⏰ ነገ ጁምዐ ነው‼️
ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዐ ተጠበባብቀን በረሱል ላይ ሰለዋት የምናወርደው❓❓
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ ምንዘናጋው❓❓
📚እስኪ አላህና መልዕክተኛው ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇
🌴💥🕋🌴💥🕋
قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ;እናንተ ያመናቹ ሆይ በሱ(በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}
📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇
"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዐ ቀንና ጁምዐ ለሊት በኔ ላይ ሰለዋት አብዙ።በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}
"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}
" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው;አላህ በሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}
" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}
🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"
@muslims_couples