ክቡር እንግዳችን ታላቁ ረመዳን
ከነፍክብንሳ ከንቅልፍም ሳንባንን
በደምብ ሳንጠግብ ተራዊህ ለይሉን
ሚስኪን ሳናስፈጥር ሳናኸትም ቁርአን
የቁርአን ወር ነበር የሚኸተምበት
ከገፍላ ተላቀን የምንዘክርበት
በዱዓ በሰላት ምንጠነክርበት
ሄደ ግን በቶሎ ሳንጠቀምበት
ያ ረብ! መቼም ቸርነትህ ሁሌም ተከጃይ ነው
ምህረትና አፍውህ ሁሌም ተስፋችን ነው
ከስራችን ይበልጥ እዝነትህ ወሳኝ ነው
ይቅር በለን ረህማን ራህመትህ ቅርብ ነው
ለይለተል ቀድርንም ወፍቀን ያ ረህማን
አልፉርቃን ከዙል ዐርሽ የወረደበትን
ከአንድ ሺ ወራት በላጭ የሆነውን
መልአኮች ከሩህ ጋር የሚወርዱበትን
ወፍቀን ያ ረህማን ለለይል ሰላቱ
ልንፀልይህ ከልብ ልንሰግድ በሌሊቱ
ለምህረትህ ልንቀርብ ልንባል ዐፈውቱ
ልንለማመጥህ ልትለን ፈዐልቱ
ያ ረብ! አፅናን በአምልኮህ አድርገን ሙስተቂም
ረመዳን ሲወጣም በዒባዳህ ምንቆም
ከለይም ከፆሙም መልካምን ማናቀም
የቂን እስኪመጣን ቀጥ አርገን ያ ረሂም
ሰልሰቢል ዙመካን የቅርብ ወንድማችሁ
በርግጥ ገጣሚ ነኝ ብየ አልዋሻችሁ
ብዬ ነው እንግዲህ ያቅሜን ላስታውሳችሁ
ሱጁድ ላይ በሌሊት አውሱኝ በዱዓችሁ
ከነፍክብንሳ ከንቅልፍም ሳንባንን
በደምብ ሳንጠግብ ተራዊህ ለይሉን
ሚስኪን ሳናስፈጥር ሳናኸትም ቁርአን
የቁርአን ወር ነበር የሚኸተምበት
ከገፍላ ተላቀን የምንዘክርበት
በዱዓ በሰላት ምንጠነክርበት
ሄደ ግን በቶሎ ሳንጠቀምበት
ያ ረብ! መቼም ቸርነትህ ሁሌም ተከጃይ ነው
ምህረትና አፍውህ ሁሌም ተስፋችን ነው
ከስራችን ይበልጥ እዝነትህ ወሳኝ ነው
ይቅር በለን ረህማን ራህመትህ ቅርብ ነው
ለይለተል ቀድርንም ወፍቀን ያ ረህማን
አልፉርቃን ከዙል ዐርሽ የወረደበትን
ከአንድ ሺ ወራት በላጭ የሆነውን
መልአኮች ከሩህ ጋር የሚወርዱበትን
ወፍቀን ያ ረህማን ለለይል ሰላቱ
ልንፀልይህ ከልብ ልንሰግድ በሌሊቱ
ለምህረትህ ልንቀርብ ልንባል ዐፈውቱ
ልንለማመጥህ ልትለን ፈዐልቱ
ያ ረብ! አፅናን በአምልኮህ አድርገን ሙስተቂም
ረመዳን ሲወጣም በዒባዳህ ምንቆም
ከለይም ከፆሙም መልካምን ማናቀም
የቂን እስኪመጣን ቀጥ አርገን ያ ረሂም
ሰልሰቢል ዙመካን የቅርብ ወንድማችሁ
በርግጥ ገጣሚ ነኝ ብየ አልዋሻችሁ
ብዬ ነው እንግዲህ ያቅሜን ላስታውሳችሁ
ሱጁድ ላይ በሌሊት አውሱኝ በዱዓችሁ