መረጃ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


" መረጃ አይናቅም አይደነቅም ።"
♦️በየጊዜው ከተለያዩ የዜና ጣቢያዎች እና የዜና ቴሌግራም ቻናሎች የተሰሙ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ !!!!!!
በተጨማሪም ስለ
#ቴክኖሎጂ ነክ
#ጤና ነክ
#ትምህርት ነክ መረጃዎችን ያገኛሉ።
#Join , #Share
🚩** our second Channel👇👇👇
@ChristianDoc

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


#ጤናችን

የኩላሊት ጠጠር(kidney stone)

የኩላሊት ጠጠር በኩላሊትዎ ዉስጥ ትናንሽና ጠንካራ የሆኑ ማዕድናት ሲጠራቀሙ የሚመጣ ችግር ነዉ፡፡ ድንጋዮቹ የተሰሩት ከማዕድናትና አሲድነት ካላዉ ጨዉ ነዉ፡

የህመሙ ምልክቶች(signs and symptoms)

በአብዛኛዉን ጊዜ የኩላሊት ጠጠሮች በኩላሊትዎ ዉስጥ ካልተዘዋወሩ አሊያም ወደ ዩሬተር(ሽንትን ከኩላሊትዎ ወደ ፊኛ የሚወስደዉ ቱቦ) ካልወረዱ በስተቀር ምንም አይነት የህመም ምልክት አያሳዩም፡፡ ስለሆነም የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡
• ጎንና ጀርባዎ ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር
• ወደ ታችኛዉ የሆድዎ ክፍልና ብሽሽት የሚሰራጭ ህመም መፈጠር
• ሽንት ሲሸኑ ህመም መኖር
• ቀይ ወይም ቡናማ የመሰለ የሽንት መልክ መከሰት
• ጉም የመሰለ ወይም ሽታ ያለዉ ሽንት መዉጣት
• ማቅለሽለሽና ማስታወክ
• በተደጋጋሚ ለመሽናት መፈለግ
• ከተለመደዉ ጊዜ/ብዛት በላይ ሽንት መሽናት
• ኢንፌክሽን ካለ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት መኖርና
• በጣም ትንሽ መጠን ያለዉ ሽንት መሽናት ናቸዉ፡፡
በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰተዉ ህመም ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ጠጠሩ ወደ ሌላ ቦታ ከሄደ/ ከተዘዋወረ ህመሙ ሊጨምር ይችላል፡፡

የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር መከላከል(to prevent kidney stone formation)

የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና መድሃኒቶች ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታሉ፡፡
• በየቀኑ በቂ ፈሳሽ/ዉሃ መጠጣት፡- ሞቃታማና ደረቅ የአየር ንብረት ዉስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም በመደበኛ ሁኔታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ ሽንት በበቂ መጠን እንዲመረት/እንዲወጣ ፈሳሽ በበቂ መጠን መጠጣት ይመከራል፡፡ ሽንትዎ ነጣ ያለና ንፁህ ከሆነ ዉሃ በበቂ መጠን እየወሰዱ መሆኑን ያሳያል፡፡
መጠነኛ የኦክዛሌት/ oxalate ይዘት ያላቸዉን የምግብ አይነቶች ማዘዉተር፡- የካልሲየም ኦግዛሌት ድንጋይ እየተፈጠረ ካለ ወይም ተጋላጭነት ካለዎ እንደ ስኳር ድንች፣ ቆስጣ፣ ኦቾሎኒ፣ ሻይ፣ ቼኮሌት፣ የአኩሪ አተር ተዋፅኦዎችና ቀይስር ያሉምግቦች በኦግዛሌት የበለፀጉ ስለሆኑ/ከፍ ያለ የኦግዛሌት መጠን ስላላቸዉ/ እነዚህን ምግቦች መመገብ መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
• የጨዉና የፕሮቲን ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ/ማዘዉተር፡- የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን እንዲሁም ከእንስሳት ተዋፅኦ ዉጪ ያሉ የፕሮቲን ምንጮችን መመገብ ( ለምሳሌ ባቄላና አተር)
• የካልሲየም ይዘታቸዉ ከፍ ያለ ወይም በካልሲያም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ነገር ግን የካልሲየም ሰፕሊመንት(ተጨማሪ እንክብል) ሲወስዱ ጥንቃቄ ያድርጉ፡- በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠር እድሉን አይጨምሩትም፡፡ የህክምና ባለሙያዎ ካልከለከለዎ በስተቀር የካልሲየም ይዘታቸዉ ከፍ ያሉ ምግቦችን መመገብ ይቀጥሉ፡፡ ነገር ግን የካልሲየም ሰፕልመንቶች ከኩላሊት ጠጠር መከሰት ጋር ተያያዥት/ግንኙነት ስላላቸዉ ከመዉሰድዎ በፊት የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች (risk factors for kidney stone)

• በዚህ በፊት በቤተሰብዎ ወይም በራስዎ ላይ መሰል ችግር ከነበረ
• የፈሳሽ እጥረት/ ድርቀት ካለ፡- በየቀኑ ፈሰሽ በበቂ መጠን መዉሰድ ካልቻሉ ለኩላሊት ጠጠር ይጋለጣሉ፡፡ ከሌሎቹ ይልቅ በሞቃታማ የአየር ንብረት ዉስጥ የሚኖሩና ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያልባቸዉ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡
• የተወሰኑ የምግብ አይነቶች፡- የፕሮቲን፣ የሶዲየምና የስኳር ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ለተወሰኑ የኩላሊት ጠጠር አይነቶች ይጋለጣሉ፡፡
• ዉፍረት፡- ከመጠን ያለፈ ክብደት ያላቸዉ ሰዎች ላይ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠሩ ጉዳይ ከፍተኛ ነዉ፡፡

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ(when do you consult health professional)?

የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ባስቸኳይ ያማክሩ፡፡
• ህመሙ በጣም ከፍተኛ ከሆነና መቀመጥ ያለመቻል ወይም ምቾት የሚሳንዎ ከሆነ
• ህመሙን ተከትሎ ማቅለሽለሽና ትዉከት ከመጣ
• ከህመሙ ጋር ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ካለ
• ከሽንትዎ ጋር ደም ከመጣ
• ሽንትዎን መሽናት ከተቸገሩ

❇️ሌሎች የጤና መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇👇👇

@merejalehulu


የመንግስት ምስረታ የሚካሄድበት ቀን ታወቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጪው መስከረም 24 ቀን 2014 ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ እንደሚካሄድ ዛሬ አስታውቋል።

@merejalehulu


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መሪዎቹ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያም ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን በጠበቀ መልኩ የሁለትዮሽና የቀጠናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መነጋገራቸውም ታውቋል።

@merejalehulu


በአምቦ ከተማ ግጭት ለማነሳሳት የተደረጉ ጥረቶች ሳይሳኩ መቅረታቸው ተነገረ ‼

የአምቦ ከተማን ለማወክ የሚጥሩ አካላት ህገ ወጥ የሆነ ድርጊት በመፈፀም ለማነሳሳት ጥረቶችን እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል ፡፡

በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር በአምቦ ከተማም እንዲፈጠር ለማድረግ ቢጥሩም ፤ በህዝቡ እና በፀጥታ ሃይሉ አማካይነት ሳይሳካ መቅረቱን የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳህሉ ዲሪብሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ግጭት በመፍጠር ህዝቡን ለማነሳሳት ከመጣር ባሻገር በከተማዋ ችግር እና አለመረጋጋት የተፈጠረ አስመስለው ወሬ የሚያናፍሱ በርካቶች እንደሆኑ ከንቲባው አንስተዋል፡፡

ለሶስት አስርት ዓመታት ለተቃረበ ጊዜ የከተማይቱ ነዋሪዎች የቀደመውን ስርዓት በመጣል ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ያሉት ከንቲባው ፤ በአሁን ሰዓት ግን ሙሉ ትኩረታችንን ልማት ላይ አድርገን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓትም የህዝቡንና የከተማይቱን ደህነንት ለመጠበቅ በጥንቃቄ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ አቶ ሳህሉ ድሪብሳ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ

@merejalehulu


ፈረንሳይ 10 ሚሊዮን ክትባቶች ወደ አፍሪካ ለመላክ እየሰራች ነው ተባለ!

የፈረንሳይ መንግስት ከ አፍሪካ ህብረት ጋር በፈጠሩት አጋርነት በኩል የአፍሪካ ህብረት አባል አገራቶች ተጨማሪ 10 ሚሊዮን የአስትራ ዜኒካ እና የፋይዘር ኮቪድ 19 ክትባቶችን በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ ያገኛሉ።

ክትባቱ ከአፍሪካ ቫክሲን አኩዊዚሽን ትረስት (AVAT) እና ከ ኮቫክስ ቫክሲን ኢኒሼቲቭ ጋር በመሆን የሚሰራጭ እና የሚከፋፈል ይሆናል።

የAVAT ኢኒሼቲቭ የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት ከሚፈልጉት የክትባት መጠን ውስጥ ቢያንስ 50% የሚሆነውን በጨረታ መልክ እንዲገዙና እንዲጠቀሙ የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪም AVAT ከ ኮቫክስ ኢኒሼቲቭ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የቀረውን 50% በእርዳታ መልክ እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል።

AVAT ከ አለም ባንክ አጋሮች ጋር በመሆን በቀጣዩ አመት መስከረም ላይ 3 ቢሊዮን ዶላር በሚሆን ወጪ 400 ሚሊዮን የሚሆነውን ወይም አንድ ሶስተኛ የሚሆነውን የአፍሪካ ህዝብ ለመከተብ በቂ የሆነ ክትባት በእጁ ላይ ይገኛል።

ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አፍሪካ የክትባቱ እኩል ተጠቃሚ እንድትሆን ትልቅ ተነሳሽነት የነበራቸው ሲሆን የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት እንደ AVAT አይነት ያሉ ተቋማቶችን እንዲመሰርቱም ከየትኛውም ሀገር መሪ የበለጠ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው።

via - AddisZeybe
@merejalehulu


ታሊባን አሜሪካ ከአፍጋኒታን ለቃ መውጣቷን ተከትሎ 'ነፃ ሀገር' ሲል አውጇል

ታሊባን የአሜሪካ ጦር ከ 20 ዓመታት ወረራ በኋላ መውጣቱን እንደ “ታሪካዊ ጊዜ” በመግለፅ አፍጋኒስታን “ነፃ እና ሉዓላዊ” ሀገር ናት ብሏል።

የመጨረሻው የአሜሪካ ወታደሮች ከሀገር ሲወጡ የታሊባን ተዋጊዎች ዛሬ የካቡልን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረዋል።

ይህንን አጋጣሚም ለማክበርም የካቡል ሰማይ ሌሊቱን በተኩስ እና በርችት ሲናወጥ አንግቷል እንደ አልጀዚራ ዘገባ፡፡

የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢምሬት ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር እንደሆነ አንጠራጠርም።

“አሜሪካ ተሸነፈች… እናም አሁን በሀገራችን ስም ከሌላው ዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን” ብለዋል።

ለአፍጋኒስታኖችም የታሊባን ሀይሎች “ነፃነታችንን እና እስላማዊ እሴቶቻችንን ይጠብቃሉ” በማለት ቃል ገብቷል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ የሆኑት ማሪን ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ ቀደም ሲል የአሜሪካ ወታደሮች ከካቡል እንደወጡ አስታውቀዋል።

“እኛ ለመውጣት የፈለግነውን ሰው ሁሉ አላወጣንም ግን እኔ እንደማስበው ሌላ 10 ቀናት ብንቆይ እኛ ለማውጣት የፈለግነውን ሁሉ እናስወጣ ነበር”ብለዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ወታደሮችን ለቀው እንዲወጡ ነሐሴ 31 ቀን ቀነ ገደብ አስቀምጠዋል።

Via Ethio FM

@merejalehulu


ደብረ ዘቢጥ በመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ቁጥጥር ሥር ሆነች‼️

ደብረ ዘቢጥ ላይ መሽጎ የነበረው የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ተደምስሷል። አሁን ላይ ደብረ ዘቢጥ በመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ቁጥጥር ስር መሆኗን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

Via - ESAT

@merejalehulu


በደቡብ ሱዳን የተጠራውን ተቃውሞ ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

የሀገሪቱ የፖለቲካ አመራሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በደቡብ ሱዳን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ እና የስልክ አገልግሎት እንዲወሰን ተደርጓል። የበይነመረብ ክትትል ላይ የሚሰራው ኔትብሎክስ የአገልግሎት መስተጓጎል እንዳለ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

በዋና ከተማዋ ጁባ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ሀይል ተቃውሞ ከተነሳ በሚል ተሰማርቶ ይገኛል።የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረበው ቡድን ራሱን ሕዝባዊ ጥምረት ለሲቪል እርምጃ ብሎ የሚጠራ ሲሆን ፕሬዝዳንቱን እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሪክ ማቻር የደቡብ ሱዳንን ሕዝብ ተስፋ አስቆርጠዋል ሲል ቡድኑ ከሷል።የጁባ ከተማ ከንቲባ ካሊስቶ ላዶ ፋውስቲኖ አይደለም የተቃውሞ ሰልፍ በከተማው ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አስተዳደራቸው እንደማይፈቅድ ተናግረዋል።

የተቃውሞ ሰልፉን የሚጠራውን ቡድን የሰላም ስምምነቱን የሚቃወሙ ሰዎች ናቸው በማለት ከንቲባው ላዶ ገልፀዋል። ከቡድኑ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተከሰሱ በርካታ የመብት ተሟጋቾች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

@merejalehulu


#ሰበር

አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ሙሉ ለሙሉ መዉጣቷን ተከትሎ በታሪኳ ረጅሙ የተባለዉ ጦርነት በይፋ ተጠናቀቀ❗️

መስከረም 11 በአሜሪካ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ዋሽንግተን አፍጋኒስታንን ከወረረች ሃያ ዓመታት ሙሉ ለሙሉ በመዉጣቷ በካቡል የታሊባን ተዋጊዎች በደስታ ወደ ሰማይ ተኩሰዋል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ የባህር ኃይል ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ በፔንታጎን በሰጡት መግለጫ ቀሪ ወታደሮቻችንን አስወጥተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ባይደን ለተፋጠነ ያልተቀናጀ በተባለዉ እርምጃቸው ሪፐብሊካኖች ትላንትና ማታ በባይደን ላይ ትችታቸዉን አጠናክረዋል፡፡ ዛሬ ማለዳ የካቡል ነዋሪዎች ከእንቅልፋቸዉ ሲነሱ የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ሙሉ በሙሉ ወጥታል በታሊባን ቁጥጥር ሥር ሆናለች፡፡

የመጨረሻው የአሜሪካ አውሮፕላን ከአፍጋኒስታን ለቆ መዉጣቱን ተከትሎ ታሊባኖቹ ወደ ካቡል አየር ማረፊያ ሲገቡ የሚያሳይ ምስል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል፡፡የአሜሪካ ጦር ሀገሪቱን ለቆ መዉጣቱን ተከትሎ የታሊባን ደጋፊዎች ደስታቸዉን በመግለጽ ላይ ናቸዉ፡፡

አፍጋኒስታን ሙሉ ለሙሉ ነፃነቷን አገኘች ሲሉ የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቡላህ ሙጃሂድ ሲናገሩ ሌላኛዉ ከፍተኛ የታሊባን ባለሥልጣን አናስ ሃቃኒ እንዲህ ዓይነቱ ታሪካዊ ወቅት ለመመልከት በመብቃቴ ኩራት ይሰማኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

@merejalehulu


በ530 ሚሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የሾላ ገበያ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ህንጻ ግንባታ ከመሬት በታች ያለውን ንጣፍ ተጠናቀቀ

ህንጻው ከመሬት ስር የሚገነቡ ሁለት ወለሎች እና ከመሬት በላይ አምስት ወለሎች ሲኖሩት፣ በአሁኑ ወቅት ከመሬት በታች ያለው የአንዱ ወለል ንጣፍ በመጠናቀቅ ላይ ነው ሲሉ በትራንስፖርት ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

በእያንዳንዳቸው ወለል በአማካኝ 142 የተለያየ መጠን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ሲሆን በአጠቃላይ 1 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም አለው።

መሰረተ ልማቱ ዘመናዊ የደህንነት መቆጣጠሪያ እና የተሽከርካሪ አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎች ተግባራዊ የሚደረጉበት ይሆናል፡፡ ፕሮጀክቱ በሚጠቀመው ቴክኖሎጂ፣ በመሬት አጠቃቀም ዘዴ እና ከሚያስተናግደው የተሽከርካሪ መጠን አንጻር  ሞዴል ፕሮጀክት ያደርገዋል፡፡

አካባቢው የከተማዋ ሁለተኛው ትልቅ የገበያ ማእከል እንደመሆኑ መጠን፣ ፕሮጀክቱ በዙሪያው ያሉትን የመንገድ ዳር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎቶችን በማስወገድ መንገዶች ባላቸው ሙሉ ስፋት ልክ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያስተናግዱበትን አቅም ይፈጥራል፡፡

በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት ከ120 ላላነሱ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ደግሞ ከ80 ላላነሱ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ በ530 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲደረግበት ግንባታውን ዞንግሚ ኢንጂነሪንግ የተባለ ድርጅት መከናወኑን አቶ አረጋዊ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡


 ቤተልሄም እሸቱ

@merejalehulu


በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 284 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

አዲስ አበባን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የአሸባሪው ህወሓት ቡድንን ዓላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 284 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

199 ሽጉጥ ከ2 ሺህ 453 ጥይት ጋር፣ 32 ክላሽንኮቭ 5 ሺህ ከሚልቅ ጥይት ጋር እንዲሁም 4 የጦር ሜዳ መነፅር ከተጠርጣሪዎቹ እጅ፣ ከስራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው መያዝ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት ሃገር የማፍረስ ተልዕኮ የገቢ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያከማቹት ከአንድ ኪሎ ተኩል በላይ ወርቅ እንዲሁም 37 ሺህ 294 ነጥብ 8 ግራም የብር ጌጣጌጥ መያዙን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር የሚጠቀሙባቸው የአዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የማረሚያ ቤትና የራሱ የህወሓት የሽብር ቡድን አልባሳት መያዛቸውንም አስረድተዋል።

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ 123 የምርመራ መዝገብ መደራጀቱንም ነው የገለጹት።የጥፋት ቡድኑ የትኛውንም ዓይነት ሽብር ከመፈፀም ስለማይቦዝን ህብረተሰቡ አካባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

Via EBC
@merejalehulu


ዶክተር ሞውራይስ ታይብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ለሉሲ ቅሪተ አካል መገኘት እና ለሰው ልጆች ዝግመተ ለውጥ መነሻ የሆነውን “ሃዳር” የተሰኘ ስፋራ ያገኙት የስነ-ምድር ተመራማሪ ዶ/ር ሞውራይስ ታይብ ከዚህች ዓለም በሞት መለያታቸውን አል አይን ኒውስ የፈረንሳይ ብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከልን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

የስነ-ምድር ተመራማሪው ዶክተር ሞውራይስ በ86 ዓመታችው ነው ህይወታቸው ያለፈው።

ዶክተር ሞውራይስ ታይብ በአፋር ክልል የሚገኘው እና “ሃዳር” የተባለው ስፍራ በርካታ ጥንተ-ቅሪተ አካል ሊገኝበት እንደሚችል ቀደም ብለው ምርምር ካደረጉ ተመራማሪዎች መካካል አንዱ እንደነበሩ የፈረንሳይ ብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከል ገልጿል።

ተመራማሪው የ3.2 ሚሊየን ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነችው የአውስትራሎ ፒተከስ አፋረንሲስ በልዩ መጠሪያ ስሟ “ሉሲ” ቅሪተ አካል በስነ-ምህዳር ምርምር መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ናቸው።

ሉሲ የተገኘችው እ.ኤ.አ 1974 ሲሆን፤ ዶ/ር ሞውራይስ ታይብ ከባለደረቦቻቸው ጋር በመሆን የሃዳር ስፍራን የሰው ልጆች መነሻ መሆኑን የጠቆሙት 1968 ላይ ነበር።

(አል ዓይን ኒውስ)

@merejalehulu


ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት አገራት አንዷ ናት አሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን!

የቱርክ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ቱርክ በዘርፉ ከቀደምት ከሆኑ እና በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ሶስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ማለታቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል። በሰሜን ምዕራብ ባለች አንድ ግዛት በተከናወነ ወታደራዊ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “ቱርክ ሰው አልባ በሆነው የአየር ላይ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ውስጥ ከሦስቱ እጅግ የተራቀቁ አገሮች አንዷ ሆናለች” ብለዋል።

ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቀዳሚ አገር ለመሆን ቆርጣ መነሳቷን ያስረዱት ኤርዶጋን ቱርክ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማዘጋጀት አለባት ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል። የአገሪቱ ግብ በውጭ ሀገራት የአውሮፕላኖች ተልእኮ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ አጫጭር ማኮብኮቢያዎችን የሚይዙ እና በአውሮፕላን ተሸካሚዎች ላይ ሊያርፉ የሚችሉ የታጠቁ ድሮኖችን ማልማት ነው ብለዋል።

#EthioFM

@merejalehulu


ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ የሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ ‼

የግል ትምህርት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለስልጣን ባወጣዉ የማስፈጸሚያ ማኑዋል መሰረት መስራት እየተገባቸዉ ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡

ይሁንና ለቢሮዉ እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸዉ እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸዉ ፤ በ41 ትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረዉ እገዳ እንዲነሳላቸዉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና አብሮነት እሴቶችን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን ማዕከል በማድረግ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
ጥሪዉን ማቅረቡን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አንዱ በሌላዉ ላይ ጫና የሚፈጥርበት እንዳልሆነ ታውቆ የግል ትምህርት ቤቶች ከደንበኞቻቸዉ ጋር በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሰሩ አሳስቧል።

በቀጣይም ይህን አልፈዉ በሚቀርበዉ ጥቆማ መሰረት ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የክፍያ ጭማሪ የሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች የሚኖሩ ከሆነ ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ቢሮው እንደሚወስድ አሳስቧል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

@merejalehulu


በ2013 በጀት ዓመት 4 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው የህክምና ግብዓቶች መሰራጨቱ ተነገረ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2013 በጀት ዓመት 1.5 ቢሊየን የሚያወጡ የመደበኛና የህይወት አድን 2.6 ቢሊየን በአጠቃላይ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው የህክምና ግብዓቶች ስርጭት መከናወኑን የአዲስ አበባ ቁጥር አንድ ቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሞገስ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ይህም በኤጀንሲው ከሚገኙ 19 ቅርንጫፎች በህክምና ግብዓት ስርጭት ከፍተኛውን ድርሻ መያዙን ያመላክታል ተብሏል።

ከተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል የሞዴል-19 (የዱቤ ሽያጭ አሰባሰብ)98.6 በመቶ ፣ የአመታዊ ቆጠራ በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ፣የሽረት ጊዜያቸው ተነሳሽነት መድኃኒቶችን በማስወገድ ለአሰራር ምቹ ሁኔታዎች መፈጠሩንና ወጣቶች በራስ ተነሳሽነት የስራ አካባቢን ማስዋብ ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጲያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ 500 ሚሊየን ብር የሚያወጡ መከላከያና መመርመሪያ ግብዓቶችን እንዲ 1 ሚሊየን 168 ሺህ 290 ዶዝ የኮቪድ-19 የክትባት መድኃኒቶችን ለተለያዩ ጤና ተቋማት ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

@merejalehulu


ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ያደረጉ 58 የንግድ ድርጅቶች ማሸጉን የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ ።

በ ጉራጌ ዞን ምክንያታዊ  ያልሆነ የዋጋ  ጭማሪ እያደረጉ  በሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ሲሆን መምሪያው  ችግሩን ለመቅረፍ በዞኑ በሚገኙ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤቶች የሚመራና ሌሎችም ባለድርሻ   ተቋማትን ያሣተፈ የዋጋ ማረጋጋት  ግብረ-ኃይል አቋቁሟል።

የመምሪያው  ኃላፊ አቶ መሀመድ  አማን ግበረ-ኃይሉ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት  የዋጋ  ጭማሪው ምክንያታዊ  አለመሆኑን   በመረጋገጡ  ህጋዊ አርምጃ  መውሰድ  መጀመሩን ገልጸዋል፡፡58 የተለያዩ የእህልና የሸቀጣሸቀጥ መጋዘኖች የማሸግ  ስራ የተሰራ ሲሆን ከ66 በላይ  የንግድ ድርጅቶች  ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ከአንድ ሺ በላይ  የሚሆኑት ደግሞ   ወቅታዊና ትክክለኛ  የዋጋ ተመን እንዲለጥፉ ተደርጓል።

እርምጃው  የተወሰደው  በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፣ በሞህር አክሊል ወረዳ ፣ በገደባኖና ጉታዘር ወለኔ ወረዳና በሌሎች በዞኑ አካባቢዎች መሆኑን  የገለጹት አቶ መሀመድ    እርምጃ መውሰድ ከተጀመረ ወዲህ  አንጻራዊ  መሻሻሎች  መኖራቸውን  ጠቁመዋል ።

እንደ መንግሥት ገበያን ለማረጋጋትና  ህብረተሠቡን በከፍተኛ ደረጃ  እየተፈታተነ ያለውን  የኑሮ ውድነትን ችግር ለመቀነስ   ቀጣይነት ያለው ሰራ ስለሚሰራ ህብረተሠቡም እነዚህን ህገ ወጦችን  በአካል በየደረጃው  ለሚገኙ ንግድና ገበያ  ጽህፈት ቤቶች ወይም ባሉበት ሁነው በነፃ የስልክ መስመር በ8034 መረጃ በመስጠት የዜግነት  በግዴታውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


በበረከት ሞገስ

@merejalehulu


የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በተጠናቀቀው 2013 ዓመት ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ገቢ የተሰበሰበው በዋናነት ከውሃ ሽያጭና ከሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች መሆኑን በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ካቀደው ውስጥ 1.3 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል፡፡

የገቢ አሰባሰብ ላይ ትልቅ ችግር  የሆነው ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚዎች በወቅቱ የአገልግሎት ክፍያቸውን ያለመፈጸም ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ባለስልጣኑ በ2013 በጀት አመት ብቻ ለረጅም ጊዜ ውዝፋቸውን ያልከፈሉ ከ52 ሺ በላይ ደንበኞች የውሃ አገልግሎት በማቋረጥ ከቅጣት ጋር ሰብስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ለደንበኛው የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ለማዘመን ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ከመዘርጋት ባለፈ ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የውሃ አገልግሎት ክፍያ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በኩል እንዲሆን ማድረጉ ይታወሳል ፡፡

ሳምራዊት ስዩም

@merejalehulu


በርካታ አይነትና መጠን ያላቸው የብረት ክምችት በኢኮኖሚ አሻጥር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል ተያዘ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 አስተዳደር ለግንባታ አገልግሎት ሊውሉ የሚገባቸው ፌሮና ብረታ ብረቶች የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተዋቀረው ግብረ-ኃይል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።

ለግዜው በገንዘብ ለመተመን ያልተቻለ ለረዥም ግዜ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የተከማቹና የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ፌሮና ብረታብረቶች መያዛቸውን ነው የተገለጸው።

በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ወረዳ 2 አስተዳደር ከግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከማችተው የነበሩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለው ለህብረተሰቡ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲሰራጭ የተደረገ ሲሆን ገንዘቡ በአ.አ ፋይናንስ አካውንት ገቢ እንዲሆን ግብረ-ሀይሉ ወስኗል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር ግብረ-ሀይሉ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ምርቶች ውስጥ መኮሮኒ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ምስር እና ሌሎች ምርቶች የሚገኙበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ860 ኩንታል በላይ የሚገመት ምርቶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደ አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር እጅግ ከፍተኛ የሆነ የብረታ ብረት አይነቶችና በቢሊዮን የሚገመት ዋጋ ያላቸውን የብረታ ብረት ውጤቶች መያዝ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል።

@merejalehulu


በጦርነት ምክንያት 7 ሺህ ትምህርት ቤቶች በከፊልና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተገለፀ!

ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት 7 ሺህ ያህል ትምህርት ቤቶች በከፊልና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።ይህ የተገለፀው ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።የትምርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አሸባሪው ቡድን በትግራይ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችንና ከ48 ሺህ በላይ መምህራንን ከትምህርት ስርዓት ውጭ አድርጓል ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም ተማሪዎችን ወደ ጦርነት እየማገደ መሆኑንም ተናግረዋል። ቡድኑ ግጭቶችን ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በማስፋፋት ትምህርት ቤቶችን አውድሟልም ነው ያሉት።ባለፈው አንድ ወር ብቻ በአፋር ክልል 88 ሺህ ተማሪዎች ይማሩ የነበሩባቸው 455 ትምህርት ቤቶች በአሸባሪው ቡድን መውደማቸውን ገልጸዋል።በአማራ ክልል ደግሞ 140 ትምህርት ቤቶችና ሁለት የመምህራን ኮሌጆች ሙሉ በሙሉና በከፊል መውደማቸውን አስረድተዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የውጭ አጋር ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መገኘታቸውም ታውቋል።

@merejalehulu


ሰሜን ኮርያ የኒውክሌር ኃይል  ማብላያን በድጋሚ ልታስጀምር ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

ሰሜን የዮንግባዮን የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ጣቢያዋን በድጋሚ ስራ ልታስጀምር ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአቶሚክ ኤጀንሲ በሪፖርቱ አስታውቋል።በማብላያ ማዕከሉ ውስጥ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ለመስራት የሚረዳው ፕሉቶኒየም እንደሚመረትም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እ.ኤ.አ በ2009 ከሰሜን ኮርያ የሚያደርገውን ምርመራ አቁሞ እንዲወጣ የተደረገ ቢሆንም የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም ግምገማ ማድረጉን ቀጥሏል።ከሀምሌ ወር ጀምሮ የኒውክሌር ሀይል ማብላያው የማቀዝቀዣ ውሃ ፍሰት ተደርጓል።

የዮንግባዮን የኒውክሌት ማርከል የ5 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል።የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን በሲንጋፖር ከተገናኙበት ጊዜ በኃላ በዚህ ማብላያ ላይ ስራ ሲጀመር የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።


በስምኦን ደረጄ


@merejalehulu

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

78

obunachilar
Kanal statistikasi