. 💗▬▬ஜ۩ገምሃልያ۩ஜ▬▬💗
💘አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ💘
▬====🧣ተከታታይ ታሪክ🧣====▬
#ክፍል6
...🖊በዛ ድቅድቅ ጨለማ ምንም የሰው ዘር በሌለበት አንድ ላዳ መጥቶ አጠገቤ ቆመ ኮትራት? አለኝ አው ብዬው ወዴት እንደምሄድና ዋጋ እንኳን ሳንነጋገር ሰተት ብዬ ገባው ብርዱ እና ጨለማው እያንዘፈዘፉኝ ነበር በተለይ ፅልመቱ ምንም ሰው ስላልነበረበት ነው መሰል በጣም ያስፈራል። ሹፌሩ አንገቱን ወደኃላ ጠምዝዞ እያየኝ ወዴት እንሂድ የኔ እናት አለኝ ነጠላዬን እያጣፋው ስቴዲየም እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ውሰደኝ አልኩት። ሹፌሩ ምንም መልስ ሳይሰጥ በፍጥነት ወደ ስቴዲየም መገስገስ ተያያዘው ቶሎ እንደምደርስ ሳስብ ደስ አለኝ።
ስልኬን በነጠላው ውስጥ እንዳለ ቀና አድርጌ አየሁት 11፡50 ይላል በመጠኑም ቢሆን እየነጋጋ ነው ሰማዩ ደመና ቋጥሮ የአህያ ሄድ መስሏል አዲስ አበባ በዚ ሰአት ያላእ እርጋታ አስገረመኝ፤ ቀን ከለሊት ሁሉም እሚሮጥባት ናት በዚ ሰአት ግን በጎዳናዎቿ ላይ ነጠላ የለበሱ ሰዎች እና ለሊቱን ሙሉ ሲጠጡ ያነገ ሰካራሞች ብቻ አልፎ አልፎ ይታዩባታል። ከሰመመኔ ስነቃ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ደርሰናል አከባቢው እንዳለ ነጫጭ ብርሃናማ ነጠላ በለበሱ ሰዎች ተሞልቷል። በፍጥነት ሹፌሩ የጠየቀኝን ብር ሰጥቼው ወረድኩ የእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንን ደረጃ ወጥቼ ተሳለምኩና ወደ ውስጥ ገባው የቅዳሴ ድምፅ ከውስጥ እንደ ነጎድጓ ያስተጋባል የሰዉ ብዛት አስፈራኝ ከዚ ሁሉ ሰው ታዲን ላገኘው እንደማልችል ገባኝ በቀኝ እና በግራ ወንዶች እና ሴቶች ለብቻቸው ተለይተው ቆመው እያስቀደሱ ነበር ታዲን ባገኘው እንኳን ወደሱ መሄድ እንደማልችል ገባኝ ግዴታ እስኪያልቅ መጠበቅ ነበረብኝ። ቤተክርስቲያን አልፎ አልፎ ለበአላት ከመሄድ ውጪ ብዙም የመሄድ ልማድ የለኝም ሴቶቹ ባሉበት አቅጣጫ አንድ ዛፍ ስር ቆሜ ሰዉ ሲያስቀድስ እኔ በአይኔ ታዲን መፈለግ ጀመርኩ። ግን ላገኘው አልቻልኩም በጣም ብዙ ሰው ነበር ቢቸግረኝ እኔም እንደሰዉ ለማስቀደስ ጆሮዬን ወደ መቅደሱ ጣልኩ እኔም ታዲን ለማግኘት እስኪያልቅ መጠበቅ ነበረብኝ ቅዳሴው በጣም ረዘመብኝ ለብዙ ሰአታት የቆምኩ መሰለኝ ተሰላቸው ስልኬን ወጣ አድርጌ እየው 01፡30 ይላል ወይኔ... ገና ነው ብዙ ሰአት የቆምኩ የመሰለኝ ገና 40 ደቂቃ ቆሜ ነው። ሲደክመኝ ባለሁበት ዛፉን ተደግፌ ቀጢጥ አልኩ ጉልበቴ ታቅፌ እንደተቀመጥኩ በዛው እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ በኔ ሰአት አቆጣጠር ገና የእንቅልፍ ግዜ ነበር። የሆነ ሰአት ላይ አንድ ደንደን ያለ እጅ ሲነካኝ ደንግጬ ብድግ አልኩ ተደነባበርኩ በእንቅልፍ ልቤ ቤተክርስቲያን የመጣው እስኪመስለኝ ድረስ ደነገጥኩ ነግቷል ቅዳሴው አልቆ ሰዉ እየወጣ ነው ቀና ብዬ የቀሰቀሱኝን እጆች አየኃቸው ታድኤል እጄች ነበሩ። አይዞሽ ፅናት እኔ ነኝ ታድኤል! ቅድም ስትገቢ አይቼሽ ነበር ከዋናው በር ኃላ ነበርኩ አለኝ ውስጤ በሃሴት ተሞላ እየሳቅኩ ሰላም አደርክ ታዲ አልኩት ደና ነኝ እግዚአብሄር ይመስገን ብሎ መለሰልኝ። አተኩሬ አየሁት በነጠላ ደግሞ ይበልጥ ያምራል የለበሰው ነጠላ ከፀሃይዋ ነፀብራቅ ጋር ተዳምሮ ከሰማይ ቤት የመጣ መልአክ አስመስሎታል። ሰአቱ እየሄደ ስለነበር ቅዳሴ የመጣው ምእመን ቀስ በቀስ ከግቢው እየወጣ ወደየቤቱ መሄደ ጀመረ ፀጥታ ሰፈነ እኔና ታዲ ከኃላ ካሉት የድንጋይ ወንበሮች ላይ ተቀመጥን ትንሽ ዝም ተባብለናል ሰዉ ቀለል እስኪል ድረስ።
ፅናት የምትነግረኝን ታሪክ በጣም ተመስጬ እየሰማኃት ካለሁበት ቦታ እና ግዜ ተላቅቄ ፅናት በምትነግረኝ ታሪክ ውስጥ ራሴን አስገብቼ በአእምሮዬ ውስጥ እየሳልኩት ነበር ድንገት ይህንን ተመስጦ የሚያቋርጥ ሰው መጣ ከተቀመጥንበት ፓርክ ጥበቃዎች አንዱ ዘበኛ ነበር ከኛ ትንሽ ፈንጠር ብሎ እንደቆመ ትኬት ይዛቹሃል!? አለ ጮክ ብሎ። ፅናት ታሪኳን ቶሎ እንድትነግረኝ ስለፈለኩ በፍጥነት ቅድም የቆረጥኩትን ባለሮዝ ቀለም ትኬት ፍለጋ ኩሴን መበርበር ጀመርኩ። ሳገኘው ደስ አለኝና ወደ ጥበቃው እየዞርኩ አው ይዘናል አልኩና ደማቅ ሮዟን ትኬት አሳየሁት እሺ ብሎን በዛፎቹ መሃል እያቆራረጠ ሄደ አልፎ አልፎ እየመጡ የመጠየቅ አባዜ አለባቸው እሱን ትንሽ ካየሁት በኃላ ወደ ፅናት ዞርኩና እሺ... ቤተክርስቲያን ተገናኛችው ከዛስ አልኳት...
#ይቀጥላል...
❥..................🍃⚘🍃...................❥
🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇
@princabeni @princabeni