◆የወልቂጤዉ አንጋፋዉ ተስፋ ቤተ መጽሐፍት◆
ለወልቂጤ ህዝብና በዙሪያዋ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች
ለበርካታ አመታት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
መጽሀፍት ቤቱ ህዳር 1989 አመተ ምህረት በወጣት ደራሲ
እንዳለጌታ ከበደ አማካኝነት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
መፃሕፍት ዝም ብለው ጠንካራ ልባድ እና የውስጥ ገፆች ብቻ ያላቸው አይደሉም።
ውስጣቸው ሰው አለ ፤ ሕዝብ አለ ፤ ታሪክ አለ ፤ የሰው ልጅ ውጣ ውረድ አለ ፤ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ተመራማሪዎች ፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ ፣ያኛው ብዙ አሜኬላና እንቅፋት አለው እያሉ የዚህችን ዓለም ምስጢራት ይገላልፁልናል በትንሽ ኪዬስ በምትመስል ሱቅ ለከተማዉ ህዝብና በዙሪያዋ ለሚገኙ ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ ቤተ መጽሀፍቱ ሲጀምር 84 በሚጠጉ መጽሀፍት ስራ በመጀመርና በቀን በአንድ መጽሀፍት 25 ሳንቲም በማከራየት ስራ ጀመረ።
መጽሐፍት ለሰው ልጅ በተሰጠው መንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰውየመሆናችንን ፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን ናቸው በወልቂጤ ከተማ ምንም አይነት ቤተ መጽሀፍት ወይም መጽሀፍ
መሸጫ መደብር ባልነበረበት ወቅት ይህ ቤተ መጽሀፍት የብዙዎች ባለዉለታ ነች።
ከዶክተር እስከ ኢንጅነር ?፣ ከደራሲ እስከ ሀያሲ ከተዋናይ እስከ ሰአሊ ያፈራ አንጋፋ ቤተ መጽሀፍት ነዉ።
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ስለ ቤተ መጽሀፍቱ ጠይቄዉ እንዲህ
ብሎኛል ቤተ መጽሀፍቱ በ1989 አመተ ምህረት 84 የተለያዩ
መጽሀፍት በትንሽዬ ኪዬስ ዉስጥ በማስገባት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ይህ ቤተ መጽሀፍት ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት በተከፈተበት ቀን አንድ መጽሀፍ ብቻ ቀን ሙሉ የተከራየ መሆኑንና ከተከራዩም ጋር ለትዝታ የሚሆናቸዉን ፎቶ ግራፍ እንደተነሱም ነግሮኛል።
በልቂጤ ከተማ ምንም አይነት ላይብረሪና መጽሀፍት መደብር ባልነበረበት ወቅት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ መጽሐፍት ቤቱ በቀን ወይም ለ24 ሰአት አንድ መጽሀፍ 25 ሳንቲም ሲከራይ እንደነበረና መጽሀፍ የመከራየት አቅም የሌላቸዉ ተማሪዎች ይሁን አንባቢዎች በነጻ እንዲያነቡ ይመቻችላቸዉ ነበር።
በዛን ወቅት በጠባቧ ቤተ መጻሐፍት ዉስጥ ሙሁራኖች ተሰባስበዉ በየጊዜዉ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዎች ላይ ዉይይት ይደረግበት እንደነበረና ብዙዎች ቁጭ ብለዉ ያነቡባት ነበር።
ተስፋ ቤተ መጽሐፍት ከራዘስላሴ እስከ የቀድሞዉ ጎሮ ወይም የአሁኑ አበሩስ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪዎችን የማበረታታት እና በደረጃ ለወጡ ተማሪዎች የመጽሐፍ ሸልማት ያበረክት እንደነበረ ይታወቃል።
የብዙዎች ባለዉለታ የሆነዉን ቤተ መጽሐፍት ፣ ለደራሲ መንግስቱ በስር ፣ ለደራሲ ፋሪስ አስፋ ፣ለደራሲ ሀይከል ሙባረክ ፣ለደራሲ ንጋቱ ወልዴ እንዲሁም ለራሱ ለደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እና ለበርካታ ደራሲዎች እዚህ ደረጃ የመድረስ መነሻም ነዉ።
በቤተ መጽሐፍቱ ስም በየጊዜዉ ወልቂጤ ከተማ በጎሮ በአሁኑ ያበሩስ ትምህርት ቤት ላይ የስነ ጹሁፍ እና ድራማ ዉድድር በማዘጋጀት በአማተርና ታዋቂ በሆኑ የጥበብ ሰዎች ጥሩ ጥሩ ስራዎች ይቀርቡ እንደነበረም የቤተ መጽሐፍቱ መስራች እንዳለጌታ አስታዉሷል።
በከተማዉ በትምህርታቸዉ ከፍተኛ ዉጤት አምጥተዉ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት ዉጤት ለመጣላቸዉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላቹሁ ፕሮግራም ይዘጋጅ እንደነበረም አዉስቷል።
ተስፋ ቤተ መጽሐፍት ከቀድሞ ጎሮ ወይም የአሁኑ አበሩስ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እስከ እራዘስላሴ እና ሰላምበር ተማሪዎች ድረስ በዚህ ቤተ መጽሀፍት ለትምህርታቸዉ አጋዦ የሚሆናቸዉ መጽሐፍ ተዉሰዉ የሚያነቡት ተማሪዎች ቁጥራቸዉ
ቀላል የሚባል አልነበረም።
ተማሪዎች የክረምትን ወቅት ተጠቅመዉ የተለያዩ ልበወለድ
መጽሐፍቶች በመከራየት የእረፍት ጊዜያቸዉን በንባብ ያሳልፋሉ።
ብዙዎችም በደረጃ እንዲወጡ ቤተ መጽሐፍቱም የማይተካ ሚና እየተወጣ እንደሆነም ይታወቃል።
ዛሬ ላይ መጽሐፍት ቤቱ በጥሩ ሁኔታ ተደራጅቶ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ መጽሐፍት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
በታዋቂዉ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ የተጀመረዉ አንጋፋዉ ቤተ መጽሐፍት ለተማሪዎች ፣ለመንግስት ሰራተኞች እና ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች አሁንም ድረስ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የዚህን ቤተ መጽሐፍት ተገልጋይ የነበሩ አብዛኛዎች ትልልቅ ቦታ በመድረስ እና እራሳቸዉ ችለዉ በትላልቅ የስራ ሀላፊነት ተሰማርተዉ እየሰሩ እንደሆነም ይታወቃል።
መፃሐፍት ውስጥ ዋዛ እና ለዛ አለ። በዋዛና በለዛ ቋንቋ ተቀነባብሮ የሕይወትን አቅጣጫ እንድንፈትሽ ፣ እንድናውቅ ፣ እንድንመራመር ፣ እንድንጠይቅ፣ እንድንመልስ ፣ እንድናብራራ ያደርጉናል።
መፃሕፍት ሲከፋን የሚያፅናኑን፣ ስንሳሳት የሚያርሙን፣ ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን ከውስጣችን አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና የሚገነቡልን የሊቃውንቶች ስጦታ ናቸው።
ይህ አንጋፋ ቤተ መጽሐፍት የብዙዎች ባለዉለታ ነዉ።
ብዙዎችን በጥሩ ስነ ምግባር እንዲቀረጹ ፣ ብዙዎች የእዉቀት ባለቤት እንዲሆኑ መሰረት የጣለ እንዲሁም ለከተማዉ ህዝብ ለዉጥ ትልቅ አሻራ እያስቀመጠ ይገኛል።
◆ኑሬ ረጋሳ◈