🔒
የኢሜይልዎ ደህንነት አስተማማኝ ነው?በአሁኑ ጊዜ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች እና የማጭበርበር ድርጊቶች የሚፈጸሙት በኢሜይል (Email) አማካኝነት ነው። የኢሜይል አካውንትዎ ከተጠለፈ የግል መረጃዎችዎ፣ የሶሻል ሚዲያ አፕሊኬሽኖችዎ እና የባንክ መረጃዎችዎ አደጋ ላይ ይወድቃሉ።
ኢሜይልዎን ከአጥቂዎች ለመጠበቅ እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች ይተግብሩ፡
ጠንካራ የፓስወርድ አጠቃቀም (Strong Password):ፊደላትን፣ ቁጥሮችን እና ልዩ ምልክቶችን (@, #, $) ያቀላቀለ ፓስወርድ ይጠቀሙ።
ለሁሉም አካውንትዎ አንድ አይነት ፓስወርድ አይጠቀሙ።
ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን ማብራት (2-Step Verification):ይህ መንገድ ፓስወርድዎ እንኳ ቢሰረቅ ሌላ ሰው እንዳይገባ ይከለክላል። በስልክዎ ላይ ኮድ እንዲላክላችሁ በማድረግ ያበሩት።
አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመንካት (Beware of Phishing):የማያውቁት አካል የላከላችሁን ሊንክ ወይም ፋይል (Attachment) ከቶ አትክፈቱ።
ባንኮች ወይም ድርጅቶች በኢሜይል ፓስወርድዎን ወይም ሚስጥራዊ ቁጥርዎን በጭራሽ አይጠይቁም።
የማrecovery መረጃዎችን ማደስ:የመጠባበቂያ ስልክ ቁጥር (Recovery Phone) እና ተጨማሪ ኢሜይል ማካተትዎን ያረጋግጡ።
መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከሳይበር ጥቃት ይታደጓቸው!
በቴክኖሎጂ፣ በሳይበር ደህንነት እና በዲጂታል እውቀቶች ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉
@PARO_MEDIA