💞ፍቅር እና እምነት💞
#ክፍል_10
ብሌንና ቶማስ የሰርጋቸው ቀን ደርሳ ሲመኙት የነበርው የአብሮ
ማደርና አብሮ መዋል እውን ሊሆን ነው,ሰርጉ በሚፍልጉት
መልኩና ደስ በሚል ሆኔታ ተጠናቀቀ ..
ፍፁም ደስታ ፍፁም ስላም ደስ የሚል የፍቅር ህይወትን ሰንቀው
አብሮ መኖርን ሊጀምሩ ነው የቤተስብ የወዳጅ ዘመድና የጓደኛ
ምርቃ አንበሽበሻቸው ውለዱ ክበዱ አይለያችሁ እንኳን ደስ
ያላችሁ መልክ ከየቦታው ይስማል ..ሰርጋቸውን ጨርስው
ለመጀመርያ ግዜ አንድ ቤት አደሩ
ብሌን ከቶማስ በፊት ፍቅርኛ ቢኖራትም ነገር ግን ከጋብቻ በፊት
ምንም ነገር ማድርግ እንደማትፍልግ ስትነግርው ነበር አንቺ ለኔ
ፍቅር የለሽም ቢኖርሽ ኖሮ ከኔጋር ምንም ነገር ማድርግን
ባልፈራሽ ነበር ብሎ ነበር የተለያት ብሌን ለቶማስ ከወንድ ጋር
ግንኙነት አድርጋ እንደማታውቅ ብትነግርውን እውነት ይሆናል
ብሎ ግን አስቦ አያውቅም እኔ የማፍቅርው አንቺን ነው ስለዚህ
ሌላ ነገር ትርፍ ነው ይላት ነበር,
ቶማስ እውነትና ውሽት መሆኑን የሚያርጋግጥበት ስአቱ ደረሰ
እውነት ባይሆን እንኳን በእርሱ ዘንድ ምንም ነገር እንደማይፍጠር
ግን ደጋግሞ ለራሱ ነግሮ አሳምኖታል ,,
ብሌን ምንም እንኳን የሴት ጓደኛ ባይኖራትም ካሏት የወንድ
ጓደኞች ጋር ግልፅ ስለሚያወሩ ሁሉንም ነገር ታውቃለች
እህቷም ነግራታለች ብትፍራም ግድ ነው ,,
ቶማስ ብሌን የነገርችው ነገር እውነት እንደሆነ ሲያርጋግጥ
በጣም በመገረም የእውነት ልዬ ሴት ነሽ እድሜ ዘላለሜን
አፍቅርሻለው አላት ብሌን የህመምም የፍቅር እንባ አነባች ስቃይ
በተናነቀው ድምፅ ሀኒዬ ዘላለሜን እስከ ህይወቴ እስትንፍስ
አፍቅርሀለው ያንተ ብቻ ነኝ ብላ ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች,.
የብሌንና የቶማስ ህይወት ከዛን ቀን አብሮናታቸው ቀጠለ ደስ
የሚል የፍቅር ግዜ ቶማስ ስራ አስፍቅዶ ለሽርሽር ቢሾፍቱ ከዛ
መልስ አዳማ እያለ በደንብ አዝናናት ብሌን በጣም ደስተኛ ነች
.የብሌን ፈገግታ የብሌን ሳቅ ቶማስን ያጠግበዋል ያስደስተዋል
ሌላ ስው በደንብ ሲያያት ከተመለከተ መነፅር ካደርገ መነፅሩን
አውልቆ ካልሆነም ጃኬቱን አውልቆ ያለብሳታል ብሌን
ትስቅበታለች አልበርደኝም እኮ ሀኒ ትለዋለች ,እናቴ የሰው አይን
ጥረ አይደለም ልበሽው ይላል ,ያፍቅራታል ያከብራታል
በመሀከላቸው የሚያስቀና... ደስ የሚል ፍቅር አለ ደስ የሚል
ስላም አለ ,.
ብሌን የውዝዋዜ ስራዋን ትወደዋለች በተለይ ትወና ውስጥ
ለመግባት ያላት ጉጉት ለየት ያለ ነው .ብሌን ጠዋት ወጥታ
ልምምድ አድርጋ ተመልሳ እቤት ትመጣለች አንዳንዴም ወደ
ቤተስቦቿ ቤት ትሄዳለች ,ሰሞኑን ግን ለየት ያለ ነገር
ተፍጥሮባታል ውዝዋዜ ስትስራ ይደክማታል ትንሽ ስትጓዝ
ይደክማታል በቃ ምን ቅጡ ግራ ገብቷታል .
ቶማስ አንድ ሀሳብ አሰበ ብሌን አንዳንዴ ስራ ሲኖር ወደ
ክፍለሀገር ለቀርፃ እንዳንዴ ደግሞ ናይት ክለብ ስራ ሲኖራት
አምሽታ ትመጣለች ያ ነገር ቶማስን ሰላም ነስቶታል
ስለሚያፍቅራት እንዳንዴ የምትስራበት ናይት ክለብ ሄዶ ለሷ
ሲሽልሟት አብረዋት ሲጨፍሩ እንደ ቅናት አድርጎታል በቃ ይሄንን
ስራ መተው አለባት ከፈለገች ሌላ የፍለገችውን ትስራ ብሎ
ለራሱ አስበ,
ብሌን የናይት ክለብ ስራ ስለነበራት እዛ አምሽታ ወደ ቤት
ስትመጣ ቶማስን ሶፍ ላይ ተኝቶ አገኝችው የኔ ፍቅር ሀኒ
አለችው ,ወዬ እናቴ መጣሽ ብሎ ተነሳ ልብሷን ቀይራ ወደ እሱ
መጣች ቶማስ ሊናገርው የሚፍልገው ነገር እንዳለ
ያስታውቅበታል እንዳይነግራት ውዝዋዜ እንዴት እንደምትወድ
ያውቃል ዝም እንዳይል አብርዋት የሚጨፍሩት የሚሽልሟት
የሚወስዱበት መስሎ ተሰማው,
የቶማስ ዝምታ ግራ ያጋባት ብሌን ምን ሆንክብኝ ሀኒ አለችውአጠገብ ቁጭ ብላ ,ምንም
እናቴ ግን የሆነ ነገር ልነግርሽ ብዬ
ነበር አለ ፍቱን ወደሷ በማዞር ,ግራ ገባት ምንድነው ሀኒ ንገራኛ
ንገረኝ ,አለችው ,ምን መስለሽ እናቴ ያው እንደሚታወቀው
ውዝዋዜ በጣም ትወጇለሽ ግን በቃ እሱ ተይውና ሌላ
የፈለግሽውን ስራ ስሪ አብርን እናምሽ አንቺ ናይት ክለብ ለስራ
ባመሽሽ ቁጥር እኔ ብቻዬን እየከፍኝ ነው አላት ,
ብሌን ደነገጠች ያልጠበቀችው ነገር ውዝዋዜን ማቆም
ባጠቃላይ ከጥበብ መራቅ ሆኖ ታያት ሀኒ እንዴት አስበኽው ነው
ምን ያክል ...ብላ ሳትጨርስ አቋርጣት አውቃለው አለ ቶማስ
ስለማፍቅርሽ ነው ከስራ ስአት ውጪ ግዜየን በሙሉ ካንች ጋር
ማሳለፍ እፈልጋለው ስወድሽ እሽnnnnn በይኝ አላት. በሚያሳዝን
አስተያየት እያያት ብሌንም ...........
ክፍል ➊➊ ይቀጥላል......
@offical_McMccall