ነገረ ፈጅ Negere Fej


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ነገረ ፈጅ Negere Fej
contact us @NegereFeji_Bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


አቤቱቱታ ስለ ማሻሻል - የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርአት ህግ ቁጥር 91

አቤቱታ ማለት ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ/መልስ/ይግባኝ/ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት አንድ ባለ ጉዳይ ከፍ/ቤት የሆነ ዳኝነት እንዲወሰንለት በመጠየቅ የሚያቀርበው ማመልከቻ ነው፡፡

አቤቱታ ላይ ያቀረበው ሰው የሚጠየቅው ዳኝነት እና ይህንን ዳኝነት ሊያገኝ የሚገባውን ጉዳይ አብራርቶ መጠየቅ ያለበት ሲሆን ክስ ከቀረበ በኋላ ወይም ጉዳዩ ከጀመረ በኋላ በአቤቱታው ላይ መገለጽ የነበረበት እና አለመገለጹ ባለ ጉዳዩን የሚጎዳ፤ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳይሰጥ ሊያደርግ የሚችል እና ለፍትህ አሰጣጥ የሚስቸግር ከሆነ ባለ ጉዳዩ ይህንን አቤቱታ አሻሽሎ ወይም የተጓደለውን አሟልቶ እንዲያቀርብ እንዲፈቀድለት ለፍ/ቤት ሊያመለከት ይቻላል፡፡

አቤቱታ ሲሻሻል ነገሩን በይበልጥ ወይም በተሻለ መንገድ ማብራራት እንጂ በመጀመሪያው ዳኝነት ላይ ያልተጠየቀ እና ፈጽሞ የተለየ ጉዳይ ወይም ዳኝነት ይፈጸምልኝ የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ልጅነት ስለማረጋገጥ

በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 154 መሠረት በአባት ወይም በእናትነት በኩል ያለ የአንድ ሰው ልጅነት የእከሌ ልጅ ነው/ናት የሚል የልደቴ ሰርተፍኬት በማቅረብ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን የልደት ሰርተፊኬት ከሌለ የልጅነት ሁኔታ መኖሩን በማስረዳት ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ (አንቀጽ 155) የልጅነት ሁኔታ ማለት አንድ ሰው በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ የእርሱ ወይም የእርሷ ልጅ ነው እየተባለ የሚገመት እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ልጅነት ማረጋገጥ የፈለገ ሰው በዚህ መሠረት የሚያስረዱለትን/የሚመሰክሩለትን የሰው ምስክሮች በማቅረብ ልጅነቱን ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡
ልጅነት ማረጋገጥ አስፈላጊ የሚሆነው አንድ ሰው በአሳዳጊ ወይም በሌላ ሰው ስም ሲጠራ ቆይቶ የአባቱን ስም ወደ ትክክለኛ የወላጅ አባቱ ለመቀየር የፈለገ እንደሆነ፤ ከአባት/እናት በኩል የሚገኝ ውርስ ለማግኘት ወራሽነት ለማረጋገጥ/ ለማግኘት ልጅነት ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፤ የልደት ሰርተፊኬት ለማውጣት እና ውልደቱ በወቅቱ በወሳኝ ኩነቶች ወይም ሌላ ስልጣን ባለው የክብር መዝገብ ሹም ፊት ሳይመዘገብ ቀርቶ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያቀርብ የተጠየቀ እንደሆነ ሊሆን ይችላል፡፡
ልጅነት ለማረገጥ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ አቤቱታ ከዚህ በታችን በተገለጸው ፎርም የሚቀርብ ሲሆን አባት/እናት በህይወት ካሉ ተጠሪ ሊደረጉ የሚገባ ሲሆን በህይወት ከሌሉ ግን ይህንን በመግለጽ ተጠሪ የለም ብሎ በመጻፍ ሊቀርብ ይችላል፡፡ የሚቀርብበትን ፍ/ቤት አድራሻ በተመለከተ አባት ወይም እና ካሉ እና ተጠሪ ከተደረጉ እነርሱ በሚኖሩበት ክ/ከተማ ባለው የፌደራል ፍ/ቤት ሲሆን አባት እና/ወይም ከሌሉና ተጠሪ ማንም ካልተደረገ አመልካቹ በሚኖርበት ክ/ከተማ ነው፡፡
ነገረ ፈጅ Negere Fej
contact us @NegereFeji_Bot
https://t.me/NegereFej

1 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

165

obunachilar
Kanal statistikasi