#ላንዲት_የገጠር_ሴት
ስትፈጭ የኖረች ሴት
መጁ በመጠኗ ፣ ወፍጮውም በልኳ
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲኾን ያበቃል ታሪኳ።
አስባው አታውቅም
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደ መጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን ከ ናቷ ሆድ ወጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች
ከ'ለታት ሌላ ቀን ለባሏ ተሰጠች
ተዚያን ቀን ጀምራ
ተዚያን ቀን ጀምሮ
ድንግል ድንጋይ ወቅራ
ትፈጫለች ሽሮ።
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አታውቅም፣
ሹማምንት፣ በ'ሷ ስም፣ምን እንደሚሰሩ
አነሣኹት እንጂ እኔም ለነገሩ
በፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ
ምን ይጠቅማትና፣ጓያዋን ለማድቀቅ።
ከቶ ማንም የለ፣አበባ የሚሰጣት
ከቶ ማንም የለ፣ከተማ የሚያወጣት
ከቶ ማንም የለ፣በዳንኪራ መላ፣ወጠቧን የሚያቅፋት
ልፋቷም፣ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት።
እንደ ዓባይ ፏፏቴ ሺሕ ዓመትቢንጣለል
ቢጎርፍም ዱቄቱ
እንደ ሲኦል ወለል
ጫፍ የለውም ቋቱ ።
ከዘመናት ባ'ንዱ
መስታወት ፊት ቆማ፣በተወለወለው
ፊቷን ለማየት
ከፀጉሯ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት
ያኔ ይገባታል የተሰጣት እጣ
ከማድቀቅ ቀጥሎ መድቀቅ እንደ መጣ።
የመጅ አገፋፏ አምሳለ ሲሲፈስ
ከቋት ስስት እንጂ ሲሳይ አይታፈስ
ትቢያ ሚተነብይ ዱቄት በዙርያዋ
ከባርኔጣ አይሰፋም የኑሮ ጣርያዋ
"ስትፈጭ የኖረች ሴት " ይህ ነው መጠሪያዋ።
#ሲሲፈስ- በግሪክ ተረት ውስጥ የሚገኝ ተኮናኝ ሲኾን ኩነኔው ያለግብ ድንደፈጋይ መግፋት ነው።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
@sayatmekdi
ስትፈጭ የኖረች ሴት
መጁ በመጠኗ ፣ ወፍጮውም በልኳ
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲኾን ያበቃል ታሪኳ።
አስባው አታውቅም
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደ መጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን ከ ናቷ ሆድ ወጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች
ከ'ለታት ሌላ ቀን ለባሏ ተሰጠች
ተዚያን ቀን ጀምራ
ተዚያን ቀን ጀምሮ
ድንግል ድንጋይ ወቅራ
ትፈጫለች ሽሮ።
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አታውቅም፣
ሹማምንት፣ በ'ሷ ስም፣ምን እንደሚሰሩ
አነሣኹት እንጂ እኔም ለነገሩ
በፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ
ምን ይጠቅማትና፣ጓያዋን ለማድቀቅ።
ከቶ ማንም የለ፣አበባ የሚሰጣት
ከቶ ማንም የለ፣ከተማ የሚያወጣት
ከቶ ማንም የለ፣በዳንኪራ መላ፣ወጠቧን የሚያቅፋት
ልፋቷም፣ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት።
እንደ ዓባይ ፏፏቴ ሺሕ ዓመትቢንጣለል
ቢጎርፍም ዱቄቱ
እንደ ሲኦል ወለል
ጫፍ የለውም ቋቱ ።
ከዘመናት ባ'ንዱ
መስታወት ፊት ቆማ፣በተወለወለው
ፊቷን ለማየት
ከፀጉሯ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት
ያኔ ይገባታል የተሰጣት እጣ
ከማድቀቅ ቀጥሎ መድቀቅ እንደ መጣ።
የመጅ አገፋፏ አምሳለ ሲሲፈስ
ከቋት ስስት እንጂ ሲሳይ አይታፈስ
ትቢያ ሚተነብይ ዱቄት በዙርያዋ
ከባርኔጣ አይሰፋም የኑሮ ጣርያዋ
"ስትፈጭ የኖረች ሴት " ይህ ነው መጠሪያዋ።
#ሲሲፈስ- በግሪክ ተረት ውስጥ የሚገኝ ተኮናኝ ሲኾን ኩነኔው ያለግብ ድንደፈጋይ መግፋት ነው።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
@sayatmekdi