የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከውጭ ወደ አገር ቤት ለሚመጡ እና ከፍለው ሆቴል መቆየት ለማይችሉ ወገኖቻችን ማረፊያ የሚሆን 2000 አልጋዎችን አዘጋጅቷል።
የኮሮና ቨይረስን ስርጭት ለማከላከል ሲባል ከውጭ ወደ አገር ቤት የሚገባ ሁሉ ለ14 ቀን ራሱን ለይቶ መቆየት እንደለበት በቅርቡ መንግስት መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህም በመነሳት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከውጭ ወደ አገር ቤት ለሚመጡ እና ከፍለው ሆቴል መቆየት ለማይችሉ ወገኖቻችን ማረፊያ የሚሆን 2000 አልጋዎችን አዘጋጅቷል።
የዩኒቨርስቲውን ዝግጅት በአካል ተገኝተው የጎበኙት የሰይንስና ከፋተኛ ት/ም ሚንስትር ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም እና የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም የጤና ሚንስተር ከፍተኛ ኃላፊዎች፤ ተቋሙ በራሱ ወጭ እያበረከተ ላለው አገራዊ አስተዋጽኦ አመስግነዋል። ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ከተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በሚመለሱበት ወቅት እንዳይጉላሉ ዩኒቨርስቲው መሸጋገሪያ/ማረፊያ በመሆን የሰጠውን ትልቅ ግልጋሎት ያወሱት ፕ/ር ሂሩት ሌሎችም መሰል ተቋማት የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ አርአያነት በመከተል ለአገራዊ ጥሪ መዘጋጀት እንዳለባቸው በመጠቆም፣ ለተደረገው ሁሉ የዩኒቨርሲቲውን ማኔጀመንት እና ሠራተኞች አመስግነዋል።
የዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቻው ይህንን ፈታኝ ወቅት ለማለፊ ሁሉም ዜጋ ከመንግስት ጎን በመቆም እንዲሁም በለው አቅም ሁሉ መረባረብ እንዳለበት እንደለበት በመጠቆም፤ ከፍለው በሆቴል መቆየት ለማይችሉ ወገኖቻችን ዩኒቨርሲቲው በራሱ ወጭ የመኝታ እና የምግብ እንዲሁም ሌሎች ለመቆየት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን አሟልቶ ለአንድ ሰው አንድ ክፍል ማዘጋጀቱን አስተውቀዋል፡፡
ከጤና ሚንስተር ኃለፊዎች ለመረዳት እንደቻልነው