትን ሰዓቴ የተባሉትንም ⌚ሰዓት በመስማት የሚመጣበትን ⌚ሰዓት እንጠብቅና ሲመጣ ረሱልﷺ ዘንድ ይዘነው እንሄዳለን ተባባሉ እናም ቀኑ መሸ ልጁ በተባባሉት ⌚ሰዓት ላይ ወተት ሊጠይቅ ሲመጣ ሰሃቦቸ ያገኙታል ልጁ በጣም ከስቷል፣ በሃዘን ምክንያት ተጎሳቁሎ ሲመለከቱት በጣም አዘኑ ልጁንም ያዙትና ወደ ረሱል ﷺ ዘንድ ለወሰዱት እንደሚፈልጉ ሲነግሩት ፍቃደኛ አልሆነም ፣ መሄድ እንደ ማይችል በጣም አጥብቆ ነገራቸው፣ በደከመ ጉልበቱ ከእጃቸው ለያመልጥም ፈለገ። ነገር ግን ጉልበት እንደሌለው ስላወቁ በግድ ተሸክመው ወደ ረሱልﷺ ዘንድ ወሰዱት።
ከርሳቸውም ዘንድ ደረሱ ረሱልﷺ ና እስቲ ብለው ጭንቅላቱን ታፋቸው ላይ ሊያስተኙት ሲሉ፣ ጭንቅላቱን ከታፋቸው ላይ በማንሳት (ያረሱለላህ) ﷺ ይህ የኔ ጭንቅላት በጣም ቡዙ ወንጀል ተሸክሟል ሰለዚህ የርሶዎ የተከበረ አካል ላይ አታስተኙኝ በሎ ገሰጻቸው ልጁ ረሱልﷺ ጋ በደረሰ ጊዜ ከመክሳቱ የተነሳ በጣም ተጎሳቁሎ የሞት ጥላ በእሱ ላይ አጥልቶ ጣረ ሞት ላይ ነበር። እናም አይኑ ደንገት ባየው ነገር ተፀፀቶ በተራራ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ እያለቀሰ (አስተግፊሩላህ) እያለ የጌታውን ምህረት እየጠቀ ቆይቶ በመጨረሻም ሸሀዳ ይዞ በረሱልﷺ እጅ ላይ ሞተ
ከዛም ጀናዛው ታጥቦ ወደ ቀብር መሄድ ጀመረ ጀናዛው ተሸክመው በሚሄዱበት ⌚ሰዓት ረሱልﷺ አረማመድ ይለይ ነበር። ረሱልﷺ በእግር ጣቶቻቸው ይራመዳሉ። ሰሃቦችም ረሱልﷺ መንገድ የተጣበበባቸው መስሏቸው ሰዎችን እየገፈታተሩ ፣መንገድ ይከፈቱላቸዋል ። ነገር ግን አሁንም ረሱልﷺ እንደመጀመሪያው ነበር በጣታቸው የሚጓዙት ሰሃቦችም በረሳቸው አረማመድ ግራ፣ ተጋቡ ተገረሙ እንዲህም ሲሉ ጠየቁ?
ያረሱለላህ ﷺ ምነው መንገዱ ክፍት ሆኖ ሳለ ለምን በእግር ጣቶችዎ ይራመዳሉ አሏቸው ረሱልﷺ እንዲህ በማለት መለሱላቸው የ(ሰዕለባህ ኢብን፣ አብድረህማን) ን ጀናዛ ለማጀብ ለመጡ መላአካዎች ፣ ብታዩዋቸው ኖሮ፣ ገብዛታቸው የተነሳ አንድ እግር እንኳን ለማሰቀመጥ የሚመች ቦታ አታገኙም ነበር ብለው ነገራቸው።
Subhan allah
t.me/menhaguselfusalihanagiya724