በአንድ ወቅት አንድ ሰዉ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፤ ተጓዘ፡፡
ይህ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በመንገድ ላይ እየተጓዝ ሳለ በድንገት ወንበዴዎችና ሽፍቶች አገኝተውት መጥተዉ አስቆሙት::ገንዘቡን ወሰዱ፤ ልብሱንም ገፈፉበት:: ደብድበዉም፤ አቁስለው ሊሞት ሲቃረብ በመንገድ ላይ ጥለውት ሔዱ:
አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲሔድ ያን ተደብድቦ የወደቀውን ሰው ቀርቦም ቢያየው ተጎድቷል፤ ነገር ግን ሳይረዳዉ አልፎ ጥሎት ሔደ፡፡
ከካህኑ ቀጥሎ ደግሞ አንድ ከሌዊ ወገን የሆነ ሰው በዚያ መንገድ ሲያልፍ በወንበዴዎች ተደብድቦ የወደቀዉን ሰዉ አገኘው እና አየዉ:: ነገር ግን እርሱም ሳይረዳዉ ዝም ብሎ በመንገድ ላይ እንዳየው እንደቀደመው ካህኑ ሌዋዊውም ገለል ብሎ አልፎት ሔደ::
አንድ ሳምራዊ ግን በዚያች መንገድ ሲሄድ አገኘው፤ አይቶም አዘነለት፤ ወደ ቆሰለው ቀርቦ በቁስሉ ላይ እንዲያደርቅለት ወይን አደረገለት፤እንዲያለሰልስለት ደግሞ ዘይት በቁስሉ ላይ አፈሰሰለት፡፡
ደጉ ሳምራዊው የተደበደበውን ተጓዠ ሰው ቅርብ ወዳለው እንግዳ ማረፊያ ስፍራም ከአስገባው በኋላ እየተንከባከበዉ፤እያስታመመው የሚፈልገውን እያደረገለት አብሮት በሰላም አደሩ።
በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዶች ማረፊያ ማደሪያ ወይም ማደሪያ ቤት ባለቤት ኃላፊ ለሆነው ሰው ሰጠዉ፡፡ ከሰጠዉም በኋላ «የምትከስረዉን ሁለ እኔ ስመለስ እከፍልኀለው» ብሎ የተደበደበውን ሰው አደራ ሰጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሔደ፡፡
ሉቃ ፲÷፴፫
https://t.me/raiye_mariyam