ከሰነፎች ራቁ!
፨፨፨////፨፨፨
በምትሔዱበት የትኛውም ስፍራ ሊጠቅማችሁ የሚችለውን ይሔን እውነታ እወቁት። አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ፣ ጠቃሚም ሆነ ጎጂ፣ አሻጋሪም ሆነ አሰናካይ በዙሪያችሁ ያለው የትኛውም ነገር ሙሉ በሙሉ እናንተን የመግዛት አቅም አለው። በታታሪዎች ስትከበቡ የመታተር አቅማችሁ እጅጉን ይጨምራል፣ ከብርቱ ሰራተኞች ጋር ስትውሉ ጎበዝ ሰራተኛ የመሆን እንድላችሁ ይሰፋል። በአንፃሩም ከሰነፎች ጋር ስትውሉ፣ የሰነፎችን ምክር ስትሰሙ መጨረሻችሁ ስንፍና ይሆናል። የቸልተኞችን ጎራ ስትቀላቀሉ፣ ከቸልተኞች ጋር ስታብሩ ሄዳችሁ ሄዳችሁ ለምንም ግድ የሌላችሁ ቸልተኛና የዘፈቀደ ሰዎች ትሆናላችሁ። ዓለም ላይ ብዙ አደገኛ ሰዎች አሉ። ከእነርሱም ውስጥ ሰነፍ ሰዎች ግንባርቀደም አደገኛና መጥፎ ሰዎች ናቸው። ምናልባት ፈልገውና ደስ እያላቸው ሰነፍ አልሆኑ ይሆናል ነገር ግን ስንፍናን መርጠው መቀመጣቸው ሳያንስ ሳያውቁትም ሆነ አውቀውት ወደ ሌላው ሰው ማሸጋገራቸው አደገኛ መጥፎ ሰዎች ያደርጋቸዋል። አብዛኛውን ሰነፍ ሰዎች አንድ የሚያደርጋቸው ባህሪ ሁሉም በሚባል ደረጃ ብዙ ያወራሉ፣ የሚሰራን ሰው ማብጠልጠል ይወዳሉ፣ ትቺት ባለበት ሁሉ አሉ፣ በስም ማጥፋት የተካኑ ናቸው፣ የሰውን ተነሳሽነት በመስበር ማንም የሚውዳደራቸው የለም።
አዎ! ምንም ተጨማሪ ጊዜ ማሰብ አያስፈልግም። ወስናችሁ ከሰነፎች ራቁ፤ ቆርጣችሁ ስራ ጠል የሆኑ ሰዎችን ከህይወታችሁ አስወጡ። ማውደልደልና ወሬ ማመላለስ ለእናንተ አይደለም ለእነርሱም አልጠቀመም። በእርግጥ ሰው ስራፈት ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም ለአንዳንዶች ስንፍና በራሱ ስራ ነውና። ቅዱስ መፅሐፍ የሰነፎችን አንድ ባህሪ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፦ "ሰነፎች ግን ጥበብን እና ተግሳፅን ይንቃሉ።" ለእነርሱ አስባችሁ ልትመክሯቸው ብትሞክሩ ካለመስማትም በላይ ይንቋችኋል፣ ይዘባበቱባችኋል፤ ያላችሁን እውቀት ልታካፍሏቸው ብትሞክሩ፣ የተገለጠላችሁንም ጥበብ ልታስተላልፉላቸው ብትጥሩ ከእናንተ ከሚወስዱት ጠቃሚ ነገር በላይ እናንተም መመዘን ይሞክሩ፣ ከትምህርቱ ይልቅ የእናንተን ደረጃና ማንነት ማጣጣልን ይመርጣሉ። ማንም የምትሰሙት ሰው ብታጡ ሰነፎችን በፍፁም አትስሙ፤ ማንም የምታማክሩት ሰው ብታጣቱ ስለስራና እድገታችሁ በፍፁም ሰነፍ ሰዎችን እንዳታማክሩ። ለእናንተ አዝነው ስሜታችሁን የሚጎዳ ነገር ባይናገሩም ከእነርሱ የሚወጣው የስንፍና መንፈስ አሳስሮ እንደሚያስቀምጣችሁ እወቁ።
አዎ! ጀግናዬ..! ጨለማው መሃል አንዲት ሻማ ብትበራ አይኖችሁ ሁሉ ከጨለማው ይልቅ ሻማዋንና ብረሃኗን መመልከትን ይመርጣል። አንተም እንዲሁ በብዙ ሰነፎችና ቸልተኞች ተከበህ ብቻህን ብርቱና ታታሪ ሰራተኛ ሆነህ ብትገኝ ትኩረት የማትስብበትና ጎልተህ የማትታይበት ምክንያት አይኖርም። ሰርቶ የሚያሰራህ በሞላበት ዓለም ከሰነፎች ጋር ጊዜህን አታባክን። ለብቻ መስራት ከሰነፍ ጋር ከመስራት እጅጉን የላቀ ውጤትን ያስገኛል። ከቻልክ አግዛቸው፣ ከስንፍና በሽታ እንዲላቀቁ ከጎናቸው ሁኑ፣ እንደ አቅምህ ልትረዳቸው ሞክር ከአቅምህ በላይ ከሆኑ ግን አንድም ደቂቃ እነርሱን ለመቀየር አትታገል። ብዙ ጊዜ የሰው ልጅ የሚገባው ስትነግረው ወይም ስትመክረው ሳይሆን አድርገህ ስታሳየው ነውና ከእነርሱ ስንፍና በተቃራኒው ቆመህ ጠንክረህ ሰርተህ ውጤቱን አሳናቸቸው። በአሰናካዮችና በማይደግፉህ ሰዎች ራስህን አጥረህ በውድቀትና በብስጭት የተሞላ ትግል የበዛበት ህይወት አትኑር። የራስህን ነፃና ለሰዎች የሚተርፍ ዓለም ትፈጥር ዘንድ ዙሪያህን ከግዴለሽና ሰነፍ ሰዎች አንፃው። በምትኩም ቁምነገረኛና ታታሪ ሰዎችን ወደ ህይወትህ አስገባ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪