ለውጥን አትፈልጉት!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ለውጥን አትፈልጉት ይልቅ ለውጥን ምረጡ። ስለምን ለመለወጥ ብላችሁ ረጅም ርቀት ትጓዛላችሁ? ስለምን ለውጣችሁን ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ትሆናላችሁ? ስለምን መለወጥ ስለምትፈልጉት ነገር አብዝታችሁ ትጨነቃላችሁ? ለውጥን ፈልጋችሁ ወይም ያለልክ አስባችሁ አታገኙትም፣ ምክንያቱም አጠገባችሁ ነውና፣ ምክንያቱም በየቀኑ እያለፋችሁበትና እየኖራችሁት ነውና። ብዙ ሰዎች ለመለወጥ ብዙ ሲያወጡ ብዙ ሲያወርዱ ይስተዋላል ነገር ግን ከማውጣትና ከማውረድ በላይ እራሳቸው የት እንዳሉና ምን እያደረጉ እንዳሉ መገንዘብ ይኖርበታል። ለውጥ ተራራ ላይ የተቀመጠ ወይም ከርሰምድር ውስጥ የተቀበር ማዕድን ወይም እንቁ አይደለም። ለውጥ ግልፅ ነው። ትናንት ነበረ፣ ዛሬም አለ እንዲሁ ነገም ይኖራል። እርሱን ለማምጣት ከመታገል በላይ ራስን ማየትና የግልን የህይወት አቅጣጫ መረዳት እጅጉን ወሳኝ ነው። እናንተ የምትሰሩትን ስራ ከልብ ከሰራችሁ፣ ሁሌም ትኩረታችሁ ራችሁ ከሆነ፣ ከጊዜ ጊዜ ከቀን ወደ ቀን ከመሻሻል ወደ ለውጥ ከለውጥም ወደ እድገት የማትገቡበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
አዎ! ለውጥን አትፈልጉት፣ እርሱን ለማግኘት ብዙ አትልፉ፣ በስሜታችሁ እንዲጫወት፣ ከሰዎች ጋርም እንዲያነካካችሁ አትፍቀዱ። ለውጥ በየቀኑ በሁላችንም ህይወት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። የእኛ ድርሻ የለውጡን አይነት መምረጥ ነው። በሚያሳድጋችሁ ወይም በሚጥላችሁ የለውጥ መንገድ የመጓዝ መብቱ አላችሁ፣ በአዎንታዊው ወይም በአሉታዊው አቅጣጫ የመሔድ ምርጫ አላችሁ። ማንም ሰው እንደ አቅሙ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ጠንቅቆ ያውቃል። "ውሃ ውሃ ነው ያሰምጥሃል፣ እሳትም እሳት ነው ያቃጥልሃል" መባል ያለበት ሰው የለም። ማንም ሰው የራሱ የእውቀትና የመረዳት ደረጃ አለው። ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትሰራናለች፣ ህይወት በብዙ ዘርፍ ታንፀናለች። አንዴ በደስታ አንዴ በሃዘን፣ አንዴ በፍቅር አንዴ በጥላቻ፣ አንዴ በማቅረብ አንዴ በማራቅ ትገለፅልናለች። ለምን ብላችሁ መድከም እንዳለባችሁ አስቀድማችሁ እወቁ፤ መውጣት መውረዳችሁ፣ መሰደብ መተቸታችሁ፣ መገፋት መጠላታችሁ ለምን እንደሆነ አስቀድማችሁ ተረዱት። ይሔ የምትከፍሉት ዋጋ በእርግጥም ለሚመጣው ውጤት የሚገባው ነው? ጥያቄውን በጥንቃቄ መልሱ።
አዎ! ጀግናዬ..! በየቀኑ ህይወትህ እየተቀየረ ነው። ነገር ግን ወዴት እየተቀየረ እንደሆነ መረዳቱ ከሌለህ እየጠፋህ እንዳሆነ አስተውል። አንድ ቀን ስትነቃ አስበህ እንኳን የማታውቀው የማትፈልገው ቦታ ራስህን እንዳታገኘው ዛሬውኑ እያንዳንዱን እርምጃህን በጥልቀት መርምር። ማንንም ለመግዛት ከማኮብኮብህ በፊት ስለራስህ መነሻና መዳረሻ እውቀቱ ይኑርህ። ህይወትህን በምታሻሽልበት በእያንዳንዱ ቅፅበት የምታስተውለውን ነገር አስቀድመህ የምታጣጥመው አንተ ነህ። በሰዎች ላይ የምትመለከተውን ለውጥ መመኘት አቁም፣ በምትኩ ባንተ ህይወት እየተከናወነ ስላለው ለውጥ ግንዛቤው ይኑርህ። አንተ በንቃት የምትረዳውም የማትረዳውም ብዙ ነገር በህይወትህ ውስጥ እየተከናወነ ነው። አይንህን ክፈት፤ አሁን በዋናነት በህይወትህ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ክስተት ትወደዋለህ? ትፈልገዋለህ? ያንን የምትመኘውን ለውጥ ለማምጣት የሚጠቅምህ ይመስልሃል? ጊዜ አታጥፋ፣ የምትፈልገውን ለውጥ አሁኑ ምረጥ፣ በእርሱ ላይም ለመስራት በልበሙሉነት ተነስ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪