ፍጥነትህን ጨምር!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ሩጫህ የት ለመድረስ ነው? ለምንድነው የምትጣደፈው? እንቅልፍህን የምታጣው ለምን ይሆን? ትግልህ፣ ድካምህ፣ አልበገር ባይነትህ፣ ፅናትህ፣ ትዕግሥትህ፣ ወኔህ ለምን ይሆን? ይህ ሁሉ ለህይወት አለማህ /Life Purpose/ የምትሰጠው ስጦታ፣ የምትከፍለው መሱዓትነት ነው።
አላማ ላለው ሰው እያንዳንዱ ቀናት፣ እያንዳንዱ ሰዓትና ደቂቃዎች የእራሳቸው ትርጉም አላቸው። እያንዳንዱ ተግባሩ በሰዓታት የተከፈሉ፣ ከዓላማው የተገናኙ፣ ወደፊትቱን የሚወስኑ መሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል። የህይወት ጠዓም፣ እርካታዋ ከልብ ይሰማዋል።
አዲስ ቀን ሲያይ በምክንያት እንደሆነ ይረዳል፣ አዲስ ሰው ሲያገኝ የሚሰጠው፣ የሚቀበለው ነገር እንዳለ ያጤናል፤ ያሯሩጠው፣ አብሮት ይጓዝ ይሆን፣ የጋራ አለማ፣ ተያያዥ ራዕይ ይኖራቸው ይሆን ይመረምራል።
አዎ! ጀግናዬ..! በህይወት አላማህ ወሳኝነት ልክ
ፍጥነትህን ጨምር፣ ፅናትትህን ከፍ አድርግ፣ ትዕግስትህን አብዛ፣
ትግልህን አጠንክር። የአላማህ አስፈላጊነት፣ የራዕይህ ትልቅነት ለእያንዳንዱ ተግባርህ በምትሰጠው ትኩረት የሚወሰን ነው።
ፊትለፊትህ ብሩህ ነው፤ አላማህ ግብ አለው፤ ህይወትህ ትርጉም አግኝቷል፤ ለምን እንደምትኖር አውቀሃል፤ አምላክ አብሮህ እንዳለ ተረድተሃል፤ ጉዞህን የምታመቻቸው አንተ እንደሆንክ ገብቶሃል።
አዎ! የሩጫህ ሚስጥር፣ ትጋት፣ የትግልህ ምክንያት በግልፅ ታይቶሃል፤ የቀናት መምጣት ትለቁ የህይወት በረከት፣ የህይወት ስጦታ መሆኑን ተረድተሃል፤ ጀምሮ የሚተው፣ የሚያቆም ማንነት የለህም፤ የምትታወቀው በአላማ ፅናትህ፣ በትዕግስትህ፣ በአድራጊነትህ ነው።
በርታ! መልካም ጊዜያት ከፊትህ አሉ፤ በጎ፣ ተናፋቂ ሁነቶች ከፊት ይጠብቁሃል። ተስፋህን ከሚቀሙህ፣ የህይወት ትርጉምህን፣ አለማህን ከሚያሳጡህ ተግባራት ተቆጠብ፤ ዞር በል፤ የህይወትህን እጣፋንታንም እራስህ ወስን።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
🔺🔻
SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1ምክረ-አዕምሮ/
@MentalCounsel 😊💪