Ⓜⓔⓠⓢⓤⓓ_ⓘⓑⓝ ⓜⓤⓗⓐⓜⓜⓔⓓ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


https://t.me/joinchat/AAAAAEPkt7DlRoj-xDOIbA
ተውሂድና ሱና አንድ ያደርጋሉ፣ የውሸተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡ ሽርክና ቢድዐ ይበታትናሉ፣ የእውነተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡የአሕለል ሱና ወልጀመአ ☞ @meqsud_ibn_muhammed
በሚለቀቀው ትምርት ላይ አስተያየት ካላቹሁ
@maqsude

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ምንም ብታብጥ
ልትፈነዳ ብትደርስም
አላህ ከቀደረ
ከአንድ ቦክስ አታልፍም ፡፡

ምን ለማለት ፈልጌ ነው "ብዙ አትኮፈስ"ቀለልና ገር መሆንን ልመድ ፡፡

join t.me/meqsud_ibn_muhammed


ጀማዓ አል ተብሊግ እነማን ናቸዉ ?

🔊 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን ዐልዐሩሲ ( ሀፊዘሁሏህ )

t.me/meqsud_ibn_muhammed




ከቁርዓን መራቅ

መልዕክተኛውም ጌታዬ ሆይ ሕዝቦቼ ይህንን ቁርዓን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት አለ›› አል-ፉርቃን 30
ኢብኑል ቀይም ከቁርዓን መራቅ ብዙ አይነት እንደሆነ ጠቅስዋል ከነዚህም ውስጥ

➊ በቁርአን ከማመን መራቅ

➋ በቁርአን አምኖ ግን በተግባሩ ላይ አለመገኘት

➌በቁርአን አለመዳኘት

➍ ከማስተንተን እና ከማወቅ መራቅ

➎ ከልብ በሽታዎች በቁርዓን ከመታከም መራቅ

እነዚህ ነገሮች በሙሉ ከቁርዓን ከማፈንገጥ (ሀጅር) ይመደባሉ፡፡
የማፈንገጥ ደረጃው ቢለያይም ግን ሁሉም ማፈንገጥ ናቸው ያፈነገጠ ዳግም አላህ የተጨናነቀ ኑሮን አንደሚሰጠዉና እና በዕለተ ትንሳዔ እውር አድርጐ እንደሚቀሰቅሰው ገልፆልናል፡፡

ከወንድም t.me/meqsud_ibn_muhammed


የ «ኺላፍ» ጉዳዮች ባጭሩ ፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

ስለ ኢስላማዊ ህግጋት ሊኖረን የሚገባውን ምልከታ በሁለት ከፍለን ልናይ እንችላለን፦

➊ኛ በርዕሶቹ ላይ የሚሰጠው ሸሪዓዊ ፍርድ በግልጽ ቁርአናዊና ነቢያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የፀደቀ እንደሆነ ለየትኛውም ዓይነት ውዝግብ መድረክ አይኖርም ብይኑንም ያለምንም ማንገራገር ተቀብሎ ማስተናገድ የግድ ይሆናል።
ይህንን እውነታ ከተረዳ በኋላ በጉዳዩ ላይ ከተመለከተው ሸሪዓዊ ህግ ጋር የሚጣረስ አቋም ያንፀባረቀ ካለ አስፈላጊ ሲሆን እንደ ጥፋቱ መጠንና ተፅዕኖ ስህተተኝነቱን በግልጽ አንደበት ማስፈር ይገባል ጥፋቱም ተቀባይነት የሚያስገኝ ምክንያት ስለማይኖረው አቋሙ እንደማፈንገጥ ታስቦ የእርምት እርምጃ ይወሰድበታል አልፎ ተርፎም የሚከተለው የአላህ ቃል የሚመለከተው
ሊሆን ይችላል፦

وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًا
ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን ገሀነምንም እናገባዋለን መመለሻይቱም ከፋች ( ኒሳእ 115 )

ታዋቂው የኢስላም ጠቢብና ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦ ግልፅ ያለውን የቁርኣን አስተምህሮት የተሰራጨውን ነብያዊ ፈለግ አሊያም የዚህ ህዝበ-ሙስሊም ቀደምት ትውልዶች በአንድ አቋም የተስማሙበትን ጉዳይ ይቅርታ ሊደረግለት በማይገባ መልኩ ዑዝር በማያሰጥ መልኩ የጣሰ የቢድዓ አንጃዎች በሚስተናገዱበት (ስርዓት) ይስተናገዳል የነርሱ ብይን ይሰጠዋል። {መጅሙዑ’ል-ፈታዋ [24/172]}
ለዚህ ክፍል ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ድንጋጌዎች አሉ ከአላህ በቀር ማንንም (የአምልኮ ጥሪ) አለመጣራት የአላህ ስሞችንና ባህሪያቱን መልዕክታቸውን ሳያዛቡ በተገቢው መልኩ ተቀብሎ ማስተናገድ ኢማን መልካም ንግግርንና ተግባርን እንደሚያካትት ማርጋገጥ በቀደር በአግባቡ ማመን ከቢድዓ መጠንቀቅ…ወዘተ ,,,, እነኚህ ከኢስላም ህልውና ጋራ ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ቦታ የሚሰጠው “ኺላፍ” (ውዝግብ) የለም! አንዳንድ ግለሰቦች (ለምሳሌ፦ ስለ አላህ ባህሪያት አንድ ሙስሊም ሊኖረው የሚገባው ትክክለኛ አቋም ሲገለፅ) “በርዕሱ ላይ የኢስላም ሊቃውንት ተወዛግበዋል የሚሉት አባባል ፍፁም የተሳሳተና አደገኛ ድምዳሜ ነው ብዙዎች ይህን መሰል ቃል የሚሰነዝሩት እውነታውን በተገቢው መልኩ ለመረዳት ከሚደረግ ውይይት ለመሸሽ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከግንዛቤ እጥረት በመጣ የዋህነት ነው ሆኖም ከሶስቱ ምርጥ ትውልዶች በኋላ ከመጡት የኋለኞቹ ሊቃውንት መካከል አንዳንዶቹ እንደሌሎች ርዕሶች ሁሉ በዚህኛውም ላይ በተለያዩ ምክንያቶችና ትፅዕኖዎች የተነሳ ስህተት ላይ መውደቃቸው ይታወቃል ይህ አቋማቸው ግን እንደ ስህተት ታይቶ ይታረማል እንጂ የቀድሞዎቹን ትውልዶች ስምምነት የሚንድ "ኺላፍ" በፍፁም አይሆንም አዎን ለተሳሳቱ ዓሊሞች የሚሰጠው ማስተካከያ በቢድዓ አራማጅ ጎጠኞች ላይ እንደሚደርሰው ውግዘት አይደለም! ግን ስህተት ሁሉ እንደመደበኛ ሚዛን ላይ አይሰቀልም በርዕሱ ላይ የሚሰጠው ሸሪዓዊ ፍርድ በግልጽ ቁርአናዊና ነቢያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የፀደቀ ስለሆነ ውዝግብን የሚያስተናግድ መድረክ አይኖረውምና!
~~~~~~~
➋ኛ በርዕሶቹ ላይ የሚጠቀሱት ማስረጃዎች የሚጠቁሙትን መልዕክት በተመለከተ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት በግንዛቤ ልዩነት የተለያየ አቋም ያንጸባረቁ ከሆነናና ጉዳዮቹ በዑለማዎች ዘንድ ሸሪዓዊ ምልከታን (ኢጅቲሃድን) የሚያስተናግዱ መሆናቸው የታወቀ እንደሆነ አንድ ዓሊም በዚህ ረገድ ከሌላው የተለየ አቋም ቢመርጥ ብሎም ቢሳሳት ፍርዱ እንደሙሉ ጥፋት ተወስዶ አይኮነንም፤ መልዕክተኛው እንደዚህ ብለዋል፦«አንድ ፈራጅ ሲፈርድ እውነታን ለመረዳት ተጣጥሮ ትክክል ከሆነ ሁለት ምንዳ አጅር አለው ሲፈርድ እውነታን ለመረዳት ተጣጥሮ ከተሳሳተ አንድ አጅር አለው (አል-ቡኻሪ/ 7352 ፣ ሙስሊም/1716)
ሆኖም የላይኛው "ሀዲሥ" እንደሚያስረዳው በዚህኛውም ርዕስ ላይ ቢሆን እውነትን ለማወቅ ሁሉም እንደየአቅሙ መጣር ይጠበቅበታል።
~~~~~~~
አላህ ሁላችንንም ወደ ጀነት ጎዳና ይምራን!

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
"""""""""""""""""""""""
july / 18 / 2019
ሀምሌ / 11 / 2011

✍ከወንድም meqsud muhammed

#አሰላሙ_ዐለይኩም

t.me/meqsud_ibn_muhammed

                   
                  


⇨የማንቂያ ደወል💎

⇨ወቅታዊ የሰለፍያ ዳዕዋና ሰለፍዮችን የተመለከተ ሙሀደራ

√→🎙በኡስታዝ ባህሩ ተካ
【حفظه الله تعالى】


#አሰላሙ_አለይኩም_ወረህመቱሏሂ_ወበረካቱ
=============================
በአሁኑ ዘመን ብዥታዎች ከጊዜ ወዴ ጊዜ እየጨመሩ ነው ቢድኣ አድሥ በድን ላይ ፈጠራም ) እየተበራከቱ ነው የነብዩን ሱለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም የሱሃቦችንና የሱሃባ ተማሪዎችን መንገድ መከተል በተቃራኒው ደግሞ እየተወገዘ ያለበት ዘመን ላይ ነው ያለንው።
ሥለዚህ ውድ ወንድምና እህቶች በመጀመሪያ ራሴን በመቀጠል ደግሞ እናንተን ማሥገንዘብ የምፈልገው የቀደምቶችን መንገድ እንከተል ይህም ማለት በማንኛውም ሁኔታችን በቀደምቶች መንገድ ልንጓዝ ግድ ይለናል በመጀመሪያ በእውቀት ላይ ራሥን ቢዚ ማድረግ በመቀጠል ኢኽላሥና ሙታበኣ ያለውን ተግባር መፈጸም ከዚያም ጥሩ በሆነ ግሣጼ ለሠዎች ትምህርት (ዳዕዋ )ማድረግ ይኖርብናል ።
ኢንሻ አላህ እንነዚህን ነገሮች ከተገበርን በሁለቱም ሀገር የበላይ እንሆናለን
~~~~~~~
ከቢድኣም መሥመር ራሣችንን እናርቅ ሙሥሊም ወገኖቻችንንም እናሥተምር እናሥጠንቅቅ ቢድኣን አሥመልክቶ ቀደምት ምሁራኖች ብዙ ብለዋል አንድ ሁለቱን ምሣሌ ለመግለጽ እሞክራለሁ ፡፡

➊ ኢብኑ ሃጀር አሥቀላኒ ረሂመሁላህ እንድህ ይላሉ"ደሥተኛ ሰው ብሎ ማለት ሰለፎች(ቀደምቶች) የነበሩበትን አጥብቆ ይዞ ከለፎች (ከነሡ በኋላ የመጡ ሰዎች ) የፈጠሩትን አድሥ መጤ ነገር(ቢድኣን )የራቀ ነው (ፈትሁል ባሪ ጁዝ 13 :ገጽ 267)

➋ ሱፍያን አሠውሪ ረሂመሁላህ እንድህ ይላሉ ቢድኣ ኢብሊሥ ዘንድ ከተራ ወንጀል የተወደደ ነው ምክንያቱም ወንጀለኛ የሆነ ሠው ወንጀል ላይ እንዳለ ሥለሚረዳ ንሣሃ(ተውበት)ሊያደርግ ይፈልጋል ቢድኣ የሚሠራው ሠውዬ ግን ወዴ አላህ የሚቃረብ እየመሠለው በወንጀሉ ላይ ይቀጥላል "

➌ ኢብኑ ተይሚያ አላህ ይዘንላቸውና እንድህ ይላሉ "የቢድኣ ባለቤቶች በማህበረሠቡ ውሥጥ ወንጀል ከሚሠራው በበለጠ አደገኛዎች ናቸው" (መጅሙዑል ፈትዋ 7:ገጽ 284)

አላህ ሆይ የመልካም ቀደምቶችን መንገድ የምንከተል አድርገን

""""""""""""""""""""""
July / 15 / 2019
ሀምሌ / 8 / 2011

✍ከወንድም meqsud muhammed

#አሰላሙ_ዐለይኩም

t.me/meqsud_ibn_muhammed

                   
              




ል ባለቤቶች መካከል ይከፋፍላል ብለዋል ፡፡
እኔም አዎ ይከፋፍላል ፅዱ ከነበረው የሰለፎች ( ቀደምቶች ) መንገድ ላይ ሰርጦ ገብን ተግባራትም ይሁን እምነትን ከሚያራምዱ ግለሰቦች ጋ ልዩነትን ይፈጥራል ይህ ደግሞ የሚጠላ ሳይሆን #እሰይ የሚያስብል ነው ፡፡
"
"
"
"
እንግዲህ በኔ የእውቀት ደረጃ ይህንን ብያለው አቋሜን ሀቅ ሆኖ ካገኛችሁት የመቀበል ግዴታ አለባችሁ ፡፡
አደራ ሀቅ ሆኖ እንዳታስተባብሉትና መግቢያ ላይ በጠቀስነው ሀዲስ መሰረት ኩራተኛ ተብላችሁ ጀሀነም እንዳትወርዱ ፡፡

ባጢል ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ ፦ እኔም መንገድ ስቼ እናንተንም አስቼ እንዳልጠየቅ ራቁት ፡፡
"
"
"
ጌታችን ( አላህ ) ሀቅን ሀቅ አድርገህ አሳየንና የምንከተለው አድርገን
ባጢልንም ባጢል አድርገህ አሳየንና ከሱ የምንርቅ አድርገን !!!!

ሰለፊያ በሁለት ድንበር ማለፎች መካከል የምትገኝ የጠራችና የፀዳች #የነብያችንና_የሰሀቦች መንገድ ነች ፡፡

ጌታችን ( አላህ ) የስም ብቻ ሳይሆን የተግባርም ሰለፊይ ታደርገን ዘንድ በምርጥ ስሞችህና በላቁት ባህሪያቶችህ እንለምንሀለን ።

""""""""""""""""""""""
July / 13 / 2019
ሀምሌ / 6 / 2011

✍ከወንድም meqsud muhammed

#አሰላሙ_ዐለይኩም

t.me/meqsud_ibn_muhammed

                   
                  


ሰለፊይ ማለት ያልተበረዘውንና ጤናማውን የረሱል ሱለላህ አለይሂ ወሰለም እና የሶሀቦቺን የሰለፎችን ( ቀደምቶችን ) መንገድ መከተል ነው ፡፡
======
=============================
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ ፡፡
~~~~~~
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ነጥብ አንድ
~~~~~~

➊ ሰለፊይ ማለት ምን ማለት ነው ..?
.
➋ እራስን ሰለፊይ ብሎ መጥራት ይቻላል ..?
.
➌ እራስን ሰለፊይ ብሎ መጥራት ለምን አስፈለገ ...?
.
➍ ሰለፊይ የሚለው ስያሜ ይከፋፍላል ..?

በቅድሚያ ፦ ይህንን ሀዲስ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ፡፡

>
ትርጉሙም ፡~
-----------------

አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ ነብያችን ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ልቡ ላይ የብናኝ ያህል ኩራት ያለበት #ጀነት_አይገባም የዚህኔ አንድ ግለሰብ ( ያ ረሱለሏህ ) ከኛ መካከል ልብሱና ጫማው ምርጥ እንዲሆንለት የሚፈልግ አለ ፡፡ [ ይህ ኩራት ነውን ..? ]
.
ረሱል ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) -

> ብለውኛል ፡፡ [ ማለቷ ተዘግቧል ]
"
"
"
በዚህም መሰረት ሰለፊይ ማለት ነብያችን ሰሀቦችን ታቢዒኖችንና አትባዑ ታቢዒን ብሎም ከዛ በኀላ ያለፉ ምርጥ አዒማዎችን የሚከተል ማለት ነው ምክንያቱም ፦ ሰለፊይ ማለት ሰለፎችን የሚከተል ማለት ነውና ፡፡
"
"
"
ነጥብ ሶስት
~~~~~~~

➋ እራስን ሰለፊይ ብሎ መጥራት ይቻላል .?
( ለተባለው መልሱ )
"
"
አንድ መቶ አስራ አራቱን የቁርዐን ምዕራፎችንና ለቁጥር የሚታክቱትን ሀዲሶች ከላይ እስከ ታች ብትመለከቱ አንድም ቦታ ላይ ሙስሊም ከሚለው ስያሜ #በተጨማሪ ( ልብ በሉ በተጨማሪ ) ሌሎችን ስያሜዎች መጠቀም አይቻልም የሚልን አንቀፅ አታገኙም ይልቁንስ በተቃራኒው እራስን #በተጨማሪ ስሞች መሰየም እንደሚቻል መረጃዎች በሽ ናቸው ፡፡
ለዚህም መረጃዎቹ በአይነት ተከፍለዋል ፡፡

"
"
ነጥብ አራት
~~~~~~~~
"
"
➊ ) ከቁርዐን ፦ በቁርዐን ውስጥ ከሙስሊምም ባሻገር ምርጥ ሙዕሚኖችን አላህ በተለያዩ ስያሜዎች ጠርቷቸው እናገኛለን ለዚህም በግንባር ቀደምትነት #አስሀቡል_ካህፍ ( የዋሻው ባለቤቶች ) እና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ስሞች ይገኛሉ ፡፡
"
"
➋) ከሀዲስ ፦ ከላይ የተመለከትነው ነብያችን እራሳቸውን #ሰለፍ ብለው መጥራታቸውና ሰሀቦች ፦
- አህሉል በድር
- በይዐቱ ሪድዋን
- ሙሀጂር
- አንሷር
ተብለው ተጠርተዋል ይህም ተጨማሪ ስያሜዎችን መጠቀም እንደሚቻል ያሳያል ፡፡
"
"
"
➌) ከዑለሞች ፦ ጥቂት የማይባሉ ዑለሞች እራስን ሰለፊይ ማለት እንደሚያስፈልግ ከመጥቀሳቸው ባሻገር #አህለ_ሱና_ወልጀመዐ የሚለውን ስያሜ በየ ንግግራቸውና ኪታባቸው ላይ ለቁጥር በሚታክት መልኩ ሰፍሮ እናገኛለን
ይህም ተጨማሪ ስሞችን መጠቀም እንደሚያሳይ ፍንትው አድርጎ ያሳያል ፡፡
"
"
"
➍) አራተኛው የመረጃ አይነት #ቂያስ ነው ፡፡ በመጀመሪያው የማስረጃ አይነት ላይ እንደተመለከትነው አንድም የቁርዐን ዐንቀፅም ይሁን ሀዲስ ስያሜን የሚከለክል ባለመኖሩ የስያሜ መሰረት #የተፈቀደ መሆኑን እንረዳለን ፡

"
"
"
ነጥብ አምስት
~~~~~~~
"
"
"

ማሳያ ፦
---------
.
- የሚያርስ = አራሽ
- የሚማር = ተማሪ
- የሚሰራ = ሰራተኛ
- የኢልም ባለቤት = አሊም
- ሰለፎችን የሚከተል ደግሞ = ሰለፊይ ይባላል ፡፡
"
"
"
➌ ይህንን ስያሜ መጠቀም ለምን አስፈለገ ..?( ከተባለ መልሱ )
"
"
ነብያችን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙዐዊያ በዘገበው ሀዲስ ላይ የመፅሀፍ ባለቤቶች በዲናቸው ላይ 72 ተከፋፍለዋል ይህ የኔ ዑማ ( ሙስሊሙ ) ደግሞ 73 ቦታ ይከፋፈላል አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው አሉ ፡፡

የዚህኔ ሰሀቦች የትኛዋ ናት ሰላም የምትሆነው ሲሉ ጠየቁ
"
"
ነብያችንም ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ዛሬ እኔና እናንተ ( ሰሀቦቼ ) ያላችሁበት መንገድ ናት ብለው መለሱላቸው ፡፡
"
"
ከላይ ለመመልከት እንደሞከርኘው ፦ ሰሀቦችና ነብያችን ደግሞ #ሰለፍ ይባላሉ እነሱን የተከተለ ደግሞ እራሱን በዚህ ስም ባይጠራም #ሰለፊይ ይባላል ፡፡
"
"
አሁን ባለንበት ተጨባጭ ፦ የተለያዩ የፈጠራ ቡድኖችና መንገዶች እንደ መብዛታቸው የራስን አቋም ማንፀባረቅና ግልፅ ማድረግ ባስፈለገ ጊዜ እኔ ነብያችንና ሰሀቦች ከዛም በኀላ በመጡት ደጋግ ባሮች መንገድ ላይ የምመራ #ሰለፊይ ነኝ ይላል ፡፡
"
"
"
ልብ በሉ ፦ ሰለፊይ የሚለው ስያሜ እንደ ጠዋትና ማታ ዚክር ምላሳችን እስኪዝል የምንለፍፈውና እንደ መንግስት ተቋማት ሲነጋና ሲመሽ የምናውለበልበው ባንዲራ አይደለም ይልቁንስ ፦ አቋምን ግልፅ ማድረግ በሚያሻ ወቅት ብቻ መጠቀሙ ተገቢ ነው ፡፡
"
"
" ነጥብ ስደስት
~~~~~~~
"
"
"
➍ ሰለፊይ የሚለው ስያሜ ይከፋፍላል ? ( ለተባለው መልስ )

ይህንን ጥያቄ የዘመናችን ስመ ጥርና አንጋፋው ዐሊም ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አል ፈውዛን ተጠይቀው አዎ ሰለፊይ ይከፋፍላል በሀቅና ባጢ


ሁላችንም እራሳችን እንፈትሽ ስንቶች ናቸዉ ኢስላማዊ ድራማ "ነሺዳ"ፊልም"ኮሚዲያን እያሉ ወንዶች ሴቶች ሆነዉ የሚቀርቡት በተመሳሳይ ሴቶች እንደዛዉ አስገራሚ ደግሞ ለነዚህ ሙብተዲዎች ጥብቅና የምትቆሙ ወንድምና እህቶች አሏህን ፍሩ አሏህ ሁላችን ትክክለኛዉ የሰለፎች መንገድ ይምራን

t.me/meqsud_ibn_muhammed


ከሰለፎች አንዱን እንዲህ አሉት!!

አንድ ዳቦ አንድ ዲናር ገባ አሉት እኔ ይህ አያሳስበኘም አንዱ የገብስ ፍሬ አንድ ዲናር ቢገባ እንኳን አያሳስበኘም!!!
አላህ እንዳዘዘኘ አመልከዋለሁ እሱ ደግሞ ቃል እንደገባልኝ ይረዝቀኛል አለ ፡፡
በአላህ ላይ ጠንካራ ተወኩል አላቸው ቀደምቶች(ሰለፎች) አላህ ይዘንላቸው

t.me/meqsud_ibn_muhammed




by meqsud muhammed ሱና ,,,,,,,,,,,,,,,.pdf
123.7Kb
የነቢያት ተልዕኮ የሆነዉ ተዉሂድ አዉቀዉ ሽርክን እንዲ ጠነቀቁ ትክክለኛ የመልክተኛዉ ﷺ ሱና አዉቀዉ ከቢዳዐ እንዲርቁ በአሏህ መልካም ፍቃድ ይሔ አጠር ያለች pdf download በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ ለሌሎችም ሼር ያደርጉ

ከወንድም meqsud muhammed

t.me/meqsud_ibn_muhammed


ተዉሂድ የሁሉም ነቢያት ተልዕኮ
========================
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩሀህ በጣም አዛኝ በሆነው ፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አላህ በተለየዩ ዘመናት በርካታ ነቢያትን ልኳል እነዚህ ነብያት ለተላኩላቸው ሕዝቦች ያስተምሩ የነበረው የአላህን ብቸኛ አምላክነት የሚገልፀውን (ተውሂድ አል ኡሉሂያ) የተውሂድ ክፍል እንደነበረ ቁርአን ይነግረናል፡፡
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡›› (አል ነህል 36)
በሱረቱል አንቢያ ውስጥም አላህ ወደየህዝቦቻቸው ስለላካቸው መልዕክተኞች ለነቢያችን ሲገልፅላቸው እንዲህ ይላል፡-
‹‹ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡›› (አል አንቢያ 25)
በየዘመናቱ ወደ ሕዝቦቻቸው የተላኩ ነቢያት በአቂዳ ዙሪያ ጠንከር ያለ የፀና አቋምና እምነት እንዲኖራቸው ነበር፡፡
ሕዝባቸውን ያስተምሩና ይመክሩ ያስጠነቅቁና ይዘክሩ የነበረው ህዝቡ ግን ጌታቸው ለእርሱ የዋለውን ውለታና አመስግነው መቀበል ሲገባቸው አስተባበሉ በአመፀኛነታቸውም ገፉበት፡፡
በአቂዳ ዙሪያ ባሉ የዲን ጉዳዮች ማወላወል ፈፅሞ የለም፡፡
የሐቀኛ ምዕመናን የአህሉ ሱና ወልጀመዓ የሕይወት መመሪያ የሆነውን ቁርአንንና የነብዩን ሱና ሙሉ በሙሉ መከተል ብቻ ነው በየዘመናቱ የተላኩ ነቢያትም ያስተማሩት ይህንኑ ነው፡፡

"""""""""""""""""""""""
July / 9 / 2019
ሀምሌ / 2 / 2011

✍ከወንድም meqsud muhammed

#አሰላሙ_ዐለይኩም

t.me/meqsud_ibn_muhammed

                   
                  


አንድነት
~~~~~~
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ፡፡
============================

َበአላህ የእምነት ገመድ ተያያዙ አትለያዩም﴿ (አል ኢምራን 103)

የአንድነት መሰረቶቹም ቢሆኑ ፍጹም ግልጽና የማያሻሙ አንኳር ነጥቦች ናቸው::
አላህን በብቸኝነት ማምለክ እንዲሁም በእርሱ ላይም ማንንም አለማጋራት አለቀ ደቀቀ::

ይህንን ነጥብ ስታብራራው ግን ብዙ ይበልጥ አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችን ትዳስሳለህ::
ስለዚህ አወጣህም አወረድክም በዚህ ምሰሶ ዙሪያ የጠብታ ልኬት ክፍተት ከተፈጠረ በ'ይፈርሳል' ስጋት በየዋህነት ከተዳፈነ አንድ በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ነገር አለኝ:: እርሱም ዛሬ ይህንን መሰረት አስመልክቶ ስንዝር የተለያየንባቸው ነጥቦች ነገ አጋጣሚውን ሲያገኙ የምስራቅና የምዕራብን ክፍተት ያህል እንደሚያራርቁን ተረዳ::
በመሆኑም የአንድነታችንን መዘውር የሳቱ እሳቤዎች ጋር በፍጹም አንድ አንሆንም (ፍላጎት ሳይሆን እጣ ፈንታችን ነውና) ባይሆን እንደ ወጉ እንደ ልማዱ ነጥቦችን እየፈተሽን እንወያይባቸዋለን እየሞረድን እየቀረጽን ክፍተቶችን እናጠባለን ብሎም እናጠፋለን::
በተፈተሹና በተሞረዱ ቁጥር ዳር እና ዳር የሚመስሉ ግንዛቤዎቻችን ይበልጥ አንድነትን እያጎሉ ይመጣሉ::
ስለዚህ አንድ አይነት አመለካከት እንድናዳብር በተጠየቅንበት አጀንዳዎች ላይ 'ኸረ እንዳንበታተን ብለህ አትበል ምክንያቱም ይሔንን የጥሜት ፊረቆች አካሄድ ነዉ በዋነኛነት የኢኽዋኖች ::
ይልቁንም ሀሳብህን አቅርብ እምነትህን አሳይ ምናልባትም ከመዘውሩ የሸሸኸው አንተ ብቻ
ልትሆን ትችላለህና ::
በግርድፉ እንዲህ ልበል በተውሂድ ላይ መወያየታችን መሰረታዊ ስህተቶችን መጠቆማችን እንዲሁም ሽርክና ዘመዶቹን በስፋት መዳሰሳችን ፍጹም አንድነት የሚያጎናጽፉን ነጥቦች ናቸውና አትስጋ ኢኽዋኖች እንደ ሚሉት አንድነት የሚንድ አይደለም ይሔ እዉነታኛ አንድነት የሚያጎናጽፉ ነዉ ::
ዳሩ ከዚህ ውጪ የተመሰረተ አንድነት ለባለቤቱ እያደር ብቸኝነትን እንጂ አያወርሰውም ስለዚህ አሏህ በተዉሂድ በሱና አንድ ሆኑ አለን እንጂ ከአሏህ ዉጭ የሚገዛ ከእሱ አንድ አንድ ሆኑ ብሎ አላዘዘንም ነቃ የአሏህ ባረያ ትክክለኛ አንድነት በተዉሂድ ብቻ ነዉ ::
~~~~
እውነትን ከልብ በመሻት ለማስረጂያ እጅ በመስጠት እንዲሁም ስሜታዊነትን በማስወገድ የሚደረግ ውይይት ፍቱን መድሀኒት ነው ህይወት ከቆመው ህዝብ ጋር ብቻ ሳይሆን በጀነት ከታጩ ሙታኖች ጋርም በማይበጠስ የአንድነት ገመድ
ያስተሳስረናልና

አሏህ እዉነተኛ አንድነት ይሰጠን በተዉሂድ በሱና አንድ ያርገን ከጠሞ አጥማሚዎች አሏህ ይጠብቀን እነሱም አሏህ ይምራቸዉ ፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
"""""""""""""""""""""""
July / 8 / 2019
ሀምሌ / 1 / 2011

✍ከወንድም meqsud muhammed

#አሰላሙ_ዐለይኩም

t.me/meqsud_ibn_muhammed

                   
                  


ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምሩም

በኡስታዝ ሳዳት ከማል (ሀፊዘሁላህ)

t.me/meqsud_ibn_muhammed


ኢብኑ ተይሚይያህ እንዲህ አሉ ፦

«ከሰዎች አብዛኞቹ ንግግሮችን በሰዎች ነው የሚመዝኑት ታዲያ አንድን ሰው የላቀ ነው ብለው ካመኑ ንግግሮቹን ይቀበላሉ ምንም እንኳ ከንቱ እና ቁርኣንን እና አስሱናህን የተቃረነ ቢሆንም።»

[ጃሚዕ አልመሳኢል 7/ 463]

ሰዎች በሃቅ ይመዘናሉ እንጂ ሃቅ በሰዎች አይመዘንም እራሳቸውን ወደ ሰለፎች ያስጠጉ ሰዎችም በሰለፎች ንግግር ይመዘናሉ እንጂ ሰለፎች በእነርሱ አይመዘኑም።
አሏህ ሆይ! ትክክለኛ ሃቅን ተከታዮች አድርገን

✍ ከወንድም t.me/meqsud_ibn_muhammed


ሱኒ ነኝ በላቸው
======================
===========
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
===========
========================
ብለው ሲያነሳሱህ ወደ ውጭ እንውጣ
የበርጫ እንበል ኸምርም እንጠጣ
በጊያችን ጠብሰን ከብዙው እንውጣ አቦ ዘና እንበል ምን ታካብዳለህ
ሁሌ ሱና ሱና መስጂድ ታበዛለህ
ና ዛሬን ተደሰት ነገን ትደርሳለህ
ብለው ሲያነሳሱህ ቢያጓሩ ከፊትህ
የእብሊስን ወህይ ሲያስተላልፉልህ
ወላሂ አትስማ በላቸው ሱኒ ነኝ
ከሰሃቦች ውጪ ሞዴልም የሌለኝ
ሀላል ነው ህይወቴ ሃራም የማልመኝ
አዎን ንገራቸው ሙስሊም መሆንህን
በሰለፎች ጎዳና ሁሌም መጓዝህን
ፍንክች እንደማትል በግልፅ ንገራቸው
ሃቅ ሀቁን ነግረህ እዛው ምከራቸው
ብለህ ንገራቸው
ቅጠልም አልበላም እሱ የፍየል ነው
በግም አያሻኝም እረኛም አይደለው
አብሬያቹው አልሄድ እኔ ልሁን ፋራ
ሱናዬን ልከተል አልክሰር ባኺራ
ተው ተመለሱ ብለህ ንገራቸው
አሻፈረኝ ካሉ ከባሰ ሸራቸው
ብለህ በላቸዉ
እናንተ ቀጥሉ እኔ ግን ወራጅ ነኝ
ወራጅ ነኝ አዚህ ጋ አሁን አቁምልኝ
አዎን ንገራቸው ሱኒይነትክን
ለአላህ ምትኖር ተቅይ መሆንህን
በነብዩ ሱና ተብቃቂነትህን።
~~~~~~~~~~
July / 6 / 2019 e.c
ሰኔ / 29/ 2011 e.c
""""""""""""""""""""""""""""""""
t.me/meqsud_ibn_muhammed


ሰለፎች የመልክተኛውን ሱናን አጥብቀን እንድንይዝ ሀቅን ለሚፈልግ ሲሉ መክረውናል ሶፍያን አሰውሪ
ረሂመሁሏህ
የሰውነትህን ቆዳ በጥፍርህ ማከክ ቢኖርብህ ቁርአንና ሀድስን መረጃ አግኝተህ ተገድፈህ ካልሆነ በቀር እንዳታክ ይላሉ ኢማሙ ማሊክን አላህ ይማራቸው፡፡
የዚህ ህዝብ መጨረሻ የሚስተካከለው የመጀመሪያው በተስተካከለበት ብቻ ነው ይላሉ።
አላህ ሆይ የረሱልን ሱና በማንኛውም ወቅት ከሚተገብሩትም አድርገን!

t.me/meqsud_ibn_muhammed

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

2 274

obunachilar
Kanal statistikasi